“When you can measure what you are speaking about and express it in numbers, you know something about it. When you cannot measure it and express it in numbers your knowledge is unsatisfactory. It may be the beginning of knowledge but your thoughts have not advanced to stage of science.” (Lord Kelvin )
“ ስለምታወሳው ነገር በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሰገላዊ እውቀት ( scientific knowledge ) አለህ የሚባለው ነገሩን መቆነን (measure) እና በቁጥር መግለጽ ከቻልክ ብቻ ነው። አለያ እውቀትህ ሰገላዊ እውቀት ሊባል አይችልም፣ የሰገላዊ እውቀት ጅማሮ ሊሆን ቢችልም። ” ( አለቃ ካልቪን )
ማሳሰቢያ
ይህ ጦማር (ማለትም ክፍል 3 ) ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው በሚቀድሙት ጦማሮች (ማለትም ከፍሎች 1 እና 2 ) ላይ ስለሆነ፣ ይህን ክፍል ከማንበብወ በፊት ክፍሎችን 1 እና 2 ቢያንስ ቢያንስ በገረፍታ ይመልከቱ።
ስርካት (System)
ስርአት የሚለውን ቃል ለማርባት ይመች ዘንድ በትንሹ በመለወጥ ስርካት (system) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
የስርካት (system) ግስ ሲረባ ሰረከተ (systematize)፣ ስርክት (ስርኩት) (systematized)፣ ሰርካች (systematizer)፣ ስርከታ (systematization)፣ ስርክተት ፣ ስርካቴ ፣ ስርካቶሽ እያለ ይሄዳል።
ሰረከተ ማለት ስርካት መሠረተ እንደ ማለት ሲሆን፣ ስርክት (ስርኩት) ማለት ደግሞ የተሰረከተ ማለት ነው።
system (systematic) = ስርካት፣ ስርካታዊ systematize = ሰረከተ systematization = ስርከታ፣ አሰረካከት
ቁነና (Measurement)
ባማረኛ ቆነነ ማለት ለካ፣ መጠነ፣ ሰፈረ ማለት ነው፣ በተለይም ደግሞ ድርጎን ወይም ዳረጎትን (commision)፣ ማለትም በየጊዘው የሚደረግን ክፍያ። ይህም ቃል measure የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
የቆነነ (measure) ግስ ሲረባ ሲረባ ቆነነ (measure)፣ ቁንን (measured)፣ ቆናኒ ( ቆናኝ ) [measuring]፣ ቁነና (measuring, measurement)፣ ቁንነት ፣ ቁናኔ ፣ ቁናኖሽ እያለ ይሄዳል።
measure = ቆነነ measurement = ቁነና measurement system = ቁነና ስርካት measurable (measurability) = ተቆናኝ፣ ተቆናኝነት
ናይባ (quantitiy) እና ጫልባ (quality)
ባይና (ማለትም ብዛት) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ናይባ (quantity) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ጫላ (ምርጥ፣ የተሻለ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ደግሞ ጫልባ (quality) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ናይባ (quantity) ማለት ብዛት፣ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ነየበ (quantify)፣ ንይብ ( ንዩብ ) [quantified]፣ ነያቢ (quantifier)፣ ንየባ (quantifying, quantification)፣ ንይበት ፣ ንያቤ ፣ ንያቦሽ እያለ ይሄዳል።
ጫልባ (quality) ማለት ጥራት ማለት እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ጨለበ ፣ ጭልብ ( ጭሉብ ) ፣ ጨላቢ ፣ ጭለባ ፣ ጭልበት ፣ ጭላቤ ፣ ጭላቦሽ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
quantity = ናይባ quantify = ነየበ measurable quantity = ተቆናኝ ናይባ quality = ጫልባ quality (verb) = ጨለበ
ግኡዝ ናይባ (Physical Quantity)
