Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124
Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124

ደረጃ ከሚለው ደርክ (ደርከኛ) [standard] የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። ደርክ (ደርከኛ) [standard] ማለት መደበኛ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ደረከ (standardize)፣ ድርክ (ድሩክ) [standardized]፣ ደራኪ (standardizing)፣ ድረካ (standardization) እያለ ይሄዳል።
standard = ደርክ፣ ደርከኛ
standard equation = ደርከኛ እኩልታ
standard deviation = ደርከኛ ፍንገጣ
standard form = ደርከኛ መልክ
standard unit = ደርከኛ ቶካድ
standard of time = የጊዜ ደርክ
standard of living = የኑሮ ደርክ
standardize = ደረከ
standardization = ድረካ
ሱራ (ስዕል) እንዲሁም ፈኪ (ስዕል) ከሚሉት የኦሮምኛ ቃሎች ሱርፊክ (figure) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ሱርፊክ ማለት ንድፍ፣ ስዕል ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ሶረፈከ (to figure)፣ ሱርፍክ (figured)፣ ሶርፋኪ (figuring)፣ ሱርፈካ (figuring) እያለ ይሄዳል። ሱርፊክሳ (figurehead) ማለት ደግሞ የይስሙላ መሪ ማለት ነው።
ኢዶ ማለትም ቦታ የሚለው የኦሮምኛ ቃል locus የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል። ኢዶ (locus) ማለት የተወሰኑ መስፈርቶችን ወይም እኩልታወችን (equations) የሚያሟሉ ነጥቦች ባንድነት የሚሠሩት ክብን (circle) ወይም ሉልን (sphere) የመሰለ ቂሳሲናዊ ሱርፊክ (geometrical figure) ማለት ነው።
figure = ሱርፊክ
locus = ኢዶ
locus of points = የነጥቦች ኢዶ
ገመረ (ፈጸመ፣ ጨረሰ) የሚለው የግእዝ ቃል complete, complement የሚሉትን የንግሊዘኛ ቃሎች ይተካልናል። ገመረ (complete, complement) ማለት ሙሉ አደረገ፣ ሞላ፣ አሟላ ማለት ሲሆን ፣ ግሱም ሲረባ ገመረ (complete, complement)፣ ግምር (ግሙር) [completed, complemented]፣ ገማሪ (competing, complementing)፣ ግማራ (completing, complementing) እያለ ይሄዳል።
በሚከተለው ሱርፊክ (figure) ላይ እንደተመለከተው፣ካልቶና ግመራ (completing the square) ማለት ካልቶናን (square) ሙሉ ማድረግ ወይም ካልቶና ያልሆነን ካልቶናማድረግ ማለት ነው።

“ክብና ፉንባ” በሚለው ጦማር ላይ በስፋት እንደተወሳው፣ ክብ ማለት ሁሉም ነጥቦቹ ከመሀሉ (center) እኩል ርቀት ላይ የሚገኙ ሰቴ ሱርፊክ (planar figure) ነው። በኢዶ (locus) ቋንቋ ደግሞ ክብ ማለት መል (center) ከሚባል አንድ ነጥብ ያላቸው ርቀት እኩል የሆነ የወልሰቴ ነጥቦች ኢዶ (locus of coplanar points) ነው ተብሎ ይበየናል (defined)።


በሩንጌራባዊ ቅንጅ ስርካት (rectangular coordinate system) መሠረት የማናቸውም ክብ አጠቃላይ እኩልታ (general equation) እንዲሁም የክቡ መሀል (center) እና አክዘንግ (radius) በሚከተሉት ቀመሮች ይሰጣሉ።

የማናችውንም ክብ እኩልታ ባጠቃላይ መልክ (general form) ከመግለጽ ይልቅ በደርከኛ መልክ (standard form) መግለጽ የበለጠ ገላጭ ይሆናል፣ የክቡን መሀል (center) እና አክዘንግ (radius) በቀላሉ ለማንበብ ያስችላልና። የክብ እኩልታ አጠቃላይ መልክ (general form) ወደ ደርከኛ መልክ (standard form) የሚለወጠው ደግሞ የካልቶና ግመራ (completing the square) ዘዴን በመጠቀም እንደሚከተለው ነው።



መሀላቸው (center) ያው (same) የሆነ፣ ማለትም አንድ መሃል ያላቸው ወልሰቴ ክቦች (coplanar circles) ማለትም በያው ሰቴ (same plane) ላይ የሚውሉ ክቦች ወልመሀል ክቦች (concentric circles) ይባላሉ። በሌላ አባባል ወልመሀል ክቦች ማለት መሀላቸውም አንድ፣ ሰቴያቸውም አንድ የሆነ ክቦች ማለት ነው።




ሩንጋ ክቦች (orthogolal circles, perpendicular circles) ማለት ሩንጋ ዘዌ (right angle = 90o) በመስራት የሚመሳበሩ (intersect) ማለትም የሚቆራረጡ ክቦች ማለት ነው። በሌላ አባባል ሩንጋ ክቦች ማለት በሚመሳበሩባቸው ነጥቦች (intersection points) ላይ ያሏቸው ታክመሮች (tangents) ርስበራሳቸው ሩንጋ (perpendicular) የሆኑ፣ ማለትም ሩንጋ ዘዌ (right angle = 90o) የሚሠሩ ክቦች ማለት ነው።

ማናችውም ሁለት ክቦች ሩንጋ (orthogonal, perpendicular) ይሆኑ ዘንድ ማሟላት ያለባቸው መስፈርት (condition, criterion)፣ የሩንጋነት መስፈርት (orthogonality condition, orthogonality criterion) ይባላል። ይህም መስፈርት በሚከተለው ሱርፊክ ላይ ተመልከቷል።


መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com