Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124
Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124

አርገቹ (ማግኘት) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ረቸገ (derive) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ግሱም ሲረባ ረቸገ (derive)፣ ርቻግ (ርችግ፣ ርቹግ) [derived]፣ ረቻጊ (deriving)፣ ርቸጋ (derivation)፣ ርችገት፣ ርቻጌ፣ ርቻጎሽ እያለ ይሄዳል። ረቸገ (derive) ማለት አገኘ እንደ ማለት ሲሆን፣ ርቻግ (derived) ማለት ደግሞ የተረቸገ (ማለትም የተገኘ) ማለት ነው።
derive = ረቸገ
derived = ርቻግ
derived formula = ርቻግ ቀመር
derived unit = ርቻግ ቶካድ
derivation = ርቸጋ

አሳበረ (መንገድ አቋረጠ፣ አግድም፣ መስቀለኛ ሄደ) ከሚለው ምስባር (intersection, intercept) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ምስባር ማለት መገናኛ፣ መቆራረጫ እንደ ማለት ነው። ግሱም ሲረባ መሰበረ (intersect, intercept)፣ ምስብር (ምስቡር) [intersected, intercepted]፣ መስባሪ (intersecting, intercepting)፣ ምስበራ (intersecting, interception)፣ ምስብረት፣ ምስባሬ፣ ምስባሮሽ እያለ ይሄዳል።
ባንድ ነጥብ ላይ የሚመሳብሩ (ማለትም የሚገናኙ ወይም የሚቆራረጡ) ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ መስመሮች ተመሳባሪ መስመሮች (intersecting lines) ወይም መስባሪ መስመሮች (intersecting lines) ይባላሉ። መስመሮቹ የሚመሳበሩበት (ማለትም የሚገናኙበት ወይም የሚቆራርጡብት) ነጥብ ደግሞ ምስባር ነጥብ (intersection point) ወይም ምስብረት ነጥብ (intersection point) ወይም መመሳበርያ ነጥብ (intersection point) ይባላል።

“ነጥቦች፣ መስመሮች እና ዘዌወች” በሚለው ጦማር ላይ በሰፊው እንደተወሳው፣ ገዘመ (ማለትም ቆረጠ፣ ከፈለ፣ አመመ) የሚለው የግእዝ ቃል transverse የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል። ገዘመ ማለት ቆረጠ፣ አቋረጠ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ገዘመ (transverse)፣ ግዝም (ግዙም)፣ ገዛሚ፣ ግዘማ፣ ግዝመት፣ ግዛሜ፣ ግዛሞሽእያለ ይሄዳል።
ሁለት ወይም ከዚያ በላይ መስመሮችን አቋርጦ የሚያልፍ፣ ማለትም ከሁለት ወይም ከዚያ በላይ መስመሮች ጋር የሚመሳበር (intersect) መስመር ገዛሚ መስመር (transverse line, transversal) ወይም ባጭሩ ገዛሚ ይባላል።
ሁለት መስመሮች በገዛሚ (transversal) ሲገዘሙ፣ ፈራቂ ውስጣዊ ዘዌወች (alternate interior angles)፣ ፍራቂ ውጫዊ ዘዌወች (alternate exterior angles) እና ወልታቢ ዘዌወች (corresponding angles) የሚባሉ ስምንት ዘዌወች ይመሠረታሉ።
ወልታቢ (corresponding) የሚለው ቃል የተገኘው ወል (የጋራ) እና ከተበ (ጻፈ) ከሚሉት ቃሎች ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ወለተበ (correspond)፣ ውልትብ (ውልቱብ) [corresponded]፣ ወልታቢ (corresponding)፣ ውልተባ (corresponding)፣ ውልትበት፣ ውልታቤ፣ ውልታቦሽ እያለ ይሄዳል። ወለተበ (correspond) ማለት ተመሳሰለ እንዲሁም ተጻጻፈ ማለት ነው።

