ጉሲን እና ቁነና (Physics & Measurement) ክፍል 7(ሐ-1)፤ መሠረታዊ ግሳቦች እና ኳርኮች (Part 7(C-1): Fundamental Forces & Quarks)

ማሳሰቢያ

ጉሲን እና ቁነና (Physics & Measurement) በሚለው ዋና ርዕስ ውስጥ የክፍል 7 ዓላማ ካልቪን (Kelvin) የሚባለውን የቤቶስ የሙቀት ቶካድ (SI unit of temperature) መበየን (define) ነው።  ይህን ለማድረግ ግን ከቶካዱ ጋር ስለተዛመዱ ፀንሳቦች (concepts) በግርድፉ ማለትም በጥልቀት ሳይሆን በተወሰነ መጠን ማውሳት አለብን።  ወደፊት ደግሞ በሌሎች ጦማሮች ላይ እነዚሁኑ ፅንሳቦች በጥልቀት እናወሳቸዋለን።    

  1. ክፍል 7(ሀ) ላይ ስለ ፍጥነት (speed)፣ ሶፊሳ (velocity) እና ጠደፋ (acceleration) አውስተናል።
  2. ክፍል 7(ለ) ላይ ስለ ቶኪማ ክባዊ ሑሰት (Uniform Circular Motion) አውስተናል። 
  3. በዚህ ክፍል ማለትም ክፍል 7(ሐ) ላይ ስለ ግሳብ (force) እና ሑሰት (motion) እናወሳለን። 
  4. ክፍል 7(መ)  ላይ ስለ ግሳብ (force) እና ሥራ (work) እናወሳለን። 
  5. ክፍል 7(ሰ) ላይ ስለ ጉልበት (energy) እና ሃይል (power) እናወሳለን።
  6. ክፍል 7(ረ) ላይ ስለ ሙቀት (temperature)፣ ግለት (heat) እና ውስጣዊ ጉልበት (internal energy) እናወሳለን። 
  7. ክፍል 7(ሠ) ላይ ስለ ሙቀትልካት (thermometry) እና ሙቀትለኪወች (therometers) እናወሳለን። 
  8. ክፍል 7(ቀ) ላይ ስለ ጋስ ሕጎች (gas laws) እናወሳለን። 
  9. በመጨረሻም ክፍል 7(በ) ላይ በክፍሎች 7(ሀ) እስከ ክፍሎች 7(ቀ) ላይ ያወሳናቸውን ፅንሳቦች (concpts) በመጠቀም ካልቪን (kelvin) የሚባለውን የቤቶስ የሙቀት ቶካድ (SI unit of temperature) እንበይናለን። 

ወንታ (positive)፣ ሉንታ (negative) እና ገልታ (neutral) 

  1. አወንታ ከሚለው ወንታ (positive) የሚለውን ቃል፣ አሉታ ከሚለው ሉንታ (negative) የሚለውን ቃል፣ ገለልታ ከሚለው ደግሞ ገልታ (neutral) የሚለውን ቃል እናገኛለን። 
  2. የገልታ (neutral) ግስ ሲረባ ገለተመ (neutralize)፣ ግልትም፣ ግልቱም [neutralized]፣ ገልታሜ [neutralizer]፣ ግልተማ (neutralization)፣ ግልትመት፣ ግልታሜ፣ ግልታሞሽ እያለ ይሄዳል።
  3. ገለተመ (neutralize) ማለት ገልታ (neutral) አደረገ ማለት ሲሆን፣ ግልትም (ግልቱም) ማለት ደግሞ የተገለተመ ማለት ነው። 
  4. የወንታ (positive) ግስ ሲረባ ወነተመ፣ ውንትም (ውንቱም)፣ ወንታሚ ፣ ውንተማ፣ ውንትመት፣ ውንታሜ፣ ውንታሞሽ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
  5. ወነተመ ማለት ወንታ (positive) አደረገ ማለት ሲሆን፣ ውንትም (ውንቱም) ማለት ደግሞ የተወነተመ ማለት ነው።
  6. የሉንታ (negative) ግስ ሲረባ፣ ለነተመ፣ ልንትም (ልንቱም)፣ ለንታሚ፣ ልንተማ፣ ልንትመት፣ ልንታሜ፣ ልንታሞሽ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
  7. ለነተመ ማለት ሉንታ (negative) አደረገ ማለት ሲሆን፣ ልንትም (ልንቱም) ማለት ደግሞ የተለነተመ ማለት ነው።    

positve = ወንታ
positive (verb) = ወነተመ
negative = ሉንታ
negative (verb) = ለነተመ
neutral =  ገልታ
neutralize = ገለተመ