ያለ ምንም አሻሚነት (ambiguty) ሊቆነን (measured) የሚችል ናይባ (quantity)፣ ማለትም ማናቸውም ሰው በማናቸውም መንገድ ቢቆንነው እሴቱ (value) ከሞላ ጎደል ያውቴ (same) የሆነ ማናቸውም ናይባ (quantity) በልዩ ስም ግኡዝ ናይባ (physical quantity) ይባላል።
በሌላ አባባል ግኡዝ ናይባ (physical quantity) ማለት በግኡዝ መንገድ የሚቆነን ተቆናኝ ናይባ (measureable quantity) ማለት ነው።
ለምሳሌ ያህል ርዝመት (length)፣ ስፋት (area)፣ ጽሐር (volume)፣ ፍልሰት (displacement)፣ ፍጥነት ( speed)፣ ሙቀት (temperature)፣ ግሳብ (force)፣ ጉልበት (energy) እና ኃይል (power) ግኡዝ ናይባወች (physical quantities) ናቸው።
ቶካድ (Unit )
ቶካድ (unit) ማለት መቆነኛ (ማለትም መለኪያ ወይም መስፈሪያ) ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ቶኮ (አንድ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል እና አሃድ (አንድ) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው። ለምሳሌ ያህል
ሜትር (meter)፣ ሃድጃኖሜትር (kilometer) እና ሃድጢኖሜትር (millimeter) የርዝመት ቶካዶች (units of length) ናቸው።
ደቂቃ (minute)፣ ኑሲቃ (second) እና ሃድጢኖኑሲቃ (millisecond) የጊዜ ቶካዶች (units of time) ናችው።
ግራም (gram)፣ ሃድጃኖግራም (kilogram) እና ሃድጢኖግራም (milligram) የቁሰት ቶካዶች (units of mass) ናቸው።
unit = ቶካድ unit of measurement = የቆነና ቶካድ
ደርክ (Standard)
ደረጃ ከሚለው ደርክ (standard) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ደርክ (standard) ማለት ለመቆነን (measure) የሚያገለገል ቶካድ (unit) ወይም ማነጻጸርያ (comparison) ወይም ደረጃ መመደቢያ ማለት ነው።
ግሱም ሲረባ ደረከ (standardize)፣ ድርክ ( ድሩክ ) [standardized]፣ ደራኪ (standardizing)፣ ድረካ (standardization)፣ ድራኬ ፣ ድራኮሽ እያለ ይሄዳል።
ደረከ (standardized) ማለት ደርክ መሠረተ ማለት ሲሆን፣ ድርክ ( ድሩክ ) [standardized] ማለት ደግሞ የተደረከ ማለት ነው።
standard = ደርክ standardize = ደረከ standardization = ድረካ standardized = ደርክ፣ ድርክ፣ ድሩክ standard deviation = ደርክ ፍንገጣ standard of length = የርዝመት ደርክ standard of mass = የቁሰት ደርክ standard of time = የጊዜ ደርክ standard unit = ደርክ ቶካድ standardized test = ደርክ ፈተና standard of living = የኑሮ ደርክ
ሲማክ ቶካድ (Basic Unit)
ሲማክ (base) ማለት መሠረት እንደ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ሰመከ ( ማለትም ተጠጋ፣ ተደገፈ፣ ጥግ ያዘ፣ ድጋፍ ያዘ) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው።
ሲማክ (base) ከሚለው ሲማክ ቶካድ ( basic unit ) የሚለውን ስያሜ እናገኛለን። ሲማክ ቶካድ (basic unit) ማለት መሠረታዊ ቶካድ እንደ ማለት ነው።
base = ሲማክ basic = ሲማክ፣ ሲማካዊ basic unit = ሲማክ ቶካድ፣ ሲማካዊ ቶካድ
ርችግ ቶካድ (Derived Unit)
አርገቹ (ማግኘት) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ረቸገ (derive) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ግሱም ሲረባ ረቸ ገ (derive)፣ ርችግ ( ርቹግ ) [derived]፣ ረቻጊ (deriving)፣ ርቸጋ (derivaiton)፣ ርቻጌ ፣ ርቻጎሽ እያለ ይሄዳል።
ረቸገ (derive) ማለት አገኘ እንደ ማለት ሲሆን፣ ርችግ ( ርቹግ ) [derived] ማለት ደግሞ የተረቸገ (ማለትም የተገኘ) ማለት ነው።
