ግኡዝ (Physical) እና ጉሲን (Physics )
ጉሲን (physics) ማለት በንግሊዘኛ ፊዚክስ የሚባለው ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ግኡዝ (physical) [ማለትም ረቂቅ ያልሆነ፣ የሚያዝ፣ የሚጨበጥ] የሚለውን ቃል ሲን (logy) ከሚለው ኋልጡፍ (suffix) [ማለትም ባዕድ መድረሻ] ጋር በማጣመር ነው።
ከዚህም ጉሲነኛ (physicist) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ጉሲነኛ ማለት የጉሲን ባለሙያ ወይም ምሁር ማለት ሲሆን፣ ለሴት ሲሆን ደግሞ ጉሲነኝት ይሆናል።
physical = ግኡዝ physics = ጉሲን physicsist = ጉሲነኛ ፣ ጉሲነኝት
ወርከፍ፣ አክዘንግ፣ ገማዘንግ እና ጽሐር
ወርከፍ (size) ማለት መጠን፣ ትልቅነት፣ ግዝፈት ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ወርድ ፣ ርዝመት እና ከፍታ ከሚሉት ነው።
አክባቢ ዘንግ ከሚለው ሐረግ አክዘንግ (radius) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ገማሽ ዘንግ ከሚለው ሐረግ ደግሞ ገማዘንግ (diameter) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ጽሐር (volume) ማለት ይዘት እንደ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ጽሕርት (ማለትም ድስት) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው።
size = ወርከፍ radius = አክዘንግ diameter = ገማዘንግ volume = ጽሐር
የቀኒጥ ወርከፍ (Size of Atom)
ቅንጣት ከሚለው ቃል ቀኒጥ (atom) የሚለውን ቃል እናገኛለን። የቀኒጥ ወርከፍ (size of atom) ማለት የቀኒጥ መጠን እንደ ማለት ነው።
ያይነተኛ ቀኒጥ አክዘንግ (radius of atom) በቅርበዛ (approximately) 50 ራብጢኖሜትር (50 picometer = 50 x 10-12 m) ገደማ ነው። ስለዚህም የቀኒጥ ቅርጽ (shape of atom) ሉል (sphere) እንደሆነ አድርገን ብንወሰድና የሉልን የጽሐር ቀመር (formula for volume of sphere) ማለትም V = (4ℼr3 /3) ብንጠቀም የቀኒጥ ወርከፍ (size of atom) በቅርበዛ (approximately) 5 x 10-31 m3 መሆኑን እናገኛለን።
ይህ የሚያሳየው ቀኒጥ (atom) ሲባል እጅግ ሲበዛ ቲኑፍ (tiny) መሆኑን ነው። ቲኑፍ (tiny) ማለት እጅግ በጣም ትንሽ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ትንሽ እና ግዙፍ (huge) ከሚሉት ቃሎች ነው። ቲኑፍ የግዙፍ ተቃራኒ ነው።
ለምሳሌ ያህል የቅንጣት ሰናፍጭ (mustard) አክዘንግ (radius) በቅርበዛ (approximately) 500 ካልጢኖሚትር (500 micrometer = 500 x 10-6 ) ስለሆነ፣ ወርከፏ በቅርበዛ (approximately) 5 x 10-10 m3 ይሆናል። ይህ ማለት ደግሞ የሰናፍጭ ወርከፍ (size) የቀኒጥን ወርከፍ 1021 ጊዜ ይበልጣል ማለት ነው። በሌላ አባባል በቅንጣት ሰናፍጭ ውስጥ በቅርበዛ 1021 ቀኒጦች ይገኛሉ ማለት ነው። የቀኒጥ ቱኒፍነት እስከዚህ ድረስ ነው።
ትንሽ (Small) እና ትልቅ (Large) በጉሲን (Physics)
በጉሲን (physics) ውስጥ አካሎች (bodies) ትንሽ (small) ወይም ትልቅ (large) የሚባሉት ወርከፎቻቸውን (sizes) ከቀኒጥ ወርከፍ (size of atom) ጋር በማነጻጽር ነው።