ጸውሪክ (Charge) እና ጽውረካ (Charging)

  1. አሌክትሪክ (electric) የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል በማሳጠር ሌትሪክ እንለዋለን። ከዚህም ሌክትሮ (electro) የሚለውን ፊልጡፍ (prefix) እናገኛለን። ለምሳሌ ያህል electrodynamics የሚለው ሌክትሮሑሲን ይሆናል። 
  2. ጸዊር (መሸከም፣ ማቀፍ፣ ማዘል) የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ሌትሪክ (electric) ከሚለው ቃል ጋር በማጣመር ጸውሪክ (charge) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ስለዚህም ጸውሪክ (charge) ማለት ሌትሪክ ተሸካሚ ወይም አዛይ እንደ ማለት ነው።
  3. ሌትሪክ ጸውሪክ (electric charge) አብዛኛውን ጊዜ ባጭሩ ጸውሪክ (charge) ይባላል። 
  4. የጸውሪክ (charge) ግስ ሲረባ ጸወረከ (to charge)፣ ጽውርክ (charged)፣ ጸውራኪ (charger)፣ ጽውረካ (charging)፣ ጽውርከት፣ ጽውራኬ፣ ጽውራኮሽ እያለ ይሄዳል፣ ስልኩን ጸውርከው (charge the phone) እንዲሉ። 
  5. ጸወረከ (to charge) ማለት ጸውሪካም (ጸውሪክ ያለው) ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ጽውርክ (charged) ማለት ደግሞ የተጸወረከ ማለት ነው።
  6. ለምሳሌ ያህል ጽውርክ እኑስ (charged particle) ማለት ጽውሪክ ያለው እኑስ ማለት ነው።

electric = ሌትሪክ
electro (prefix) = ሌክትሮ
electrodynamics  (electrodynamic) = ሌክትሮሑሲን፣ ሌክትሮሑሲናዊ
charge (electric charge) = ጸውሪክ፣ ሌትሪክ ጸውሪክ
charge (verb) = ጸወረከ
charged (uncharged) = ጽውርክ፣ አልጽውርክ
charged particle =  ጽውርክ እኑስ
positive charge = ወንታ ጸውሪክ
negative charge = ሉንታ ጸውሪክ
net charge = ፋርዳ ጸውሪክ
charge density = ጸውሪክ እፍገት
charge carrie = ጸውሪክ ኩሊ
charge transfer = ጽውሪክ እወላ

ቁስ (Matter)፣ ቁስቻ (Material) እና ቁሰት (Mass)