ርችግ ቶካድ (derived unit) ማለት ከሲማክ ቶካድ (basic unit) የተረቸገ (derived) ማለትም የተገኘ ግኝ ቶካድ ማለት ነው።
derive = ረቸገ derivation = ርቸጋ derived = ርችግ፣ ርቹግ፣ ርቻግ derived unit = ርችግ ቶካድ
ሲማክ ናይባወች (Basic Quantities) እና ርችግ ናይባወች (Derived Quantities
ግኡዝ ናይባወች (physical quantities) ሲማክ ናይባወች (basic quantities) እና ርችግ ናይባወች (derived quantities) ተብለው በሁለት ዐብይ ክፍሎች ይከፈላሉ።
ሲማክ ናይባ (basic quantity) ማለት መሠረታዊ ናይባ (fundamental quantity) እንዲሆን የተመረጠ (chosen) ናይባ (quantity) ማለት ነው።
ርችግ ናይባ (quantity) ማለት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሲማክ ናይባወች ን (basic quantities) በማገጣጠም የሚረቸግ (derived) ማለትም የሚገኘ መሠረታዊ ናይባ (fundamental quantity) እንዲሆን ያልተመረጠ ናይባ (quantity) ማለት ነው።
ለምሳሌ ያህል ርዝመት (length) እንደ ሲማክ ናይባ (basic quantitiy) ቢመረጥ ስፋት (area) ከርዝመት (length) የሚረቸግ ርችግ ናይባ (derived quantity) ይሆናል፣ ምክኒያቱም ስፋት (area) ማለት ርዝመትን በሌላ ርዝመት (ማለትም ወርድ) መበዘር (multiply) ማለት ነውና።
በተመሳሳይ መንገድ ጽሐርም (volume) ርችግ ናይባ (derived quantity) ይሆናል፣ ምክኒያትም ጽሐር (volume) ማለት ርዝመትን፣ በሌላ ርዝመት (ማለትም ወርድ) እና በሌላ ርዝመት (ማለትም ከፍታ) መበዘር (multiply) ማለት ነውና።
ሲማክ ቶካዶች (Basic Units) እና ርችግ ቶካዶች (Derived Units)
ሲማክ ናይባወች (basic quantities) የሚቆነኑባቸው (measured) መሠረታዊ ቶካዶች (fundamental units) ሲማክ ቶካዶች (basic units) ይባላሉ።
ርችግ ናይባወች (derived quantities) የሚቆነኑባቸው (measured) ከሲማክ ቶካዶች (basic units) የሚረቸጉ (derived) ማለትም የሚገኙ ቶካዶች (units) ደግሞ ርችግ ቶካዶች (basic units) ይባላሉ።
ለምሳሌ ያህል የርዝመት ቶካድ (unit of length) ሜትር (meter) እና የጊዜ ቶካድ (unit of time) ኑሲቃ (second) እንደ ሲማክ ቶካዶች (basic units) ቢመረጡ፣ የስፋት ቶካድ (unit of area) ሜትር ካልቶና (meter squared)፣ የጽሐር ቶካድ (unit of volume) ሜትር ሳልቶና (meter cubed)፣ የፍጥነት ቶካድ (unit of speed) ሜትር በኑሲቃ (meter per second) እንዲሁም የጥድፈት ቶካድ (unit of acceleration) ሜትር በኑሲቃ ካልቶና (meter per second squared) ርችግ ቶካዶች (derived units) ይሆናሉ።
ገመር ስብስብ (Complete Set )
በግእዝ ገመረ ማለት ፈጸመ፣ ጨረሰ፣ አጠናቀቀ እንደ ማለት ነው። ይህም ቃል complete (complement) የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
ግሱም ሲረባ ገመረ (to complete, to complement)፣ ግምር ( ግሙር ) [completed, complemented]፣ ገማሪ (completing, complementing)፣ ግመራ (completing, complementing)፣ ግምረት፣ ግማሬ፣ ግማሮሽ እያለ ይሄዳል።
ገመር (complete) ከሚለው ገመር ስብስብ (complete set) የሚለውን እናገኛለን። ባንድ ማእቀፍ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ነገሮች በዚህ ማእቀፍ ውስጥ በሚገኙ ጥቂት ነግሮች አንጻር ሊገለጹ የሚችሉ ከሆነ፣ የነዚህ ጥቂት ነገሮች ስብስብ (set) ለማዕቀፉ ገመር ስብስብ (complete set) ነው ይባላል።