በገዛሚ (transversal) የሚገዘሙ ሁለት መስመሮች ኩልኩት መስመሮች (parallel lines) ከሆኑ፣ ማለትም ኩልኩት መስመሮች በገዛሚ ሲገዘሙ

ልዩ እና ብቹ ከሚሉት ልቹ (unique)፣ ልቹነት (uniqueness) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። ልቹ (unique) ማለት መሰል የሌለው፣ የብቻ የሆነ ማለት ነው። በልቹ ሁኔታ (uniquely) ማለት ደግሞ መሰል በሌለው ሁኔታ ማለት ነው። ግሱም ሲረባ ለቸመ (make unique, uniquely determine) ፣ ልችም (ልቹም)፣ ለቻሚ፣ ልቸማ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም። ለቸመ ማለት ልቹ ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ልችም ማለት ደግሞ የተለቸመ ማለት ነው።
unique = ልቹ
uniqueness = ልቹነት
unique (verb) = ለቸመ
ለየ እና መረጠ ከሚሉት ለየጠ (distinguish) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ለየጠ (distinguish) ማለት ከሌሎች መርጦ ለየ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ለየጠ (distinguish)፣ ልይጥ (ልዩጥ) [distinguished, distinct]፣ ለያጢ (ለያጭ) [distinguishing, distinctive]፣ ልየጣ (distinguishing)፣ ልይጠት እያለ ይሄዳል።
distinguish = ለየጠ
distinguishable (distinguishability) = ተለያጭ፣ ተለያጭነት
distinct – ልይጥ
distinctive (distinguishing) = ለያጢ፣ ለያጭ
distinction = ልየጣ፣ ል
“አሃሲን እና ሆስሌት” በሚለው ጦማር ላይ በስፋት እንደተወሳው፣ ሸነሸነ (በቀጭኑ ሰነጠቀ) ከሚለው ቃል ነሻን (fraction) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ግሱም ሲረባ ነሸነ (fractionalize, fractionate)፣ ንሽን (ንሹን) [fractionalized, fractionated]፣ ነሻኒ (ነሻኝ) (fractionalizing, fractionator)፣ ነሸና (fractionalization, fractionation) እያለ ይሄዳል። ነሸነ (factorize) ማለት በነሻን (factor) መልክ ገለጸ ማለት ሲሆን፣ ንሽን (factorized) ማለት ደግሞ የተነሸነ ማለት ነው።
ነሻን (fraction) q/p የነሻን p/q ደባስ (reciprocal) ይባላል። ደባስ (reciprocal) ማለት ግልባጭ እንደ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ደቢሱ (ማለትም መመለስ፣ መቀለስ፣ መገልበጥ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው። ግሱም ሲረባ ደበሰ (reciprocate)፣ ድብስ (ድቡስ) [reciprocated]፣ ደባሲ(ደባሽ) [reciprocator]፣ ድበሳ (reciprocation)፣ ድባሴ (reciprocity) እያለ ይሄዳል። ደበሰ (reciprocate) ማለት ገለበጠ እንደ ማለት ሲሆን፣ ድብስ (reciprocated) ማለት ደግሞ የተደበሰ ማለትም የተገለበጠ ማለት ነው።

በሒሳብነክ ሰገሎች (sciences) ውስጥ በተለይም ደግሞ በራሱ በሒሳብሲን (mathematics) እንዲሁም በጉሲን (physics) እና በፓካርሲን (chemistry) ውስጥ የግሪክ ፊደል ደልታ (delta = Δ) የሚያገለግለው በእሴት (value) ላይ የተከሰተን ለውጥ (change) ለማመልከት ነው።

