ስፍረት (Dimension)
- ስፍረት የሚለው ያማረኛ ቃል dimension የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል። ከዚህም ስፍረታዊ (dimensional) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ስፍረት (dimension) ማለት ያሰፋፈር (ማለትም ያለካክ) ወይም የልኬት ሁኔታ እንደ ማለት ነው።
- ለምሳሌ ያህል ቀጤ መስመር (straight line) ያለው ርዝመት (length) ብቻ ስለሆነ፣ አንድ ስፍረታዊ (one dimensional) ነው ይባላል።
- ስፋት (area) ርዝመት (length) እና ወርድ (width) ስላለው ሁለት ስፍረታዊ (two dimensional) ነው ይባላል።
- ሳጥን (box) ርዝመት (length)፣ ወርድ (width) እና ከፍታ (height) ስላለው ሦስት ስፍረታዊ (three dimensional) ነው ይባላል።
- ነጥብ (point) ርዝመምትም፣ ወርድም ሆነ ከፍታ ስለሌለው ዳዶ ስፍረታዊ (zero dimensional) ነው ይባላል።
- በተጨማሪ ደግሞ ጊዜ (time) የጊዜ ስፍረት (dimension of time) አለው፣ ቁሰት (mass) ደግሞ የቁሰት ስፍረት (dimension of mass) አለው ይባላል።
- ፍጥነትን (speed) ብንወስድ ርዝመትን (length) በጊዜ (time) በመደሸር (divide) ማለትም በማካፈል የሚገኝ እሴት ስለሆነ ስፍረቱ (dimension) ርዝመት በጊዜ (length over time) ነው ይባላል፣ ወዘተ.
dimension (dimensionality) = ስፍረት
dimensional = ስፍረታዊ፣ ስፍረታዊ
zero dimensional = ዳዶ ስፍረታዊ፣ ዳዶ ስፍረታም
one dimensional = አንድ ስፍረታዊ፣ እንድ ስፍረታም
two dimensional = ሁለት ስፍረታዊ፣ ሁለት ስፍረታም
three dimensional = ሦስት ስፍረታዊ፣ ሦስት ስፍረታም
finite (infinite) dimensional = ወዳኢ (ኢወዳኢ) ስፍረታም
dimensionless = ስፍረትአልባ (ስፍረታልባ)
ስፍረታዊ ፀንቃሚነት (Dimensional Consistency)
- በጉሲን (physics) ውስጥ እሴቶች (values) ሊደመሩ (added) ወይም ሊቀነሱ (subtracted) የሚችሉት ያውቴ ስፍረት (same dimension) ካላቸው ብቻ ነው።
- ለምሳሌ ያህል ርዝመትን (length) መደመር ወይም መቀነስ የሚቻለው ከርዝመት ጋር ወይም ከርዝመት ላይ ብቻ ነው።
- ስፋትን (area) መደመር ወይም መቀነስ የሚቻለው ከስፋት ጋር ወይም ከስፋት ላይ ብቻ ነው።
- ጽሐርን (volume) መደመር ወይም መቀነስ የሚቻለው ከጽሐር ጋር ወይም ከጽሐር ላይ ብቻ ነው።
- ፍጥነትን (speed) መደመር ወይም መቀነስ የሚቻለው ከፍጥነት ጋር ወይም ከፍጥነት ላይ ብቻ ነው።
- ይህ አጠቃላይ እውነታ ደግሞ ሎሚን ከብርቱካን ጋር መደመር አይቻልም በማለት ባጭሩ ይገለጻል።
- በማናቸውም ጉሲናዊ ቀመር (physics formula) ላይ በመደመር (addition) ወይም በመቀነስ (subtraction) ምልክት የሚነጣጠሉ የቀመሩ ክፍሎች ቂራጎች (terms) ሲባሉ፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ቃል እና ሐረግ ከሚሉት ቃሎች ነው።
- ስለዚህም በማናቸውም ጉሲናዊ ቀመር (physics formula) ላይ የሚገኙ ሁሉም ቂራጎች (all terms) ያውቴ ስፍረት (same dimension) ሊኖራቸው ይገባል ማለት ነው። ይህን ሐቅ የሚያሟላ ጉሲናዊ ቀመር ደግሞ ስፍረታዊ ፀንቃሚነት (dimensional consistency) አለው ይባላል። አለያ ስፍረታዊ አልፀንቃሚ (dimensionally inconsistent) ይባላል።
- ፀንቃሚ (consistent) ማለት ስምሙ የሆነ እንደ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ፅኑ እና ቋሚ ከሚሉት ቃሎች ነው። ግሱም ሲረባ ፀነቀመ፣ ፅንቅም (ፅንቁም)፣ ፀንቃሚ፣ ፅንቀማ፣ ፅንቅመት፣ ፅንቃሜ፣ ፅንቃሞሽ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም። ፀነቀመ ማለት ፀንቃሚ ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ፅንቅም (ፅንቁም) ማለት ደግሞ የተፀነቀመ ማለት ነው።
- የጉሲን ቀመሮች (physics formulas) ስፍረታዊ ፀንቃሚ (dimensionally consistent) መሆን አለመሆናቸውን የማረጋገጡ ሂደት ስፍረታዊ ትንታኔ (dimensional analysis) ይባላል። ስለ ስፍረታዊ ትንታኔ ወደፊት በሌላ ጦማር ላይ በሰፊው እናወሳለን።