በጉሲን ውስጥ ወርከፋቸው (sizes) ከቀኒጥ ወርክፍ (size of atom) ብዙ እጠፍ የሚበልጥ አካሎች (bodies) ትልቅ አካሎች (large objects) ሲባሉ፣ ወርከፋቸው ከቀኒጥ ወርከፍ የሚያንስ ወይም በቀኒጥ ወርከፍ ደረጃ የሆነ አካሎች ደግሞ ትንሽ አካሎች (small objects) ይባላሉ።
ስለዚህም በጉሲን ውስጥ ትንሽ (small) የሚባሉት ተልኑስን (electron)፣ ቀዳምኑስን (proton)፣ ገልኑስን (neutron) የመሳሰሉ ታሕትቀኒጥ እኑሶች (subatomic particles)፣ ራሳቸው ቀኒጦች (atoms) እና ጥቂት ቀኒጦችን ያቀፉ ትናንሽ ፀምሪቆች (small molecules) ብቻ ናቸው ማለት ነው። ፀምሪቅ (molecule) የሚለው ቃል የተገኘው ፅምር ቀኒጥ ከሚለው ሐረግ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ በሠርካዊ (everyday) አመለካከት ኢምንት ናቸው የሚባሉት አካሎች ሁሉ በጉሲን እይታ ሲታዩ ግን ትልቅ ብቻ ሳይሆኑ ግዙፎች ናቸው ማለት ነው።
ለምሳሌ ያህል ሴሎች (cells)፣ ሪማወች (bacteria) እና ቁፋወች (viri) ባዘቦት እይታ ሲታዩ እጅግ በጣም አናሳ ቢሆኑም፣ በጉሲን እይታ ሲታዩ ግን ወርከፋቸው ከቀኒጥ ወርክፍ ከካልጃኖ (million) ጊዜ በላይ የሚበልጥ እጅግ በጣም ግዙፍ አካሎች ናቸው። ሪማ (bacterium) የሚለው ቃል የተገኘው ራሙ (ትል) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ሲሆን፣ ቁፋ (virus) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ ቁፋ (ጉንፋን) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው።
ሌላው ቀርቶ አያሌ ቀኒጦችን ያቀፉ ትላልቅ ፀምሪቆች (large molecules) እንኳን በጉሲን እይታ ሲታዩ ግዙፍ አካሎች ናቸው።
የብርሃን ፍጥነት
ንዑስ ደቂቃ ከሚለው ሐረግ ኑሲቃ (second) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ስለዚህም ኑሲቃ ማለት ሴኮንድ እንለው የነበረው ነው ማለት ነው። አንድ ደቂቃ (minute) ስልሳ ኑሲቃ ነው።
ብርሃን ወና (vacuum) ውስጥ የሚጓዝበት ፍጥነት ሦስት መቶ ሺ ሃጅኖሜትር በኑሲቃ (300,000 kilometer per second) ወይም 30 ካልጃኖሜትር በኑሲቃ (30 megameter per second) ነው።
ብርሃን አየር (air) ውስጥ የሚጓዝበትም ፍጥነት ወና (vacuum) ውስጥ ከሚጓዝበት ፍጥነት ጋር በቅርበዛ (approximately) እኩል ነው።
ብርሃን ወና ውስጥ እንዲሁም አየር ላይ ያለው ፍጥነት በፊደል c ይወከላል።
ብርሃን በዚህ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ፍጥነቱ እየተጓዝ
ምድርን ወገቧ (equator) ላይ በኑሲቃ (second) ከሰባት ጊዜ በላይ ይዞራታል።
ከምድር ጨረቃ ደርሶ መልስ የሚፈጅበት ጊዜ 2.5 ኑሲቃ (second) ብቻ ነው።
ከፀሐይ ተነስቶ ምድር ለመድረስ የሚፈጅበት ጊዜ 8 ደቂቃ (minute) ብቻ ነው።
የብርሃን ፍጥነት እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት ከመሆኑ የተነሳ፣ ከፍተኛ ፍጥነቶች የሚባሉ የተለያዩ ነገሮች ፍጥነቶች ከብርሃን ፍጥነት ጋር ሲነጻጸሩ ኢምንት ይሆናሉ።
የድምፅ ፍጥነት (speed of sound) 0.3 km/s ሲሆን፣ የብርሃንን ፍጥነት 0.0001% ብቻ ነው።
