Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124
Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124

በዚህ ጦማር ላይ የምንጠቀምባቸው ያንዳንድ ቃሎች ትርጉሞች የሚገኙት ወናብ እና ወታብ ቁጥሮች (Real & Complex Numbers) በሚለው ጦማር ላይ ስለሆነ፣ ይህን ጦማር ከማንበብወ በፊት ጦማሩን ቢያንስ ቢያንስ በገረፍታ ይመልከቱ።



የርቢወች (powers) እሴቶች የሚሰሉት (calculated) የጉባክ ደንቦች (rules of exponents) ወይም የጉባክ ሕጎች (laws of exponents) የሚባሉትን የሚከተሉትን ደንቦች (rules) ወይም ሕጎች (laws) በመጠቀም ነው።

ርቢወች (powers) ክልዔቱ፣ ሠለስቱ፣ ዐርባቱ ወዘተ. የሚሉትን የግእዝ ቁጥሮች አካሄድ በመከተል እንደሚከተለው ይሰየማሉ። ለተጨማሪ ማብራርያ “የቁጥሮች ስሞች” የሚለውን ጦማር ይመልከቱ።

root, radical = ሥርቢ
root, radical (verb) = ሠረበ
radicand = ተሠራቢ
radical sign (radical symbol) = ሥርቢ ምልክት፣ ሥርቢ ወመል
በሒሳብሲን (mathematics) ውስጥ ሥርቢወች (roots) የሚበየኑት (defined) እንደሚከተለው ነው።


ልክ እንደ ርቢወች (power) ሥርቢወችም (roots) የሚሰየሙት ክልዔቱ፣ ሠለስቱ፣ ዐርባቱ ወዘተ የሚሉትን የግእዝ ቁጥሮች አካሄድ በመከተል እንደሚከተለው ነው።


የሥርቢወች (radicals) እሴቶች የሚሰሉት (calculated) የሥርቢ ደንቦች (rules of radicals) ወይም የሥርቢ ሕጎች (laws of radicals) የሚባሉትን የሚከተሉትን ደንቦች (rules) ወይም ሕጎች (laws) በመጠቀም ነው።

ርቢወች (powers) እና ሥርቢወች (radicals, roots) የሚዛመዱት የጉባክ ደንቦች (rules of exponents) በሚለው ክፍል ላይ በተመለከተነው የነሻን ጉባኮች ደንብ (rule of fractional exponents) በሚባለው ደንብ (rule) መሠረት ነው።


በነሻን (fraction) p/q ላይ የላይኛው ቁጥር ማለትም (p) ፎክመን (nominator) ሲባል፣ የታችኛው ቁጥር ማለትም (q) ደግሞ ደርመን (denominator) እንደሚባል ወናብ እና ወታብ ቁጥሮች (Real & Complex Numbers) በሚለው ጦማር ላይ አይተናል።

ደርመን ፉደራ (rationalizing the denominator) ማለት ደርመኑ አልፎደር (irrational) የሆነን ነሻን (fraction) ፎደር (rational) እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው።

ደርመን ፉደራን (rationalization of the denominator) በተመለከት የሚከተሉት ቀመሮች (formulas) ጠቃሚ ናቸው።

መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com