term (mathematics) = ቂራግ
consistence (consistency) = ፅንቀማ፣ ፅንቅመት፣ ፀንቃሚነት
consistent = ፀንቃሚ
consistent (verb) = ፀነቀመ
inconsistence (inconsistency) = አልፅንቀማ፣ አልፅንቅመት፣ አልፀንቃሚነት
inconsistent = አልፀንቃሚ
dimensional analysis = ስፍረት ትንተና፣ ስፍረታዊ ትንተና
dimensional consistency = ስፍረታዊ ፀንቃሚነት
dimensionally consistent = ስፍረታዊ ፀንቃሚ
አቻ (Equivalent)፣ አቻሚ (Equilibrant) እና አችመት (Equilibrium)
- አቻ (equivalent) ከሚለው ቃል ደግሞ አቻሚ (equilibrant, equilibrator) የሚለውን ቃል እናገኛለን። አቻሚ (equilibrant) ማለት አቻ የሚያደርግ፣ የሚያማዝን እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ አቸመ (equilibrate)፣ እችም (እቹም) [equilibrated]፣ አቻሚ (equilibrating)፣ እቸማ (equilibration)፣ እቻሜ፣ እቻሞሽ እያለ ይሄዳል።
- አችመት (equilibrium) ወይም አችመም (equlibrium) ማለት ደግሞ እቸማ (equilibration) የተከሰተበት ሁኔታ እንደ ማለት ነው።
equivalent = አቻ
equilibrant = አቻሚ
equilibrate = አቸመ
equilibrium = አችመት፣ አችመም
equilibrium state = አችመት ሁነት
unstable (unstable) equilibrium = ርጉ (አልርጉ) አችመት
እርፋታ (rest)፣ ኑመት (static) እና ኑምሲን (statics)
- ኖመ ማለትም ተኛ፣ አንቀላፋ ከሚለው የግእዝ ቃል ኑመት (being static) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ኑመት (being static) ማለት እርፋታ (rest) እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ነወመ (to rest)፣ ንውም (rested)፣ ነዋሚ (resting)፣ ንወማ (resting)፣ ንዋሜ፣ ንዋሞሽ እያለ ይሄዳል
- ኑም (static) እና ሲን (logy) ከሚሉት ኑምሲን (statics) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ኑምሲን (statics) ማለት በእርፋታ (rest) ላይ ያሉ ኑም (static) አካሎች፣ ባጠቃላ አነጋገር ደግሞ ባችመት (equilibrium) ላይ ያሉ አካሎች የሚጠኑበት የጉሲን (physics) ዘርፍ ነው።
static (resting) = ኑም፣ ነዋሚ ኗሚ
static (being static) = ኑመት፣ ንወማ
static (verb) [rest] = ነወመ
statics = ኑምሲን
rest = እርፋታ፣ ኑመት
rest energy = ኑመት ጉልበት
rest mass = ኑመት ቁሰት
ሑሰት (Motion, Movement)
- በግእዝ ሐወሰ ማለት ሮጠ፣ ፈጠነ፣ ቀለጠፈ፣ ቸኮለ ማለት ነው። ከዚህም ሑሰት (motion, movement) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ሑሰት (motion, movement) ማለት እንቅስቃሴ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ሖሰ (move)፣ ሑስ (ሑስስ) [moved]፣ ሗሲ (moving)፣ ሑሰት (motion, movement) እያለ ይሄዳል።
motion (movment) = ሑሰት
move = ሖሰ
moving = ሗሲ
moved = ሑስ፣ ሑስስ
ክልበት (Kinetic)፣ ክልበቲክስ (Kinematics) እና ክልበትሲን (Kinetics)
- ባማረኛ ከለበ ማለት እንደ ከልብ (ውሻ) ሆነ፣ ቸኮለ፣ ሮጠ፣ ተክለፈለፈ ማለት ነው፣ ከላባ እንዲሉ። ከዚህም ክልበት (kinetic) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ክልበት (kinetic) ማለት ሑሰት (motion) እንደማለት ነው።
- ክልበት (kinetic) እና ማተማቲክስ (mathematics) ከሚሉት ቃል ክልበቲክስ (kinematics) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ክልበቲክስ (kinematics) ማለት ያካሎች አሗሗስ (motion) የሚብራራበት (described) የጉሲን (physics) ዘርፍ ነው።