የጥይት ፍጥነት (speed of bullet) ቢበዛ 1.5 km/s ሲሆን፣ የብርሃንን ፍጥነት 0.0005% ነው።
የተዋጊ ሰታይ ፍጥነት (speed of fighter plane) ቢበዛ 2 km/s ሲሆን፣ የብርሃንን ፍጥነት 0.0007% ብቻ ነው። ሰታይ (plane) የሚለው ቃል የተገኘው ሰቲት (ማለትም ለጥ ያለ፣ ቀጥ ያለ፣ የተዘረጋ ከሚለው) የግእዝ ቃል ነው።
የቤናጉራዊ ፈናሪ ደርባጊ (intercontinental ballistic missile, ICBM) ፍጥነት ቢበዛ 8 km/s ሲሆን፣ የብርሃንን ፍጥነት 0.003% ብቻ ነው። ፈናሪ (ballistic) የሚለው ቃል የተገኘው ፈነረ (ጣለ፣ ወረወረ፣ አሽቀነጠረ) ከሚለው ያማረኛ ቃል ሲሆን፣ ደርባጊ (missile) የሚለው ቃል የተገኘው ደረበየ (ደጋግሞ፣ መላልሶ ወረወረ፣ መታ፣ ወገረ፣ ወጋ) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው። ቤናጉራዊ (intercontinental) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ ቤን (inter) እና አህጉር (continent) ከሚሉት ቃሎች ሲሆን፣ ቤን (inter) የተገኘው ደግሞ በይነ (መካከል) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው። ቤናጉራዊ ማለት አህጉር አቋራጭ ወይም አህጉሮችን አካታች ማለት ነው።
የምድር ምሕዋራዊ ፍጥነት (orbital speed of the Earth) ማለትም ምድር በፀሐይ ዙርያ ስትሖር (ስትዞር) የምትጓዝበት ፍጥነት ማለት ነው። ይህም ፍጥነት በቅርበዛ (approximately) 30 km/s ሲሆን፣ የብርሃንን ፍጥነት 0.01 % ብቻ ነው።
ቀሳን (Slow) እና ፈጣን (Fast)
ቀስ አለ (በቀስታ ሄደ) የሚለውን ፈጣን (fast) ከሚለው ጋር በማመሳሰል ቀሳን (slow) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ቀሳን (slow) ማለት ቀስተኛ፣ በቀስታ የሚሄድ ማለት ነው። በሌላ አባባል ቀሳን የፈጣን ተቃራኒ ነው።
የቀሳን (slow) ግስ ሲረባ ቀሰነ (to slow) ፣ ቅስን ( ቅሱን ) [slowed] ፣ ቀሳኒ ( ቀሳኝ ) [slowing] ፣ /ቅሰና\ (slowing) ፣ \ቅስነት/ እያለ ይሄዳል።
ቀሰነ የፈጠነ ተቃራኒ ሲሆን፣ ቅሰና የፈጠና፣ ቅስነት ደግሞ የፍጥነት ተቃራኒወች ናቸው። የሚጠብቀው /ቅሰና\ እና የማይጠበቀው \ቅስና/ (ቄስነት) እንዳይምታቱብወት አደራ፣ ምንም ግንኙነት የላቸውምና።
fast = ፈጣን fast (verb) = ፈጠነ slow = ቀሳን slow (verb) = ቀሰነ
ቀሳን (Slow) እና ፈጣን (Fast) በጉሲን (Physics)
በጉሲን (physics) ውስጥ አካሎች (bodies) ቀሳን (slow) ወይም ፈጣን (fast) የሚባሉት ፍጥነታቸውን (speed) ከብርሃን ፍጥነት (speed of light) ጋር በማነጻጽር ነው።
በጉሲን ውስጥ ፍጥነታቸው (sizes) የብርሃንን ፍጥነት (300,000 km/s) 10% በላይ የሆነ (ማለትም ፍጥነታቸው ከ 30,000 km/s በላይ የሆነ) አካሎች (bodies) ፈጣን አካሎች (fast objects) ሲባሉ፣ ፍጥነታቸው የብርሃንን ፍጥነት 10% በታች የሆነ (ማለትም ፍጥነታቸው ከ 30,000 km/s በታች የሆነ) አካሎች ደግሞ ቀሳን አካሎች (slow objects) ይባላሉ።
በሠርካዊ (everyday) አመለካከት ፍጣን (fast) ናቸው የሚባሉት አካሎች ሁሉ በጉሲን (physics) እይታ ሲታዩ ግን እጅግ በጣም ቀሳን (slow) ከመሆናቸው የተነሳ እንደማይንቀሳቀሱ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ።