  1. በንግሊዘኛ mass የሚባለውን ባማረኛ ቁስ እንለዋለን፣ matter የሚባለውን ቁሰት እንለዋለን፣ material የሚባለውን ደግሞ ቁስቻ እንለዋለን።   
  2. ቁስ (matter) ማለት ቁሰት (mass) ያለውና ህዋ የሚቀችብ (occupy space) ማናቸውም ነገር ማለት ነው።
  3. ቀቸበ (occupy) ማለት ያዘ፣ ሸፈነ፣ ተቆጣጠረ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ቀበቹ (መያዝ፣ መውረር) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው። ግሱም ሲረባ ቀቸበ (occupy)፣ ቅችብ (ቅቹብ) [occupied]፣ ቀቻቢ (occupier, occupant)፣ ቅቸባ (occupying)፣ ቅችበት፣ ቅቻቤ፣ ቅቻቦሽ  እያለ ይሄዳል።
  4. ህዋ የሚቀችብ (occupy space) ማለት ህዋ የሚይዝ፣ ህዋ የሚሸፍን ማለትም ወርከፍ (size) ያለው ማናቸውም ነገር ማለት ነው። 
  5. የቁሰት (mass) ግስ ሲረባ  ቆሰተ፣ ቁስት፣ ቆሳች፣ ቁሰታ፣ ቁሳቴ፣ ቁሳቶሽ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም። 
  6. ቆሰተ ማለት ቁሰት ሆነ ወደ አደረገ ማለት ሲሆን፣ ቁስት ማለት ደግሞ የተቆሰተ ማለትም ቁሰት ያለው ማለት ነው።
  7. ጽውርክ አካል (charged object) ማለት ጸውሪክ ያለው አካል ማለት እንደሆነ፣ ቁስት አካል (massed object) ማለት ደግሞ ቁሰት ያለው አካል ማለት ነው።
  8. አብዛኛውን ጊዜ ግን ቁስት አካል ማለት አያስፈልግም፣ አካል ሲባል ቁሰት አለውና። 
  9. ቁስቻ (material) ማለት ቁሳቁስ እንደ ማለት ነው።

mass = ቁሰት
mass (verb) = ቆሰተ
massed object = ቁስት አካል
matter = ቁስ
material = ቁስቻ
occupy = ቀቸበ
occupier (occupant) = ቀቻቢ
occupation = ቅቸባ

ቀኒጥ (Atom) እና ቡኒጥ (Nucleus)

  1. የሃጃኖግራም እና የሞል ብያኔወች (Definitions of the Kilogram and the Mole) በሚለው ጦማር ላይ እንደተመለከትነው፣ ቀኒጥ (atom) የሚለው ቃል የተገኘው ቅንጣት (ማለትም አንድ ፍሬ) ከሚለው ቃል ነው።
  2. የቀኒጥ (atom) ግስ ሲረባ ቀነጠ (atomize)፣ ቅንጥ (ቅኑጥ) [atomized]፣ ቀናጢ (ቀናጭ) [atomizer]፣ ቅነጣ (atomization)፣ ቅንጠት፣ ቅናጤ፣ ቅናጦሽ እያለ ይሄዳል። 
  3. ቀነጠ (atomize) ማለት ቀኒጥ (atom) ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ቅንጥ (ቅኑጥ) [atomized] ማለት ደግሞ የተቀነጠ ማለት ነው።
  4. ቀኒጥ (atom) የሚለውን ቃል ቡጥ (core) ከሚለው ቃል ጋር በማጣመር ቡኒጥ (nucleus) የሚለውን ቃል እናገኛለን። 
  5. ቡኒጥ (nucleus) ማለት በቀኒጥ (atom) መሃል ወይም እምብርት ላይ የሚገኝ የቀኒጥ ቡጥ (core of an atom) ማለት ነው።
  6. የቡኒጥ (nucleus) ግስ ሲረባ ቦነጠ (nucleate)፣ ቡንጥ (ቡኑጥ) [nucleated]፣ ቦናጢ (ቦናጭ) (nucleating)፣ ቡነጣ (nucleation)፣ ቡንጠት፣ ቡናጤ፣ ቡናጦሽ እያለ ይሄዳል። 
  7. ቦነጠ (nucleate) ማለት ቡኒጥ (nucleus) ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ቡንጥ (nucleated) ማለት ደግሞ የተቦነጠ ማለት ነው።  
  8. በተጨማሪ ደግሞ ቡኒጥ (nucleus) ከሚለው ቦነጠመ  (nuclearize)፣ ቡንጥም (ቡንጡም) [nuclearized]፣ ቦንጣሚ (nuclearizing)፣ ቡንጠማ (nuclearization)፣ ቡንጥመት፣ ቡንጣሜ፣ ቡንጣሞሽ እያለ የሚሄደውን ግስ እናገኛለን፣ ቡንጥም አገሮች (nuclearized countries) እንዲሉ።

atom = ቀኒጥ
atomize = ቀነጠ
nucleus = ቡኒጥ
nucleate = ቦነጠ
nuclearize = ቦነጠመ
nuclearized countries = ቡንጥም አገሮች