ለምሳሌ ያህል በሦስት ስፍረታዊ ህዋ (three dimensional space) ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም ፍላስተ ን (vector) በቶካድ ፍላስተኖች (unit vectors) i ^ , j ^ , k ^ \hat{i}, \hat{j}, \hat{k} አንጻር በመልክ V → = V x i ^ + V y j ^ + V z k ^ \vec{V} = V_x\hat{i} + V_y\hat{j} + V_z\hat{k} ሊገለጽ ይችላል። በዚህም ምክኒያት የሦስቱ ቶካድ ፍላስተኖቹ ስብስብ (set) ማለትም { i ^ , j ^ , k ^ } \{\hat{i}, \hat{j}, \hat{k}\} በሦስት ስፍረታዊ ህዋ ውስጥ ለሚገኙ ለሁሉም ፍላስተኖች ገመር ስብስብ (complete set) ነው ይባላል።
complete (complement) = ገመር complete (complement) [verb] = ገመረ complemental (complementary) = ገመራዊ፣ ገማሪ complementary angles = ገማሪ ዘዌወች፣ ረናጊ ዘዌወች complementary colors = ገማሪ ቀለሞች complementary sets (complete sets) = ገማሪ ስብስቦች complementarity (completeness) = ገማሪነት፣ ገመራዊነት complementarity principle = ገመራዊነት መርሕ complete basis = ገመር ሲማኮች completing the square = ካልቶና ግመራ
ጀገር (Supplement) እና ጀጋሪ (Supplementary)
ገርገራ (ማለትም እርዳታ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ጀገር (supplement, supplementary) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ጀገር (supplement, supplementary) ማለት ተጨማሪ፣ አሟይ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ጀገረ (to supplement)፣ ጅግር (ጅጉር) [supplemented]፣ ጀጋሪ (supplementing, supplementation)፣ ጅገራ፣ ጅግረት፣ ጅጋሬ፣ ጅጋሮሽ እያለ ይሄዳል።
ጀገረ (to supplement) ማለት ተጨማሪ አቀረበ፣ አሟላ እንደ ማለት ሲሆን፣ ጅግር ( ጅጉር ) [supplemented] ማለት ደግሞ የተጀገረ ማለት ነው።
supplement = ጀገር supplement (verb) = ጀገረ supplementary = ጀገር፣ ጀጋሪ፣ ጀገራዊ supplementary angles = ጀጋሪ ዘዌወች፣ ቀጣጊ ዘዌወች supplementary quantities = ጀጋሪ ናይባወች supplementary units = ጀጋሪ ቶካዶች
ምልክት (Sign) እና ወመል (Symbol)
ምልክት (sign) ማለት ለማመልከት የሚያገለግል ማለት ነው፣ የእኩልነት ምልክት (equality sign)፣ የመደመር ምልክት (addition sign)፣ የመቀነስ ምልክት (subtraction sign) እንዲሉ።
ወካይ ምልክት ከሚለው ሐረግ ወመል (symbol) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ወመል (symbol) ከምልክት (sign) ጋር ተመሳሳይነት ያለውና አብዛኛውን ጊዜ የሚተካካ (interchangeable) ቃል ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ወመለ (symbolize)፣ ውምል (symbolized)፣ ወማሊ (ወማይ) [symbolizer]፣ ውመላ (symbolization) እያለ ይሄዳል።
ወመለ (symbolize) ማለት ወመል (symbol) ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ውምል (symbolized) ማለት ደግሞ የተወመለ ማለትም ወመል (symbol) የተደረገ ማለት ነው።
sign = ምልክት symbol = ወመል symbolize = ወመለ symbolization = ውመላ
የቁነና ስርካቶች አሰረካከት (Construction of Measurement Systems)
ማናቸውም የቁነና ስርካት (measurement system) የሚሰረከተው ማለትም የሚዋቀረው በሚከተለው ደተር (procedure) መሠረት ነው። ደተር (procedure) ማለት ቅደምተከተል ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ደረጃ እና ተራ ከሚሉት ነው። ግሱም ሲረባ ደተረ፣ ድትር ( ድቱር ) ፣ ደታሪ፣ ድተራ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