ለምሳሌ ያህል ፍጥነታቸው 8 km/s ገደማ የሆነው ቤናጉራዊ ፈናሪ ደርባጊወች (Intercontinental Ballistic Missiles) እጅግ ፈጣን ከሚባሉት ሰውሠራሽ (man made) ነገሮች መካከል ቢሆኑም፣ በጉሲን እይታ ሲታዩ ግን ፍጠነታቸው ከ 30,000 km/s እጅግ በጣም ያነሰ ስለሆነ፣ እንደሚሄዱ የማይቆጠሩ እጅግ ሲበዛ ቀሳኖች (extremely slow) ናቸው።
በጉሲን ውስጥ ፈጣን (fast) የሚባሉት ሙርኪታ (laboratory) ውስጥ በተለያዩ ዓይነት እኑስ ጠዳፊወች (particle accelerators) ተጠድፈው (accelerated) እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት እንዲያገኙ የሚደረጉ ታሕትቀኒጥ እኑሶች (subatomic particles) እና ከህዋ ወደ ምድር በከፍተኛ ፍጥነት የሚገቡ ካይጋዊ እኑሶች (cosmic particles) ብቻ ናቸው። ካይጋ (cosmos) ማለት ሁለንተና ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ማኪዮጋ (ማስማማት፣ ማስታረቅ) ከሚለው የወላይትኛ ቃል ነው።
ሠርካዊ አካሎች (Everyday Objects) በጉሲን
ሠርክ (everyday) ማለት በየጊዜው፣ በየቀኑ፣ በየዕለቱ፣ ዘወትር ማለት ነው፣ ሠርካለም እንዲሉ ሁሌ ዓለም፣ ሁሌ ደስታ ሊሉ። እንዲሁም የሠርክ ልብስ፣ የሠርክ ፀሎት እንዲሉ።
ስለዚህም ሠርካዊ አካሎች (everyday objects) ማለት ሠርክ የምናያቸው (ማለትም ዘወትር የሚያጋጥሙን)አካሎች (bodies) ማለት ነው።
ሠርካዊ አካሎች ከሞላ ጉደል ሁሉም ቀሳን (slow) እንዲሁም ትልቅ (large) ናቸው።
በሌላ አባባል ሠርካዊ አካሎች ከሞላ ጎደል ሁሉም በሚባል ደረጃ ፍጥነታቸው ከብርሃን ፍጥነት አንጻር ኢምንት ፣ ወርከፋቸው ደግሞ ከቀኒጥ ወርከፍ አንጻር ጃምንት ነው። ጃምንት የኢምንት ተቃራኒ ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ጃን (ትልቅ) እና ኢምንት ከሚሉት ነው።
የጉሲን መሠረታዊ ዱሪወች (Topics) እና ጥያቄወች
ጉሲን (physics) የሰገል (science) ዘርፍ ሲሆን በሚከተለው መንገድ ባጭሩ ሊበየን (defined) ይችላል። በዚህ ብያኔ ላይ ሁንዳ (universe) ማለት ሁለንተና እንደ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ሁንዳ (ሁሉም) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው። ሁንዳ (universe) ከሚለው ቃል ሁንዳዊ (universal)፣ ሁንዳዊ ሕግ (universal law) የመሳሰሉትን እናገኛለን።
ብያኔ (definition)፡ ጉሲን (physics) የሁንዳ መሠረታዊ ሕጎች (fundamental laws of the universe) ስርካታዊ ጥናት (systematic study) ነው።
በጉሲን ውስጥ የሚጠኑት መሠረታዊ ዱሪወች (fundamental topics) ዐራት ሲሆኑ፣ እነሱም ሑሰት (motion)፣ ግሳብ (force)፣ ጉልበት (energy) እና ቁስ (matter) ናቸው። ዱሪ (topic) ማለት የመወያያ ርዕስ እንደ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ዱሬ (ርዕስ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው። ዱሪ እና ድሪ (ያንገት ጌጥ) እንዳይምታቱብወት።
ሑሰትን (motion) በተመለከተ ጉሲን (physics) ሊመልሳቸው የሚሞክራቸው መሠረታዊ ጥያቄወች የሚከተሉትን የመሳሰሉ ናቸው።
ሑሰት ምንድን ነው ?