ቀዳምኑስ (Proton)፣ ተልኑስ (Electron) እና ገልኑስ (Neutron)

  1. ቀዳሚ (የመጀመርያ) ከሚለው ቀዳም (proto) የሚለውን ፊልጡፍ እናገኛለን። 
  2. ለምሳሌ ያህል ቀዳም (proton) የሚለውን ፊልጡፍ አስተኔ (አይነት) ከሚለው ቃል በማጣመር ቀዳምተኔ (prototype) የሚለውን ቃል እናገኛለን።   
  3. ቀዳም (proto) ከሚለው ፊልጡፍ (prefix) እና እኑስ (particle) ከሚለው ቃል ቀዳምኑስ (proton) የሚለውን ስያሜ እናገኛለን።
  4. ቀዳምኑስ (proton) ማለት በቀኒጥ ቡኒጥ ( nucleus of atom) ውስጥ የሚገኝ ወንታ ጸውሪክ (positive charge) ያለው እኑስ (particle) ነው።
  5. ለዚህ እኑስ በ 1913 ዓ. ም ላይ ቀዳምኑስ (proton) የሚለውን ስያሜ የሰጠው እንግሊዛዊው ጉሲነኛ (physicist) ኧርነስት ራዘርፎርድ (Ernest Rutherford) ሲሆን፣ ምክኒያቱ ደግሞ ሁሉም ቀኒጦች (all atoms) /የሚገነቡት\ ቡኒጡ (nucleus) አንድ ቀዳምኑስ (one proton) ብቻ ከሆነው ከሃይድሮጅን ቀኒጥ (hydrogen atom) ነው በሚለው እሳቤው መሠረት ነበር።
  6. ተላይ (ማለትም ተከታይ፣ ጭፍራ) ከሚለው የግእዝ ቃል እና እኑስ (particle) ከሚለው ቃል ተልኑስ (electron) የሚለውን ስያሜ እናገኛለን።
  7. የቀኒጥ (atom) ተልኑሶች (electrons) በቀኒጡ ቡኒጥ (nucleus) ዘርያ የሚዞሩ ሉንታ ጸውሪክ (negative charge) ያላቸው እኑሶች (particles) ናቸው።  ተልኑስ የተባሉትም የቡኒጥ ተላይ (ተከታይ፣ አጫፈሪ) በመሆናቸው ነው።
  8. ለምሳሌ ያህል ተልኑስ (electron) ከሚለው ቃል እና ሲን (logy) ከሚለው ኋልጡፍ (suffix) ተልኑሲን (electronics)፣ ተልኑሲናዊ (electronic) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። 
  9. ገልታ (neutral) እና እኑስ (particle) ከሚሉት ገልኑስ (neutron) የሚለውን የእኑስ ስያሜ እናገኛለን። 
  10. ለዚህ ስያሜ ምክኒያቱ እኑሱ ወንታ ጸውሪክ (positive charge) ወይም ሉንታ ጸውሪክ (negative charge) የሌለው አልጽውርክ እኑስ (uncharged particle) ማለትም ገልታ እኑስ (neutral particle) በመሆኑ ነው። 
  11. ገልኑስ (neutron) ከሚለው ገልኑሲት (neutrino) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
  12. ገልኑሲት (neutrino) ማለት አናሳዋ ገልኑስ እንደ ማለት ነው።  
  13.  ቀዳምኑስ (proton)፣ ተልኑስ (electron) እና ገልኑስ (neutron) በቀኒጥ (atom) ውስጥ የሚገኙ ወርክፎቻቸው (sizes) ከቀኒጥ ወርከፍ ያነሱ እኑሶች (particles) ስለሆኑ፣ ታሕትቀኒጥ እኑሶች (subatomic particles) ወይም ባጭሩ ቀኒጥኑሶች ይባላሉ።  
  14. ቀዳምኑስ (proton) እና ገልኑስ (neutron) ደግሞ በቀኒጥ ቡኒጥ (nucleus) ውስጥ ስለሚገኙ ቡኒጥኑሶች (nucleons) ይባላሉ። 
  15. በሌላ አባባል ቡኒጥኑስ (nucleaon) የቀዳምኑስ እና የገልኑስ የጋራ ወይም የወል ስም (common name) ነው ማለት ነው። 
  16. አሁንም በሌላ አባባል ቡኒጥኑስ (nucleaon) ስንል ቀዳምኑስ ወይም ገልኑስ ወይም ሁለቱንም ማለታችን ይሆናል ማለት ነው።