ጥቂት ናይባወች እንደ ሲማክ ናይባወች (basic quantities) ይመረጡና የነዚህ ሲማክ ናይባወች ሲማክ ቶካዶች (basic units) ይበየናሉ (defined)።
የቀሩት ሁሉም ናይባወችና ቶካዶቻቸው በነዚህ ሲማክ ናይባወች እና ሲማክ ቶካዶች አንጻር የሚገለጹ ርችግ ናይባወች (derived quantities) እና ርችግ ቶካዶች (derived) ይሆናሉ።
የሲማክ ናይባወች ቁጥር (number of basic quantities) ሁሉንም ናይባወች በነሱ አንጻር ለመገለጽ የሚያስችለው ጨቅሊስ ቁጥር (minimum number) መሆን አለበት።
ለምሳሌ ያህል በሐምሲን (mechanics) ውስጥ የሚገኙትን ሁሉንም ሐምሲናዊ ናይባወች (all mechanical quantities) ለመግለጽ ሦስት ሐምሲናዊ ናይባወችን (three mechanical quantities) ብቻ እንደ ሲማክ ናይባወች (basic quantities) መምረጥ በቂ ነው።
እነዚህም ሦስት ሲማክ ናይባወች (three basic quantities) የቀሩትን ሁሉንም የሐምሲን ናይባወች በነሱ አንጻር ለመግለጽ ስለሚያስችሉ ገመር ሲማኮች (complete basis) ናቸው ወይም ገመር ስብስብ (complete set) ይመሠርታሉ ይባላሉ።
ሁለቱ ዐብይ የቶካድ ስርካቶች
በዘመናች ላይ በሰፊው ግልጋሎት ላይ እየዋሉ ያሉት የቶካድ ስርካቶች (Systems of Units) ሁለት ሲሆኑ እነሱም የሚከተሉት ናቸው።
አንደኛው የቶካድ ስርካት የብሪቲሽ የቶካዶች ስርካት (British System of Units) ወይም የብሪቲሽ አፄኛ የቶካዶች ስርካት (British Imperial System of Units) ወይም ባጭሩ አፄኛ የቶካዶች ስርካት (Imperial System of Units) የሚባለው ነው።
ሁለተኛው የቶካዶች ስርካት ደግሞ ቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት (International System of Units) ወይም ባጭሩ ቤቶስ (SI) የሚባለው ነው። ይህም ስርካት በንግሊዘኛ SI የተባለበት ምክኒያት System International d’Unites የሚለውን የፈረንሳይኛውን ስያሜ በመከተል ነው።
ቤንቤራዊ (international) ማለት ዓለማቀፋዊ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ቤን ( inter) ከሚለው ፊልጡፍ (prefix) እና ብሔራዊ (national) ከሚለው ቃል ነው። ቤን (inter) የሚለው ፊልጡፍ (prefix) የተገኘው ደግሞ በይነ (መካከል) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው።
የብሪቲሽ የቶካዶች ስርካት (British System of Units) በሰፊው ግልጋሎት ላይ እየዋለ ያለው በራሷ በብሪታይ እና የጋራ ብልፅግና አገሮች (Common Wealth of Nations) በሚባሉት ጋናን (Ghana) እና ኬንያን (Kenya) በመሳሰሉት የቀድሞ የንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች ነው። በተለይም ደግሞ ይህን ኋላቀር የቶካዶች ስርካት በስፋት በመጠቀም እንዳይሞት እየታደገው ያለው በንግሊዝ አፄጌ (British Empire) እግር የተተካው ያሜሪቃን አፄጌ (American Empire) ነው። ስለዚህም እየሞተ ያለው ያሜሪቃ አፄጌ በቅርቡ ሲሞት፣ ይህም የቶካዶች ስርካት አብሮት እንደሚሞት ሳይታለም የተፈታ ነው።
የብሪቲሽ የቶካዶች ስርካት (British System of Units) በተለይም ደግሞ ለሰገል (science) እና ለምንደሳ ( engineering) አመቺ ያልሆነ ኋላቀር ስርካት ነው። ምክኒያቱ ደግሞ በቶካዶቹ መካከል ያለው ዝምድና የዘፈቀደ (random) በሚመስሉ ቁጥሮች (3, 5, 12) ማባዛትን የሚያካትት ስርካትን ያለተከተለ ስለሆነ በቀላሉ ለማስታወስና ለመጠቀም የሚያቸግር መሆኑ ነው። ለምሳሌ ያህል
አንድ ጫማ (foot) አስራ ሁለት ኢንች (inch) ማለትም (1ft = 12 in) ነው።
አንድ ያርድ (yard) ሦስት ጫማ (feet) ማለትም (1yd = 3ft) ነው።
አንድ ማይል (mile) አንድ ሺ ሰባት መቶ ስልሳ ያርድ (1 mi = 1760 yd) ወይም አምስት ሺ ሁለት መቶ ሰማንያ ጫማ (1 mi = 5280ft) ነው።