ሑሰትን ከህዋ (space) እና ጊዜ (time) እንፃር እንዴት መግለጽ ይቻላል?
የሑስት መንስዔው ምንድን ነው ?
ግሳብን (force) በተመለከተ ጉሲን (physics) ሊመልሳቸው የሚሞክራቸው መሠረታዊ ጥያቄወች የሚከተሉትን የመሳሰሉ ናቸው።
መሠረታዊ ግሳቦች (fundamental forces) ስንትና ምን ናቸው ?
ግሳብና ሑሰት የሚዛመዱት እንዴት ነው ?
ጉልበትን (energy) በተመለከተ ጉሲን (physics) ሊመልሳቸው የሚሞክራቸው መሠረታዊ ጥያቄወች የሚከተሉትን የመሳሰሉ ናቸው።
ጉልበት ምንድን ነው ?
ጉልበት በስንት መልኮች (forms) ይከሰታል?
ጉልበት ካንድ መልክ ወደ ሌላ መልክ የሚመይጠው (transform) ማለትም የሚለወጠው እንዴትና በምን ሕጎች መሠረት ነው?
ቁስን (matter) በተመለከተ ደግሞ ጉሲን (physics) ሊመልሳቸው የሚሞክራቸው መሠረታዊ ጥያቄወች የሚከተሉትን የመሳሰሉ ናቸው።
ቁስ (matter) በቀኒጥ (atom)፣ በፀምሪቅ (molecule) እና በመሳሰሉት የሚዋቀረው (structured) እንዴት ነው?
በቁስ (matter) እና በጉልበት (energy) መካክል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?
የጉሲን ሕጎች (Laws) እና ግንገናወች (Theories)
በጉሲን (physics) ውስጥ ለሚጠየቁ የሑሰት (motion) እና የግሳብ (force) መሠረታዊ ጥያቄወች መልሶች ናቸው ተብለው የሚቀርቡ ግንገናወች (theories) የሑሰት ግንገናወች (theories of motion) ይባላሉ።
ለምሳሌ ያህል እንግሊዛዊው ጉሲነኛ (physicist) አለቃ ይሳቅ ኒውተን (Sir Isaac Newton) ከሞላ ጎደል ለሁሉም ሠርካዊ አካሎችና የአካሎች ስርካቶች (everyday objects and systems of objects) የሚያገለግል የሑሰት ግንገና (theory of motion) ገንገኗል ።
ይህም የኒውተን የሑስት ግንገና አንደኛው የሑሰት ሕግ (first law of motion)፣ ሁለተኛው የሑሰት ሕግ (second law of motion) እና ሦስተኛው የሑሰት ሕግ (third law of motion) በሚባሉ ሦስት የሑሰት ሕጎች (three laws of motion) ላይ የተመሠረተ ግንገና (theory) ነው።
የጉሲን ዐብይ ዘርፎች (Main Branches of Physics)
ጉሲን (physics) ባራት ዐብይ ዘርፎች ወይም ቅርንጫፎች ይከፋፈላል። እነሱም የሚከተሉት ናቸው።
ብሉይ ጉሲን (classical physics) = የትልቅ (large) እና ቀሳን (slow) አካሎች ጉሲን (physics)
ኑርከን ጉሲን (quantum physics) = የትንሽ (small) አካሎች ጉሲን (physics)
ፀናራዊ ጉሲን (relativistic physics) = የፈጣን (fast) አካሎች ጉሲን (physics)
ፀናራዊ ኑርከን ጉሲን (relativistic quantum physics) = የትንሽ (small) እና ፈጣን (fast) አካሎች ጉሲን (physics)