ቀጤ መስመር (straight line) ማለት ራሱ ስያሜው እንደሚናገረው ቀጥ ያለ መስመር ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል የተወጠረ የክራር ጅማት ወይም የማሲንቆ ጭራ የሚሠራው መስመር ቀጤ መስመር ነው።
ሁለት ልይጥ ነጥቦች (two distinct points) አንድን ቀጤ መስመር (straight line) ይለችማሉ (uniquely determine)፣ ማለትም በልቹ (unique) ሁኔታ ይወስናሉ። በሌላ አባባል በሁለት የተለያዩ ነጥቦች ላይ የሚያልፍ ቀጤ መስመር (straight line) አንደና አንድ ብቻ (one and only one) ነው።

ካሁን በኋላ ቀጤ መስመር (straight line) የሚባለውን ባጭሩ መስመር (line) እንለዋለን። በሌላ አባባል ካሁን በኋላ መስመር (line) ስንል ቀጤ መስመር (straight line) ማለታቸን ነው ብለን እንስማማለን።

ተዛባ (አጋደለ፣ ተጣመመ) ከሚለው ቃል ዘበገ (to slope, incline)፣ ዝብግ (ዝቡግ) [sloped, inclined]፣ ዘባጊ (sloping, inclining)፣ ዝበጋ (sloping, inclining)፣ ዝባጌ (inclination) እያለ የሚሄደውን ቃል እናገኛለን። ዘበገ (to slope) ማለት አጋደለ ማለት ሲሆን፣ ዘበግ (slope) ማለት ደግሞ የዝባጌ መጠን ማለት ነው።
slope (inclination) =ዘበግ፣ ዝባጌ
slope (verb) = ዘበገ
sloping (inclining, inclined) = ዘባጊ
inclined plane = ዘባጊ ሰቴ
በሚከተለው ሱርፊክ (figure) ላይ የተመለከተውን መስመር እናጢን። ይህ መስመር 2 ቶካዶች (2 units) ባቀና (ማለትም ከፍ ባለ፣ በተነሳ) ቁጥር 3 ቶካዶች (3 units) እየተኛ (ማለትም እየተጋደመ) ይሄዳል። በዚህም ምክኒያት የዚህ መስመር ዘበግ (slope) 2/3 ነው እንላለን።

በሚከተለው ሱርፊክ (figure) ላይ የተመለከተው መስመር ደግሞ 3 ቶካዶች (3 units) ባዘቀዘቀ (ማለትም ዝቅ ባለ፣ በወረደ) ቁጥር 8 ቶካዶች (8 units) እየተኛ (ማለትም እየተጋደመ) ይሄዳል። በዚህም ምክኒያት የዚህ መስመር ዘበግ (slope) -3/8 ነው እንላለን።

ባጠቃላይ አነጋገር ደግሞ በነጥቦች A (x1, y1) እና B (x2, y2) ላይ የሚያልፍ መስመር ዘበግ (slope) በሚከተለው መንገድ ይበየናል (defined)።

የማናቸውም መስመር ዘበግ (slope) የመስመሩን አዝማሚነት መለኪያ (measure) ነው። በዚህም ምክኒያት

ሸቃቢ (ascending) የሚለው ቃል የተገኘው አሻቀበ (ወደ ላይ ተነሳ፣ ከፈ አለ) ከሚለው ያማረኛ ቃል ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ሸቀበ (ascend)፣ ሽቅብ (ሽቁብ) [ascended]፣ ሸቃቢ (ascending)፣ ሽቀባ (ascending, ascent)፣ ሽቃቤ እያለ ይሄዳል።
ዘቃቢ (descending) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ አዘቀዘቀ ከሚለው ቃል በመነሳትና ሸቃቢ (ascending) የሚለውን ቃል አካሄድ በመከተል ነው። ግሱም ሲረባ ዘቀበ (descend)፣ ዝቅብ (ዝቁብ) [descended]፣ ዘቃቢ (descending)፣ ዝቀባ (descending, descent)፣ ዝቃቤ እያለ ይሄዳል።
ascend = ሸቀበ
ascending = ሸቃቢ
ascending line = ሸቃቢ መስመር
descend = ዘቀበ
descending = ዘቃቢ
descending line = ዘቃቢ መስመር
አግዳሚ (horizontal) x-ረቲድን (x-axis) እሆነ ነጥብ (point) ላይ የሚያቋርጥ የማናቸውም መስመር (line) ዘበግ ዘዌ (angle of inclination, slope angle) ማለት ከነጥቡ በስተቀኝ በኩል ካለው የ x-ረቲድ (x-axis) ክፍል በመነሳት እስከ መስመሩ ድረስ በኢሰዓትያ አቅጣጫ (anticlockwise direction) የሚለካ ዘዌ (angle) ማለት ነው።