በተቃራኒ ደግሞ በቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት (International System of Units) ላይ ትላልቅና ትናንሽ ቶካዶች የሚበየኑት (defined) ያስርን ርቢ (power of ten) በመጠቀም ስለሆነ፣ ቶካዶቹን ለማስታወስና ለመጠቀም፣ በተጨማሪ ደግሞ ካንድ ቶካድ ወደ ሌላ ቶካድ ለመለወጥ በጣም ቀላል ነው። በዚህም ምክኒያት ባሁኑ ጊዜ ሰገለኛወች (scientists) እና መንዳሾች (engineers) ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ የሚጠቀሙት ይህን የቶካድ ስርካት ነው ማለት ይቻላል።
የብሪቲሽ የቶካዶች ስርካት ([British System of Units)
በብሪቲሽ የቶካዶች ስርካት ( British System of Units) ወይም ባጭሩ ብቶስ ላይ
ሐምሲናዊ ቁነናን (measurements in mechanics) በተመለከተ ሲማክ ናይባወች (basic quantities) እንዲሆኑ የተመረጡት ርዝመት (length)፣ ግሳብ (force) እና ጊዜ (time) ናቸው።
ለነዚህ ሲማክ ናይባወች (basic quantities) ሲማክ ቶካዶች (basic units) እንዲሁኑ የተበየኑት (defined) ደግሞ ጫማ (foot)፣ ፓውንድ (pound) እና ኑሲቃ (second) ናችው።
በዚህም ምክኒያት የብሪቲሽ የቶካዶች ስርካት አብዛኛውን ጊዜ ጫማ – ፓውንድ – ኑሲቃ ስርካት (foot-pound-second system) ወይም ባጭሩ ጫፓኑ ስርካት (fps system) በመባል ይታወቃል።
ለምሳሌ ያህል በብሪቲሽ የቶካዶች ስርካት (British System of Units) ላይ ቁሰት (mass) ርችግ ናይባ (derived quantity) ሲሆን፣ ርችድ ቶካዱ (derived unit) ደግሞ ፓውንድ ኑሲቃ ካልቶና በጫማ (pound second squared per foot) ነው። ይህም የቁሰት ቶካድ (unit of mass) በልዩ ስም ስለግ (slug) ይባላል። በብርቲሽ የቶካዶች ስርካት ላይ የቁሰት ቶካድ (unit of mass) ስለግ (slug) መሆኑን የሚያውቁት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው።
በሌላ በኩል ግን በቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት (International System of Units) ላይ ቁሰት (mass) ሲማክ ናይባ (basic quantity) ሲሆን፣ ሲማክ ቶካዱ (basic unit) ደግሞ ሃጃኖግራም (kilogram) ነው። አንድ ስለግ (slug) በቅርበዛ (approximately) 14.6 ሃጃኖግራም (kilogram) ነው።
ቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት (International System of Units)
በቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት ( Internatioal System of Units) ወይም ባጭሩ ቤቶስ (SI) ላይ
ሐምሲናዊ ቁነናን (measurements in mechanics) በተመለከተ ሲማክ ናይባወች (basic quantities) እንዲሆኑ የተመረጡት ርዝመት (length)፣ ቁሰት (mass) እና ጊዜ (time) ናቸው።
ለነዚህ ሲማክ ናይባወች (basic quantities) ሲማክ ቶካዶች (basic units) እንዲሁኑ የተበየኑት (defined) ደግሞ ሜትር (meter)፣ ሃጃኖግራም (kilogram) እና ኑሲቃ (second) ናችው።
በዚህም ምክኒያት ቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት አብዛኛውን ጊዜ ሜትር – ሃጃኖግራም – ኑሲቃ ስርካት (meter-kilogram-second system) ወይም ባጭሩ ሜሃኑ ስርካት (mks system) በመባል ይታወቃል።
ባጠቃላይ አነጋገር ደግሞ ቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት (International System of Units) ሁሉንም ግኡዝ ናይባወች (all physical quantities) ለመቆነን (measure) የሚያገለገሉ ሰባት ሲማክ ናይባወች (seven basic quantities) እና ሁለት ጀጋሪ ናይባወች (two supplementary quantities) ማለትም አሟይ ናይባወች አሉት።