ኑርከን (quantum) የሚለው ቃል የተገኘው ኑስ (ማለትም እኑስ) እና እርከን ከሚሉት ቃሎች ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ነረከነ (quantize)፣ ንርክን ( ንርኩን ) [quantized]፣ ነርካኒ ( ነርካኝ ) [quantizer]፣ ንርከና (quantization) እያለ ይሄዳል። ከዚህም የጉልበት ንርከና (energy quantization)፣ የጨረር ንርከና (quantization of radiation) የመሳሰሉትን ቃሎች እናገኛለን።
quantum = ኑርከን quantize = ነረከነ quantization = ንርከና quantization of energy = የጉልበት ንርከና quantum particle = ኑርከን (ኑርከናዊ) እኑስ
ፀናር (relative) የሚለው ቃል የተገኘው ለማርባት ይመች ዘንድ አንጻር ከሚለው ቃል ነው። ግሱም ሲረባ ፀነረ፣ ፅንር ( ፅኑር ) ፣ ፀናሪ፣ ፀነራ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም። ፀነረ ማለት አነፃፀረ ማለት ሲሆን፣ ፀናራዊ (relativistic) ማለት ደግሞ ንጽጽራዊ ማለት ነው። ፀናራዊነት (relativity) ማለት ደግሞ ንጽጽራዊነት ማለት ነው።
relative = ፀናር relativistic = ፀናራዊ relativity = ፀናራዊነት theory of relativity = የፀናራዊነት ግንገና relativistic particle = ፀናራዊ እኑስ
የመጀመርያው የጉሲን መስክ ብሉይ ጉሲን (classical physics) ነበር።
የጉሲን መስክ እየሰፋ ሲሄድ ግን ኑርከን ጉሲንን (quantum physics) ቀጥሎ ደግሞ ፀናራዊ ጉሲንን (relativistic physics)፣ በመጨረሻ ደግሞ ፀናራዊ ኑርከን ጉሲንን (relativistic quantum physics) የሚያካትት ሆነ።
በዚህም ምክኒያት ከብሉይ ጉሲን በኋላ የተከፈቱት ሦስቱ ዳህራዊ (ማለትም ኋለኛ) የጉሲን መስኮች (ማለትም ኑርከን ጉሲን፣ ፀናራዊ ጉሲን፣ እና ፀናራዊ ኑርከን ጉሲን) ባጠቃላይ አጠራር ሐዲስ ጉሲን ወይም ዘመናዊ ጉሲን (modern physics) ይባላሉ።
በሌላ አባባል መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተ ብሉይ ኪዳን (Old Testament) [ማለትም ያረጀው፣ ያፈጀው ኪዳን] እና ሐዲስ ኪዳን (New Testament) [ማለትም ዐዲሱ ኪዳን] እንዲሉ፣ ጉሲንን በተመለከተ ደግሞ ብሉይ ጉሲን (classical physics) [ያረጀው፣ ያፈጀው ጉሲን] እና ሐዲስ ጉሲን (modern physics) [ማለትም ዐዲሱ ጉሲን] እንላለን።
ብያኔ (definition)፡ ወርከፋቸው (size) ከቀኒጥ ወርከፍ (size of atom) የሚያንስ ወይም በቀኒጥ ወርከፍ ደረጃ የሆነ ትንሽ (small) አካሎች (bodies) እና የአካሎች ስርካቶች (systems of bodies) የሚጠኑበት የጉሲን ዘርፍ (domain of physics)፣ ኑርከን ዘርፍ (quantum domain) ወይም ኑርከን ጉሲን (quantum physics)፣ ወይም ኑርከን ሐምሲን (quantum mechanics) ይባላል።
