Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124
Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124

ይህ ጦማር (ማለትም ክፍል 4) ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው በሚቀድሙት ክፍሎች (ማለትም በክፍሎች 1 እስከ 3) ላይ ስለሆነ፣ ይህን ክፍል ከማንበብወ በፊት የቀደሙትን ክፍሎች ቢያንስ ቢያንስ በገረፍታ ይመልከቱ።
sign = ምልክት
symbol = ወመል
symbolize = ወመለ
notation = ሞከስ፣ ሙከሳ
notation (verb) = ሞከሰ
maximum = ገብዲስ
maximize = ገበደሰ
maximization = ግብደሳ
minimum = ጨቅሊስ
minimize = ጨቀለሰ
minimization = ጭቅለሳ
scalar = ሐዝተን
vector = ፍላስተን
direction of vector = የፍላስተን አቅጣጫ
magnitude of vector = የፍላስተን ብክረት


ፍላስተኖች (vectors) ሲባሉ ያቅጣጫ (direction) እና የብክረት (magnitude) የሚባሉ ሁለት ጠባዮች (properties) ስላላቸው፣ እኩል ሊሆኑ የሚችሉት ሁለቱም ጠባዮቻቸው እኩል ከሆኑ ብቻ ነው። ስለዚህም ሁለት ፍላስተኖች እኩል ናቸው የሚባሉት

ሁለት ፍላስተኖች (two vectors) የርስበራሳቸው ሉንታወች (negatives of each other) ናቸው የሚባሉት እኩል ብክረት (equal magnitude) እና በተጨማሪ ደግሞ ተቃራኒ አቅጣጫወች (opposite directions) ካላቸው ብቻ ነው። ስለዚህም፣ ፍላስተን B የፍላስተን A ሉንታ (negative)ነው የሚባለውና በመልክ B = -A የሚጻፈው


project (verb) – ፈገመ
projection – ፈገም
projection (projecting) – ፍገማ

ማናችው ፍላስተን (vector) በሆነ አቅጣጫ ያለው ፈገም (projection)፣ ፍላስተኑ በዚያ አቅጣጫ ያለው ምንዝር (component) በመባል ይታወቃል።

ፍላስተን B በፍላስተን A አቅጣጫ ያለው ፈገም (projection) ለፍላስተን A ኩልኩት (parallel) ስለሆነ፣ የኩልኩልነትን ምልከት (| |) በመጠቀም በሞከስ (notation) B| | ይሞከሳል።
ሩንጌራባዊ ቀንጅ ስርካትን (rectangular coordinate system) በተመለከተ ማናቸውም ፍላስተን (vector) በቀንጅ ስርካቱ ረቲዶች (axes) ላይ ያሉት ፈገሞች (projections) የፍላስተኑ ሩንጌራባዊ ምንዝሮች (rectangular components) ይባላሉ።

በ xy-ቀንጅ ስርካት (xy-coordinate system) ላይ የማናቸውም ፍላስተን (vector) x እና y ምንዝሮች (x and y components) በፍላስተኑ ብክረት (magnitude) እና ፍላስተኑ ከ x-ረቲድ (x-axis) ጋር በሚሰራው ዘዌ (angle) አንጻር በሚከተሉት ቀመሮች ይሰጣሉ።

የፍላስተን x እና y ምንዝሮች (x and y components) ወንታ እሴት (positive value) ወይም ሉንታ እሴት (negative value) ሊኖራቸው ይችላል። የፍላስተኖቹ ወንታነት (positiveness) ወይም ሉንታነት (negativeness) የሚወሰነው ደግሞ የፍላስተኑ ራስ (head of vector) በሚውልበት የ xy-ቀንጅ ስርካት (xy-coordinate system) ሩቤ (quadrant) ላይ ነው።



ያንድ ፍላስተን (vector) ምንዝሮች (components) ከታወቁ፣ ራሱን ፍላስተኑን፣ የፍላስተኑን ብክረት (magnitude) እና የፍላስተኑን አቅጣጫ (direction) በሚከተሉት ቀመሮች መሠረት ማስላት (calculate) ይቻላል።


ፍላስተኖች ሦስት ዓይነት ብዜሮች (multiplications, products) ማለትም ብዜቶች አሏቸው።

ማናቸውም ፍላስተን (vector) በማናቸውም ሐዝተን (scalar) ማለትም በማናቸውም ወንታ (positive) ወይም ሉንታ (negative) ወናብ ቁጥር (real number) ሊበዘር (multiplied) ማለትም ሊባዛ ይችላል። በብዜሩ (multiplication) የሚገኘው ውጤት (result) ደግሞ ከተበዛሪው ፍላስተን ጋር ኩልኩት (parallel) ወይም ኢኩልኩት (antiparallel) የሆነ ሌላ ፍላስተን (another vector) ነው። ለምሳሌ ያህል ፊደል A አንድን ፍላስተን ቢወክል፤

ባጠቃላይ አነጋገር ደግሞ የፍላስተን ብዜር በሐዝተን (multiplication of a vector by a scalar) በሚከተለው መንገድ ይበየናል (defined)።


ምሳሌ፤ ከዚህ በታች የተመለከቱት የፍልሰት ፍላስተኖች (displacement vectors) A እና B ያላቸውን ነጥብ ብዜር (dot product) A∙B ፈልግ።

የሁለት ፍላስተኖች ነጥብ ብዜር (dot product) ማለት ያንደኛው ፍላስተን ብክረት (magnitude) እና ሌላኛው ፍላስተን ባንደኛው ፍላስተን አቅጣጫ ያለው ፈገም (projection) ወይም ምንዝር (component) ብዜር (product) ማለት ነው። ይህም መሆኑን በሚከተለው ሱርፊክ (figure) ላይ ተመልክቷል።









የነጥብ ብዜር (dot product) ምንዝር መልከን (component form) የሚሰጠውን ቀመር (formula) የነጥብ ብዜርን (dot product) አስነዋኝ ጠባይ (commutative property) እና አስከፋፋይ ጠባይ (distributive property) እንዲሁም የቶካድ ፍላስተኖችን (unit vectors) ነጥብ ብዜር ጠባይ በመጠቀም በመከተለው መንገድ በቀላሉ መረቸግ (derive) ማለትም ማግኘት ይቻላል።

ምሳሌ፤ ለሚከተሉት በምንዝር መልክ (component form) ለተሰጡ ሁለት ፍላስተኖች A እና B የፍላስተኖቹን ነጥብ ብዜር (dot product) እንዲሁም በፍላስተኖቹ አቅጣጫወች መካከል ያለውን ዘዌ (angle) ፈልግ።

መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com