ቶታን (substance) ማለት የራሱ መለያ ባሕሪ ያለው ወሃን፣ ወርቅን፣ መዳብን የመሰለ ልዩ ቁስ (matter) እንደ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ወቶንታ (ማለትም እቃ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው።
ቶታን (sustance) የሚለውን ቃል ኤጅ (-age) ከሚለው ኋልጡፍ (suffix) ጋር በማጣመር ቶታኔጅ (amount of substance) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ቶታኔጅ ማለት የቶታን መጠን እንደ ማለት ነው፣ አምፐሬጅ (amperage) ሲሉ፣ የአምፔር መጠን (amount of ampere) ማለት እንደሆነ።
ባማረኛ ጀማ (ወይም ዠማ) ማለት ወንዝ፣ ጅረት ማለት ነው። ይህም ቃል current የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል። ከዚህም ሌትሪክ ጀማ (electric current) የሚለውን ስያሜ እናገኛለን።
ቀዛል (intensity) ማለት ብርቱነት፣ ጥንካሬ፣ ጉልበት እንደ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ አዛል (ብርታት፣ ጥንካሬ) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው። ግሱም ሲረባ ቀዘለ (intensify)፣ ቅዝል (ቅዙል) [intensified]፣ ቀዛሊ (ቀዛይ) [intensifying]፣ ቅዘላ (intensification)፣ ቅዛሌ፣ ቅዛሎሽ እያለ ይሄዳል።
የብርሃን ቀዛል (intensity of light) ማለት የብርሃን ብርቱነት እንደ ማለት ነው።
ጃራ (radian) የሚለው ቃል የተገኘው ዲራራ (የተዘረጋ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ሲሆን፣ ካልጃራ (steradian) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ ካልቶና (square) እና ጃራ (radian) ከሚሉት ቃሎች ነው።
substance = ቶታን amount of substance = ቶታኔጅ current = ጀማ electric current = ሌትሪክ ጀማ intensity = ቀዛል intensity of light = የብርሃን ቀዛል intensify = ቀዘለ radian = ጃራ steradian = ካልጃራ
የቤቶስ ፊልጡፎች (SI Prefixes)
ፊልጡፍ (prefix) ማለት ከቃል ፊትጌ የሚለጠፍ ማለት ሲሆን፣ ባዕድ መነሻ የምንለው ነው። ለምሳሌ ያህል ኢሰብአዊ ላይ ፊደል ኢ ፊልጡፍ ነው።
ቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካትን (ቤቶስን) [International System of Units] ተማራጭ የቶካዶች ስርካት (System of Units) ያደረገው ዋናው ባሕሪው ያስር ርቢወችን (powers of ten) እንደ ፊልጡ ፍ (prefix) በመጠቀም የማናቸውንም ቶካድ (unit) መጠን በተፈለገው ደረጃ ማተለቅ (increase) ወይም ማሳነስ (decrease) መቻሉ ነው።
እነዚህም ያስር ርቢወችን (powers of ten) የሚገልጹ ፊልጡፎ ች (prefixes) የቤቶስ ፊልጡፎች (SI prefixes) ይባላሉ።
ባማረኛ የቤቶስ ፊልጡፎች (SI prefixes) በራሳቸው የቁጥሮች ስያሜወች ናቸው። በንግሊዘኛ ግን የቤቶስ ፊልጡፎች እንደ ቁጥር ሲያገለግሉና እንደ ፊልጡፍ ሲያገለግሉ የተለያዩ ስሞች አሏቸው።
ለምሳሌ ያህል 1, 000, 000 = 106 እንደ ቁጥር ሲሆን በንግሊዘኛ million ይባላል፣ እንደ ቤቶስ ፊልጡፍ (SI prefix) ሲሆን ደግሞ Mega ይባላል። ባማረኛ ግን 1, 000, 000 = 106 እንደ ቁጥርም እንደ ቤቶስ ፊልጡፍም ሲሆን የሚባለው ካልጃኖ ነው።
እነዚህ የቁጥር ስያሜወች የተገኙት አሃዱ፣ ክልኤቱ፣ ሰለስቱ፣ አርባዕቱ፣ ኀምስቱ፣ ስድስቱ፣ ሰባዐቱ፣ ስምንቱ፣ ተስዐቱ፣ ዐሥርቱ ከሚሉት የግእዝ ቁጥሮችና ጃኖ (ትልቅ) ከሚለው ያማረኛ ቃል፣ እንዲሁም ጢኖ (ትንሽ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው።
የንግሊዘኛወቹ የቤቶስ ፊልጡፎች (SI prefixes) አሰያየም ስርካትን (ስርዓትን) ያለተከተለ፣ የዘፈቀደ የሚመስል ስለሆነ በቃል ለማጥናት በጣም አስቸጋሪ ናቸው። አስተማሪ በመሆኔ ይህን የተማሪወች ችግር አውቀዋለሁ፣ እረዳዋለሁም። ስለዚህም፣ በንግሊዘኛ ተናጋሪወች ዘንድ በሰፊው የሚታወቁት የቤቶስ ፊልጡፎች (SI prefixes) በጣም ጥቂቶቹ፣ ምናልባትም ሃጅኖ (kilo) እና ካልጅኖ (mega) ብቻ ናቸው።