proton = ቀዳምኑስ
prototype = ቀዳምተ
electron = ተልኑስ
electronics = ተልኑሲን
neutron = ገልኑስ
neutrino = ገልኑሲት
subatomic particle = ታሕትቀኒጥ እኑስ፣ ቀኒጥኑስ
nucleon = ቡኒጥኑስ

ቶስመክ (Element) እና ቶስመካዊ (Elementary)

  1. መሠረት (foundation) ከሚለው ቃል መሠረታዊ (fundamental) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
  2. ቶኮ (አንድ) የሚለውን የኦሮምኛ ቃል ምስማክ (መሠረት) ከሚለው የግእዝ ቃል ጋር በማጣመር ቶስመክ (element)፣ ቶስመካዊ (elemental, elementary) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። 
  3. ቶስመካዊ ማለት የመጀመርያ ደረጃ ማለት ነው፣ ቶስመካዊ ሀርኪታ (elementary school)፣ ቶስመካዊ ሒሳብሲን (elementary mathematics) እንዲሉ። 

fundamental = መሠረታዊ
element = ቶስመክ
elementary (elemental) = ቶስመካዊ
elementary particle = ቶስመካዊ እኑስ

ኑርክን (Quantum) እና ንርከና (Quantization)

  1. እኑስ እና እርከን (ደረጃ) ከሚሉት ኑርከን (quantum) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
  2. የኑርከን (quantum) ግስ ሲረባ ነረከነ (quantize)፣ ንርክን (ንርኩን) [quantized]፣ ነርካኒ (ነርካኝ) [quantizing]፣ ንርከና (quantization)፣ ንርክነት፣ ንርካኔ፣ ንርካኖሽ እያለ ይሄዳል። 

quantum = ኑርከን
quantize = ነረከነ
quantization = ንርከና
quantum mechanics = ኑርከን ሐምሲን
quantum physics = ኑርከን ጉሲን
quantum particle = ኑርከን እኑስ ወይም ባጭሩ ኑርከኑስ
quantum electronics = ኑርከን ተልኑሲን
quantization of charge = የጸውሪክ ንርከና
quantization of energy = የጉልበት ንርከና
quantization of radiation = የጨረር ንርከና

ቶስመካዊ ጸውሪክ (Elementary Charge)

  1. ወደፊት በሌላ ጦማር ላይ እንደምንመለከተው በቤቶስ ስርካት (SI System) ላይ የጸውሪክ (charge) ቶካድ (unit) በፈረንሳዊው ጉሲነኛ ቻርለስ ኩሎምብ (Charles Coulomb) ስም ኩሎምብ (Coulomb) ሲባል፣ የሚወከለውም በፊደል C ነው።   
  2. የቀዳምኑስ ጸውሪክ (charge of proton) በኩሎምብ (coulomb) አንጻር ሲገለጽ በቅርበዛ (approximately) 1.6×10−19C1.6\times 10^{-19}C ይሆናል። 
  3. የቀዳምኑስ ጸውሪክ በፊደል e ይወከላል። በሌላ አባባልe=1.6×10−19Ce=1.6\times 10^{-19}C ነው።
  4. የተልኑስ ጸውሪክ (charge of electron) ከቀዳምኑስ ጸውሪክ (charge of proton) ጋር እቅጩን እኩል (exactly equal) እና ተቃራኒ (opposite) ነው። 
  5. ስለዚህም የቀዳምኑስ ጸውሪክ (charge of proton) e ሲሆን፣ የተልኑስ ጸውሪክ (charge of electron) ደግሞ -e ነው ማለት ነው። 
  6. የቀዳምስ ጸውሪክ (charge of proton) የሆነው e በጉሲን ውስጥ እጅግ መሠረታዊ (fundamental) የሆነ ናይባ (quantity) ነው። 
  7. በርግጥም በጉሲን ውስጥ ዋናወቹ መሠረታዊ ናይባወች ሁለት ሲሆኑ፣ እነሱም ይሄው የቀዳምኑስ ጸውሪክ (charge of proton) e እና የብርሃን ፍጥነት (speed of light) c ናቸው።
  8. በዚህም ምክኒያት የቀዳምኑስ ጸውሪክ (charge of proton) የሆነው e በልዩ ስም የጸውሪክ መሠረታዊ ቶካድ (fundamental unit of charge) ወይም ቶስመካዊ ቶካድ (elementary charge) በመባል ይታወቃል። 
  9. ለዚህ ስያሜ ምክኒያቱ ደግሞ በተፈጥሮ ውስጥ ሊነጸር እና ሊሰፈር (observed and measured) የሚችለው የመጨረሻው ትንሹ የጸውሪክ ቅንጣት e ስለሆነ ነው።