ብያኔ (definition)፡ ፍጥነታቸው (speed) ከብርሃን ፍጥነት 10% በላይ የሆነ ፈጣን (fast) አካሎች (bodies) እና የአካሎች ስርካቶች (systems of bodies) የሚጠኑበት የጉሲን ዘርፍ (domain of physics)፣ ፀናራዊ ዘርፍ (relativistic domain) ወይም ፀናራዊ ጉሲ ን (relativistic physics) ወይም ፀናራዊ ሐምሲን (relativistic mechanics) ይባላል።
ብያኔ (definition)፡ ወርከፋቸው (size) ከቀኒጥ ወርከ ፍ (size of atom) የሚያንስ ወይም በቀኒጥ ወርከፍ ደረጃ የሆነ ኑርከናዊ እኑሶች (quantum particles)፣ ፍጥነታቸው (speed) ደግሞ ከብርሃን ፍጥነት 10% በላይ የሆነ ፀናራዊ እኑሶች (relativistic particles) የሚጠኑበት ኑርከን ጉሲንን (quantum physics) እና ፀናራዊ ጉሲንን (relativistic physics) የሚያጣምር የጉሲን ዘርፍ (domain of physics) ፀናራዊ ኑርከን ጉሲን (relativistic quantum physics) ይባላል።
ብያኔ (definition)፡ ወርከፋቸው (size) ከቀኒጥ ወርከ ፍ (size of atom) አንጻር ጃምንት (huge) የሆነ፣ ፍጥነታቸ ው (speed) ደግሞ ከብርሃን ፍጥነት አንጻር ኢምንት የሆነ አካሎች (bodies) እና የአካሎች ስርካቶች (systems of objects) የሚጠኑበት የጉሲን ዘርፍ (domain of physics)፣ ብሉይ ዘርፍ (classical domain) ወይም ብሉይ ጉሲን (classical physics) ወይም ብሉይ ሐምሲን (classical mechanics) ይባላል።
classical physics (classical mechanics) = ብሉይ ጉሲን (ብሉይ ሐምሲን) modern physics = ዘመናዊ ጉሲን፣ ሐዲስ ጉሲን quantum physics (quantum mechanics) = ኑርከን ጉሲን (ኑርከን ሐምሲን) relativistic physics (relativistic mechanics) = ፀናራዊ ጉሲን (ፀናራዊ ሐምሲን) relativistic quantum physics (relativistic quantum mechanics) = ፀናራዊ ኑርከን ጉሲን (ፀናራዊ ኑርከን ሐምሲን)
የጉሲን ዐብይ ዘርፎች ዐብይ ጉሲነኞች (Physicists)
በብሉይ ጉሲን (classical physics) ውስጥ ዐብዩ ጉሲነኛ (physicist) እንግሊዛዊው ይስሃቅ ኒውተን (Isaac Newton) ነው።
በኑርክን ጉሲን (quantum physics) ውስጥ በርካታ ዐብይ ጉሲንኞች (physicists) ሲኖሩ፣ ከነሱም ውስጥ አንዱ ጀርመናዊው ማክስ ጣውላ (Max Plank) ነው።
በፀናራዊ ጉሲን (relativistic) ውስጥ ዐብዩ ጉሲነኛ (physicist) ጀርመናዊው አልበርት አንዲንጋ (Albert Einstein) ነው። አንዲንጋ (Einstein) የሚለው ቃል የተገኘው አንድ ዲንጋ ከሚለው ነው፣ Einstein ማለት በጀርመንኛ አንድ ዲንጋ ማለት ነውና።
በፀናራዊ ኑርከን ጉሲን (relativistic quantum physics) ውስጥ ዐብዩ ጉሲነኛ (physicist) እንግሊዛዊው ጳውሎስ ዲራክ (Paul Dirac) ነው።
መስፍን አረጋ mesfinamharic.com mesfin.arega@gmail.com