በሚከተለው ሱርፊክ (figure) ላይ እንደተመለከተው፣ ሁለት መስመሮች ኩልኩት (parallel) ከሆኑ፣ ዘበግ ዘዌወቻቸው (inclination angles) ወልታቢ ዘዌወች (corresponding angles) ይሆናሉ፣ ስለሆኑም እኩል (equal) ይሆናሉ። ስለዚህም ኩልኩት መስመሮች (parallel lines) እኩል ዘበግ (equal slope) አላቸው ማለት ነው።
በግልባጭ (conversely) አነጋገር ደግሞ እኩል ዘበግ (equal slope) ያላቸው መስመሮች ሁሉ ኩልኩት (parallel) ናቸው ማለት ነው።

በሚከተለው ሱርፊክ (figure) ላይ እንደተመለከተው፣ ሁለት መስበሮች ሩስበራሳቸው ሩንጋ (perpendicular) ከሆኑ፣ ዘበጎቻቸው (slopes) የርስበራሳቸው ሉንታ ደባሶች (negative reciprocals) ይሆናሉ።


በሩንጌራባዊ ቀንጅ ስርካት (rectangular coordinate system) ላይ

የመስመር እኩልታ (equation of line) ማለት በመስመሩ ላይ የሚገኝ እያንዳንዱ ነጥብ (point) ያለውን x-ቀንጅ (x-coordinate) ከነጥቡ y-ቀንጅ (y-coordinate) ጋር የሚያዛምድ እኩልታ (equation) ማለት ነው።
በሌላ አባባል የመስመር እኩልታ (equation of a line) ማለት በመስመሩ ላይ የሚገኙ ነጥቦች (points) ሁሉም ውነት (true) የሚያደርጉት፣ ከመስመሩ ውጭ የሚገኙ ነጥቦች ደግሞ ሁሉም ውሸት (false) የሚያደርጉት እኩልታ ማለት ነው። የመስመር እኩልታ


በተመሳሳይ ሁኔታ

አልወርጃሚ (nonvertical) ማለት ወርጃሚ (vertical) ያልሆነ ማለት ነው። ስለዚህም አልወርጃሚ መስመር (nonvertical line) ማለት አግዳሚ መስመር (horizontal line) ወይም አዝማሚ መስመር (slanted line, oblique line) ማለት ነው። በሌላ አባባል አልወርጃሚ መስመር (nonvertical line) አግዳሚ መስመርን (horizontal line) እና አዝማሚ መስመርን (slanted line, oblique line) የሚያካትት አጠቃላይ ቃል ነው ማለት ነው።
የማናቸውም አልወርጃሚ መስመር እኩልታ (equation of nonvertical line) በሚከተሉት ስድስት መልኮች (three forms) ሊጻፍ ይችላል።
በተራ ቁጥር (2) ላይ ዘበግ–ምስባር መልክ (slope-intercept form) እና ዘበግ–ምስባር እኩልታ (slope-intercept equation) የሚሉትን ላማረኛ አጠራር እንዲመቹና ከተራ ቁጥር (1) ጋር እንዲመሳሰሉ ምስባር–ዘበግ መልክ (intercept-slope form) ወይም ባጭሩ ምስባር–ዘበግ እኩልታ (intercept-slope equation) እንላቸዋለን።
በማናቸውም አልወርጃሚ መስመር (nonvertical line) ላይ የሚገኝ ያንድ ነጥብ ቀንጆች (coordinates) P (x1, y1) እና የመስመሩ ዘበግ (slope) m ከታወቁ ፣ የመስመሩ እኩልታ (equation of the line) ሊታወቅ ይችላል። ይህም የመስመሩ እኩልታ መልክ (form) ነጥብ-ዘበግ መልክ (point-slope form) ወይም ባጭሩ ነጥብ-ዘበግ እኩልታ (point-slope equation) ይባላል።