ያማረኛ ስያሜወቻቸውን ግን የግእዝ ን ቁጥ ሮች አካሄድ እንዲከተሉ ስላደረኳቸው በቀላሉ ሊታወሱ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል ሃጅኖ (kilo) የሚለው ፊልጡፍ (prefix) የተገኘው፣ አሃድ እና ጃኖ የሚሉትን ቃሎች በማጣመር ሲሆን፣ ሃጢኖ (milli) የሚለው ፊልጡፍ የተገኘው ደግሞ አሃድ እና ጢኖ የሚሉትን ቃሎች በማጣመር ነው።
ኦሳ (deca, deka) እና ኦሲ (deci) የሚሉት ፊልጡፎች የተገኙት፣ አስር ከሚለው ቃል ሲሆን፣ ቶሳ (hecto) እና ቶሲ (centi) የሚሉት ፊልጡፎች የተገኙት ደግሞ መቶ ከሚለው ያማረኛ ቃል ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ የቁጥሮች ስያሜወች የሚለውን ጦማር ይመልከቱ።
ገያጊ (computer) የሚለው ቃል የተገኘው ጉግያ (የራስ ቅል) ከሚለው የወላይትኛ ቃል ሲሆን፣ ሸምዱላ (memory) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ ሸመደደ ከሚለው ቃል ነው።
የገያጊ (computer) ግስ ሲረባ ገየ ገ (compute)፣ ግይግ ( ግዩግ ) [computed]፣ ገያጊ (computing, computer)፣ ግየጋ (computation)፣ ግይገት ፣ ግያጌ፣ ግያጎሽ እያለ ይሄዳል። ገየገ (compute) ማለት አሰላ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግይግ ( ግዩግ ) [compute] ማለት ደግሞ የተገየገ ማለት ነው።
ገያጊ (computer) ከሚለው ቃል ገየገዘ (computerize) የሚለውን ተጨማሪ ግስ እናገኛለን። ግሱም ሲረባ ገየገዘ (computerize)፣ ግይግዝ ( ግይጉዝ ) [computerized]፣ ገይጋዚ ( ገይጋዥ ) [computerizing]፣ ግይገዛ (computerization)፣ ግይግዘት፣ ግይጋዜ፣ ግይጋዞሽ እያለ ይሄዳል። ገየገዘ (computerize) ማለት ገያጊ ተጠቀመ፣ በገያጊ ሠራ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግይግዝ ( ግይጉዝ ) [comuterized] ማለት ደግሞ የተገየገዘ ማለት ነው።
calculate = አሰላ calculator = አስሊ compute = ገየገ computer = ገያጊ computation = ግየጋ computerize = ገየገዘ computerization = ግይገዛ
የቤቶስ ፊልጡፎች አጠቃቀም ደንቦች (Rules for SI Prefixes)
የቤቶስ ፊልጡፎችን (SI Prefixes) አጠቃቀም በተመለከተ ሦስት ደንቦች (rules) አሉ። እነሱ የሚከተሉት ናቸው።
ደንብ #1 ፡ በቤቶስ ፊልጡፍ ወመል (SI prefix symbol) እና በቶካድ ወመል (unit symbol) መካከል ክፍተት (space) አይኖርም ወይም አይደረግም።
ደንብ #2 ፡ የቤቶስ ፊልጡፎች (SI prefixes) አይጣመሩም (cannot be compunded)
ደንብ #3 ፡ በሆስሌታዊ ስሌቶች (algebraic calculations) ላይ የቤቶስ ፊልጡፍ ወመል (SI prefix symbol) እና የቶካድ ወመል (unit symbol) የሚታዩት እንደ አንድ ነጠላ ወመል (one single symbol) ነው።
ለቤቶስ ፊልጡፎች (SI prefixes) የሚያገለግለው ደንብ 3 (rule 3 ) ለማናቸውም ጠዋጢወች (variables) ከሚያገለገለው ከተለመደው (usual) የሆስሌት ደንብ (algebraic rule) የተለየ በመሆኑ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
ምሳሌ ፣ ያዲሳባ ከተማ የቆዳ ስፋት በቅርበዛ 500 ሃጃኖሜትር ካልቶና (500 kilometer square = 500 km2 ) ነው። ባንድ ወቅት አዲሳባን ሙሉ በሙሉ የሚያዳርስ ሃይለኛ ዝናብ ጣለና 2.54 cm ውሃ አወረደ እንበል። ሁሉም የዘናቡ ጠብታቸወች (rain drops) እኩል ወርከፍ (equal size) ያላቸው ሉሎ ች (spheres) ናቸው እንበለና፣ ያንዷ ጠብታ ገማዘንግ (diameter) ደግሞ 4cm ነው እንበል። በዝናቡ ወቅት የወረዱትን ጠብታወች ጠቅላላ ቁጥር በቅርበዛ (approximately) ፈልግ።
መስፍን አረጋ mesfinamharic.com mesfin.arega@gmail.com