ጉተማወች (Integers)

  1. ወናብ እና ወታብ ቁጥሮች (Real & Complex Numbers) በሚለው ጦማር  ላይ በሰፊው እንደተመለከትነው፣ ቁጥሮች 1፣2፣ 3፣ 4፣ 5፣ … መቁጠርያ ቁጥሮች (counting numbers) ይባላሉ፣ ከጅምሩ የተፈጠሩት ለመቁጠር ነውና። 
  2. መቁጠርያ ቁጥሮች (counting numbers) ናርቲ ቁጥሮች (natural numbers) በመባልም ይታወቃሉ።
  3. ናርቲ (natural) ማለት ተፈጥሯዊ (የተፈጥሮ) ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው አርቲ (artificial) ማለትም ሰው ሠራሽ የሚለውን ቃል አካሄድ በመከተል ነው።
  4. ቁጥሮች 0፣ 1፣2፣ 3፣ 4፣ 5፣ … ድፍን ቁጥሮች (whole numbers) ይባላሉ።
  5. ስለዚህም የድፍን ቁጥሮች (whole numbers) ስብስብ (set) ከመቁጠርያ ቁጥሮች (counting numbers) ወይም ናርቲ ቁጥሮች (natural numbers) ስብስብ (set) የሚለየው ቁጥር ዳዶን (zero = 0) በመጨመሩ ብቻ ነው ማለት ነው።
  6. ቁጥሮች -5፣ -4፣ -3፣ -2፣ -1፣ 0፣ 1፣2፣ 3፣ 4፣ 5፣ … ጉተማ ቁጥሮች (integer numbers) ወይም ባጭሩ ጉተማወች (integers) ይባላሉ።
  7.  ጉተማ (integer) የሚለው ቃል የተገኘው ጉቱ (ማለትም ሙሉ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው። 

ነሻን (Fraction)፣ ፎክመን (Numerator) እና ደርመን (Denominator)

  1. ወናብ እና ወታብ ቁጥሮች (Real & Complex Numbers) በሚለው ጦማር  ላይ በሰፊው እንደተመለከትነው፣ ቁጥሮች p እና  q ጉተማወች (integers) ከሆኑ እና p ደግሞ አልዳዶ (non-zero) ከሆነ (ማለትም q ≠ 0  ከሆነ)፣ በመልክ p/q የሚገለጽ ማናቸውም ቁጥር ነሻን (fraction) ይባላል። 
  2. ነሻን (fraction) የሚለው ቃል የተገኘው ሸነሸነ ከሚለው ቃል ነው።
  3. በነሻን (fraction) p/q ላይ p ፎክመን (numerator) ሲባል፣ q ደግሞ ደርመን (denominator) ይባላል። 
  4. ፎክመን (numerator) የሚለው ቃል የተገኘው ፎቅ ከሚለው ቃል ሲሆን፣ ደርመን (denominator) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ ምድር ከሚለው ቃል ነው።   

የጸውሪክ ንርከና (Charge Quantization)