የማናቸውም አልወርጃሚ መስመር (nonvertical line) ዘበግ (slope) m እና y-መስባር (y-intercept) b ማለትም መስመሩ y-ረቲድን (y-axis) የሚያቋርጥበት ነጥብ (point) ያለው y ቀንጅ (y coordinate) ከታወቁ ፣ የመስመሩ እኩልታ (equation of the line) ሊታወቅ ይችላል። ይህም የመስመሩ እኩልታ መልክ (form) ዘበግ-ምስባር መልክ (slope-intercept form) ወይም ባጭሩ ዘበግ-ምስባር እኩልታ (slope-intercept equation) ወይም ደግሞ ላማረኛ አጠራር እንዲመች ምስባር-ዘበግ እኩልታ (intercept-slope equation) ይባላል።


በማናቸውም አልወርጃሚ መስመር (nonvertical line) ላይ የሚገኙ ሁለት ነጥቦች ቀንጆች (coordinates) P1 (x1, y1) እና P2 (x2, y2) ከታወቁ ፣ የመስመሩ እኩልታ (equation of the line) ሊታወቅ ይችላል። ይህም የመስመሩ እኩልታ መልክ (form) ሁለት-ነጥብ መልክ (two-point form) ወይም ባጭሩ ሁለት-ነጥብ እኩልታ (two-point equation) ይባላል።


የማናቸውም አልወርጃሚ መስመር (nonvertical line) x-ምስባር (x-intercept) a እና y-መስባር (y-intercept) b ከታወቁ ፣ የመስመሩ እኩልታ (equation of the line) ሊታወቅ ይችላል። ይህም የመስመሩ እኩልታ መልክ (form) ሁለት-ምስባር መልክ (slope-intercept form) ወይም ባጭሩ ሁለት-ምስባር እኩልታ (slope-intercept equation) ይባላል።


ያማረኛ አነጻጸር (comparison) የተንዛዛ ከመሆኑም በላይ አሻሚነት አለው። ለምሳሌ ያህል ትልቅ በሚለው ቅጽል ለማነጻጸር ስንፈልግ፣ በጣምትልቅ፣ እጅግበጣምትልቅ እንላለን። በጣም ትልቅ ስንል ግን ያንድን ነገር ትልቅነት እየገለጽን ወይም ደግሞ የሁለት ነገሮችን ትልቅነት እያነጻጸርን ሊሆን ይችላል። ይህን አሻሚነትና መንዛዛት ለማስወገድ ስል፣ ላማረኛ ንጽጽርን በሚከተለው መንገድ ፈጥሬለታለሁ።
ለምሳሌ ያህል ጥሩ (good) የሚለውን ብንወስድ፣ በጣምጥሩለማለት ፐጥሩ (better) እንላለን፣ እጅግበጣምጥሩለማለት ደግሞ ዠጥሩ (best) እንላለን። ፊደሎች ፐ እና ዠ ለንጽጽር የተመረጡበት ምክኒያት፣ በነዚህ ፊደሎች የሚጀምሩ ብዙ ቃሎች ስለሌሉ ነው።
short, shorter, shortest =አጭር፣ ፐአጭር፣ ዠአጭር(ዣጭር)
shortest distance = ዣጭር ርቀት
ዣጭር ርቀት (shortest distance) ከሁሉም ያጠረ ርቀት ማለትም መትሐት ርቀት (least) ወይም ጨቅሊስ ርቀት (minimum distance) ማለት ነው።
ባንድ መስመር (line) እና መስመሩ ላይ በማይውል ነጥብ (point not on the line) መካከል ያለው ዣጭር ርርቀት (shortest distance) ከነጥቡ ወደ መስመሩ የሚሰመረውና ከመስመሩ ጋር ሩንጋ ዘዌ (right angle = 90o) የሚሰራው ሩንጋ የቀጤ መስመር ዐጽቅ (perpendicular line segment) ወይም ባጭሩ ሩንጋ ዐጽቅ (perpendicular segment) ነው።