- በሌላ አባባል ክልበቲክስ (kinematics) ማለት ያካሎች የሑሰት እንዴት (the how of motion) የሚጠናበት የጉሲን (physics) ዘርፍ ነው። ወይም ደግሞ ክልበቲክስ (kinematics) ማለት አከሎች ለምን እንደሚሆሱ ሳይሆን እዴት እንደሚሆሱ የሚጠናበት የጉሲን ዘርፍ ነው።
- እንደገናም በሌላ አባባል ክልበቲክስ (kinematics) ማለት የክልበት ሒሳብ (mathematics of motion) ማለት ነው።
- ክልበቲክስ (kinematics) የሚያተኩረው በፍልሰት (displacement)፣ ፍጥነት (speed)፣ ሶፊሳ (velocity) እና ጥድፈት (acceleration) ላይ ነው።
- በተጨማሪ ደግሞ ክልበት (kinetic) እና ሲን (logy) ከሚሉት ክልበትሲን (kinematics) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ክልበትሲን (kinematics) ማለት ያካሎች አሗሗስ (motion) የሚገለጽበት (described) የጉሲን (physics) ዘርፍ ነው።
- በሌላ አባባል ክልበትሲን (kinetics) ማለት ያካሎች የሑሰት ለምን (the why of motion) የሚጠናበት የጉሲን (physics) ዘርፍ ነው። ወይም ደግሞ ክልበትሲን (kinetics) ማለት አካሎች ለምን እንደሚሆሱ፣ ማለትም የሁሰት መንስዔ ምን እንደሆነ የሚጠናበት የጉሲን ዘርፍ ነው።
- እንደገናም በሌላ አባባል ክልበትሲን (kinetics) ማለት የክልበት ሰገል (the science of motion) ማለት ነው።
- ክልበትሲን (kinetics) የሑሰት ሰገል (science of motion) ማለትም የሑሰት ጥናት ስለሆነ የተለያዩ የሑሰት ግንገናወችን (theories of motion) ያካትታል። ከነዚህም ውስጥ አንዱና ዋናው የኒውተን የሑሰት ግንገና (Newton’s theory of motion) ነው።
- ክልበትሲን (kinetics) የሚያተኩረው በቁሰት (mass) እና ግሳብ (force) ላይ ነው።
kinematic (kinematical) = ክልበቲክስ፣ ክልበቲክሳዊ
kinematical equations = ክልበቲክሳዊ እኩልታወች
kinematics = ክልበቲክስ
kinetic = ክልበት፣ ክልበታዊ
kinetic energy – ክልበታዊ ጉልበት
kinetic friction – ክልበታዊ ሰበቃ
kinetic theory – ክልበታዊ ግንገና
kinetics – ክልበትሲን
ኑምሲን (statics)፣ ሑሲን (Dynamics)፣ ሐምሲን (Mechanics)
- ኑም (static) እና ሲን (logy) ከሚሉት ኑምሲን (statics) የሚለውን ቃል እንደምናገኝ ተመልከተናል።
- በተመሳሳይ መንገድ ሑሰት (motion) እና ሲን (logy) ከሚሉት ሑሲን (dynamics) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ሑሲን (dynamics) ክልበቲክስን (kinematics) እና ክልበትሲንን (kinetics) የሚያጠቃልል ቃል ነው።
- አብዛኛውን ጊዜ ግን ሑሲን (dynamics) ሲባል ክልበትሲን (kinetics) ማለት ነው።
- ሑሲን (dynamics) እና ሑሴን እንዳይምታቱብወት። ሑሴን ትርጉሙ ውቤ ወይም ውቡ ማለት የሆነ ዐረባዊ ስም ነው።
- ሑሲን (dynamics) እና ኑምሲን (statics) ከሚሉት ቃሎች ሐምሲን (mechanics) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ሐምሲን (mechanics) ሑሲንን (dynamics) እና ኑምሲንን (statics) የሚያጠቃልል ቃል ነው።
- ሑሲን (dynamics) ራሱ ደግሞ ክልበቲክስን (kinematics) እና ክልበትሲንን (kinetics) ስለሚያጠቃልል፣ ሐምሲን (dynamics) ሲባል ኑምሲንን (statics)፣ ክልበቲክስን (kinematics) እና ክልበትሲንን (kinetics) ያጠቃልላል።
mechanics = ሐምሲን
mechanical = ሐምሲናዊ
mechanical energy – ሐምሲናዊ ጉልበት
አንድ ስፍረታዊ ክልበቲክስ (One Dimensional Kinematics)
- አንድ ስፍረታዊ ክልበቲክስ (one dimensional kinematics) ማለት በቀጤ መስመር (straight line) ላይ የሚካሄድ ሑሰትን (motion) የተመለከተ ክልበቲክስ (kinematics) ማለት ነው።
- በሌላ አባባል አንድ ስፍረታዊ ክልበቲክስ (one dimensional kinematics) ማለት የቀጤ መስመር ሑሰት ሒሳብሲን (mathematics of motion on a straight line) ማለት ነው።
መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com