Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124
Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124

ሽንብራ /ዱቤ\ አይገኝም \በዱቤ/።
ያማረኛ አነጻጸር (comparison) የተንዛዛ ከመሆኑም በላይ አሻሚነት አለው። ለምሳሌ ያህል ትልቅ በሚለው ቅጽል ለማነጻጸር ስንፈልግ፣ በጣም ትልቅ፣ እጅግ በጣም ትልቅ እንላለን። በጣም ትልቅ ስንል ግን ያንድን ነገር ትልቅነት እየገለጽን ወይም ደግሞ የሁለት ነገሮችን ትልቅነት እያነጻጸርን ሊሆን ይችላል። ይህን አሻሚነትና መንዛዛት ለማስወገድ ስል፣ ላማረኛ ንጽጽርን በሚከተለው መንገድ ፈጥሬለታለሁ።
ለምሳሌ ያህል ጥሩ (good) የሚለውን ብንወስድ፣ በጣም ጥሩ ለማለት ፐጥሩ (better) እንላለን፣ እጅግ በጣም ጥሩ ለማለት ደግሞ ዠጥሩ (best) እንላለን። ፊደሎች ፐ እና ዠ ለንጽጽር የተመረጡበት ምክኒያት፣ በነዚህ ፊደሎች የሚጀምሩ ብዙ ቃሎች ስለሌሉ ነው።
fast, faster, fastest = ፈጣን፣ ፐፈጣን፣ ዠፈጣን
slow, slower, slowest = ቀሳን፣ ፐቀሳን፣ ዠቀሳን
large, larger, largest = ትልቅ፣ ፐትልቅ፣ ዠትልቅ
smaller, smaller, smallest = ትንሽ፣ ፐትንሽ፣ ዠትንሽ
near, nearer, nearest = ቅርብ፣ ፐቅርብ፣ ዠቅርብ
far, farther, farthest = ሩቅ፣ ፐሩቅ፣ ዠሩቅ
ለምሳሌ ያህል ለዠመጥፎ ተዘጋጅ (prepare for the worst)፣ ዠመጥፎውን ጠብቅ (expect the worst)፣ ዠመጥፎ ረገድ(the worst case) ይሆናሉ። እንዲሁም the nearer the church, the further from God የሚለው የፈረንጆች ብሂል ለቤተሔር ፐቅርብ፣ ላብሔር ፐሩቅተብሎ ባጭሩ ይተረጎማል። በተመሳሳይ መንገድ የሚከተሉትን ዐረፍተነገሮች እናገኛልን።
አማረኛችን የማጥበቅና የማላላት ምልክቶች የሉትም። እርግጥ ነው፣ ይህ እንደ ጉድለት መታየት የለበትም፣ የቃልን መጥበቅና መላላት ካገባቡ (context) ወይም ከአውዱ መረዳት ይቻላልና። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ይህ የማጥበቅና የማላላት አሻሚነት፣ አማረኛን እንዳበጁት እያስበጁ ውብ ከሚያደርጉት እጹብ ጠባዮቹ ውስጥ አንዱና ዋናው ነው።
ሮቢት አግኝታት ገበያው ሲቀናኝ፣ ቅዳሜ ማለዳ ቶሎ ና ብትለኝ
ሐሙስ አላልፍ ብሎ ዓርብ ዓመትመሰለኝ።
ቅዳሜ መሽቶልኝ እስኪደርስ ሰንበት፣ ከሷ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት
ላፈር አይደለም ወይ የተፈጠርኩት።
አንዳንድ ጊዜ ግን ማጥበቅና ማላላትን ያለ አሻሚነት መግለጽ የግድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ለዚህ መፍትሄ ደግሞ ታላቁ ጦቢያዊ ደራሲ ክቡር ሐዲስ ዓለማየሁ ከሚጠብቀው ፊደል አናት ላይ ነቁጥ (.) ለመጨመር አሳብ አቅርበው፣ በታላቁ መጽሐፋቸው በፍቅር እስከ መቃብር ላይ ተግብረውታል (በተግባር አውለውታል)።
እንደኔ አመለካከት ግን፣ ነቁጥ ከመጠቀም ይልቅ መጥበቅና መላላትን በሚከተለው መንገድ መግለጽ የበለጠ አመች ይሆናል። ማጥበቅ ሲያስፈልግ፣ የሚጠብቀው ፊደል ወይም ፊደሎች በሁለት ዘብሪሶች (slashes) መካከል በሚከተለው መንገድ /…\ ይገባል። ማላላት ሲያስፈልግ ደግሞ፣ የሚላላው ፊደል ወይም ፊደሎች በሁለት ዘብሪሶች (slashes) መካከል በሚከተለው መንገድ \…/ ይገባል። ዘብሪስ (slash) የሚለው ቃል የተገኘው ለማርባት ይመች ዘንድ እዝባር ከሚለው ቃል ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ዘበረሰ (to slash)፣ ዝብርስ፣ ዘብራሲ (ዘብራሽ)፣ ዝብረሳ፣ ዝብራሴ፣ ዝብራሶሽ እያለ ይሄዳል።
ለምሳሌ ያህል አ/ለ\ ማለት ይገኛል ማለት ሲሆን፣ አ\ለ/ ማለት ደግሞ ተናገረ ማለት ነው። የሚጠ/ብ\ቅ ማለት የሚቆይ ማለት ሲሆን፣ የሚጠ\ብ/ቅ ማለት ደግሞ የሚጫኑት ማለት ነው። /አካፋ\ (drizzle) ማለት በትንሹ ጣለ ማለት ሲሆን፣ \አካፋ/ (shovel) ማለት ደግሞ ባለጀታ ማፈሻ ማለት ነው። /ያለኝ\ ማለት የያዝኩት ማለት ሲሆን፣ \ያለኝ/ ማለት ደግሞ የነገረኝ ማለት ነው። \ዱቤ/ ማለት ብድር ማለት ሲሆን፣ /ዱቤ\ ማለት ደግሞ የፈረንጅ ሽንብራ ነው። ሽንብራ /ዱቤ\ አይገኝም \በዱቤ/።
ፊደልን ለማጥበቅ ወይም ለማላላት ፊትጌ እና ኋልጌ ዘብሪሶችን (slashes) እንደምንጠቀም ሁሉ፣ ፊደልን ለማርዘም ወይም ለመገተት ደግሞ አጭር ቀስት (→) እንጠቀማለን። :: ለምሳሌ ያህል በ→ጀ፣ ኧ→ረ ይሆናሉ::
መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com