በሒሳብሲን (mathematics) እና ጉሲን (physics) ውስጥ normal ማለት perpendicular ማለት ነው። ስለዚህም ሩንጋ (perpendicular, normal) የሚለው ያማረኛ ቃል ሁለቱንም የእንግሊዘኛ ቃሎች ይተካል ማለት ነው። የንግሊዘኛው normal የተገኘው norma (ማዕዘን) ከሚለው የላቲን (Latin) ቃል ነው።

የቀጤ መስመር ሩንጋ እኩልታ (normal equation of a line) ርቸጋ (derivation) ማለትም አገኛኘት በሚከተለው ሱርፊክ (figure) ላይ ተመልክቷል።

ከዚህ በላይ የተመለከትናቸው ሁሉም የቀጤ መስመሮች እኩልታወች (equations of lines) የሚከተለው አጠቃላይ ሃድቶናዊ እኩልታ (general linear equation) ልዩ ረገዶች (special cases) ናቸው። እዚህ አጠቃላይ ሃድቶና እኩልታ (general linear equation) ላይ A, B እና C ቋሚ ወናብ ቁጥሮች (constant real numbers) ናችው።


ድርሞ (summary) ማለት ማጠቃለያ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ድምር የሚለውን ቃል በትንሹ በመለወጥ ነው። ግሱም ሲረባ ደረመ (summarize)፣ ድርም (ድሩም) [summarized]፣ ደራሚ (summarizing)፣ ድረማ (summarization)፣ ድርመት፣ ድራሜ፣ ድራሞሽ እያለ ይሄዳል። ድረማ እና ድራማ እንዳይምታቱብወት።
summary = ድርሞ
summarize = ደረመ
summarization = ድረማ

ያንድ መስመር እኩልታ ባጠቃላይ ሃድቶናዊ እኩልታ (general linear equation) መልክ ከተገለጸ፣ በመስመሩ እና መስመሩ ላይ በማይውል ነጥብ (point not on the line) መካከል ያለው ዣጭር ርቀት (shortest distance) በሚከተለው ቀመር (formula) ይሰጣል።

በዚህ አጠቃላይ ቀመር (general formula) መሠረት፣ ማናቸውም መስመር ከፈጅር (origin) ያለው ዣጭር ርቀት (shortest distance) በሚከተለው ቀመር ይሰጣል።

የነጥብና የመስመር ዣጭር ርርቀት (shortest distance) ቀመር (formula) ርቸጋ (derivation) ማለትም አገኛኘት በሚከተለው ሱርፊክ (figure) ላይ ተመልክቷል።

የሁለት መስመሮች እኩልታወች በምስባር-ዘበግ መልክ (intercept-slope form) ከተሰጡ፣ የመስመሩቹ ምስባር ነጥብ (intersection point) ማለትም መስመሮቹ የሚቆራረጡበት ነጠብ፣ እንዲሁም ምስባር ዘዌ (intersection angle) ማለትም መስመሮቹ ምስባር ነጥብ (intersection point) ላይ የሚሠሩት ዘዌ (angle) በሚከተሉት ቀመሮች ይሰጣሉ።

በሁለት ኩልኩት መስመሮች (parallel lines) መካከል ያለው ርርቀት (distance) በሚከተለው ቀመር ይሰጣል።

መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com