  1. በተፈጥሮ ውስጥ ጸውሪክ (charge) ሲባል ሊነጸርም (observed) ሆነ ሊቆነን (measured)የሚችለው በቶስመካዊ ጸውሪክ (elementary charge) አንጻር 0, ±1e, ±2e, ±3e, ±4e …   በሚል መልክ ብቻ ነው።
  2. 0, ±1e, ±2e, ±3e, ±4e …   ማለት ደግሞ የ e ጉተማ ብዜር (integeral multiple) ማለት ነው። 
  3. ስለዚህም በተፈጥሮ ውስጥ ጸውሪክ (charge) ሲባል ሊነጸርም ሆነ ሊሰፈር የሚችለው በቶስማካዊ ጸውሪክ ጉተማ ብዜር (integer multiple of elementary charge) መልክ ብቻ ነው ማለት ነው። 
  4. ይህ ማለት ደግሞ በተፈጥሮ ውስጥ የሚከሰት ጸውሪክ (charge) በቶስመካዊ ጸውሪክ (elementary charge) e አንጻር ሲገለጽ (1/2)e, (3/4)e, (5/7)e የመሳሰሉትን የሚመስሉ ነሻን እሴቶች (fractional values) ወይም ደግሞ 0.53e,  0.42 e,  0.75e የመሳሰሉትን የሚመስሉ አሴንታ እሴቶች (decimal values) ሊኖረው አይችልም ማለት ነው።
  5. በተፈጥሮ ውስጥ ጸውሪክ የሚከሰትው በቶስማካዊ ጸውሪክ ጉተማ ብዜር (integer multiple of elementary charge) መልክ ብቻ የመሆኑ ሐቅ (fact) የጸውሪክ ንርከና (charge quantization) ይባላል።  
  1. ጸውሪክ ንርከና (charge quantization) ማለት ጸውሪክ (charge) ሲባል በቅጽልጽለት (ቅጥልጥለት) መልክ የሚከሰት ቀጸላል (continuous) ሳይሆን፣ በቅንጣት ፍሬወች መልክ የሚከሰት ነጠላል (discrete) ወይም ፍርፋሪ ነው ማለት ነው።
  2. እያንዳንዷ የጽውሪክ ቅንጣት ፍሬ ደግሞ የጸውሪክ መሠረታዊ ቶካድ (fundamental unit of charge) ወይም ቶስመካዊ ቶካድ (elementary charge) የምትባለው e ናት።
  3. በሌላ አገላለጽ፣ ጸውሪክ ሲባል በቅጽልጸለት (ቅጥልጥለት) የሚከሰት ቀጻላል (continuous) ሳይሆን፣ በእኑስ እርከን ወይም ኑርከን (quantum) የሚከሰት ኑርከናዊ ወይም ኑርከናል (“quantumous”) ነው ማለት ነው።
  4. በዚህም ምክኒያት e ሌላኛው ስሟ የጸውሪክ ኑርከን (quantum of charge) ነው።
  5. በሌላ አመለካከት ግን፣ የጸውሪክ ኑርከን የሆነቸው e እሴት አጅግ በጣም አነሰተኛ በመሆኑ የተነሳ፣ ባብዛኛወቹ ግልጋሎቶች ላይ ጸውሪክ ኑርከናል (“quantumous”) ወይም ነጠላል (discrete) ሳይሆን ቀጸላል (continouus) እንደሆነ ተደረጎ ይወሰዳል። 
  6. የጸውሪክ ኑርከናልነት (“quantumness”)  ከፍተኛ ሚና የሚኖረው በቀኒጥ (atom) እና ከቀኒጥ ባነስ ደረጃ ያሉ የጥቃቅን አካሎች ጸውሪኮች በሚጤኑበት ሁኔታ ላይ ብቻ ነው።

እኑሶች (Particles)

  1. እኑስ (particle) ማለት አናሳ ማለት ሲሆን፣ ወርከፋቸው (size) እጅግ በጣም አነስተኛ የሆነ ጥቃቅን አካሎችን ለመግለጽ የሚያገለግል ቃል ነው።
  2. በንግሊዘኛ ቋንቋ ኦን (on) የሚለው ኋልጡፍ እኑሶችን (particles) ለመሰየም ያገለግላል። 
  3. ላብነት ያህል ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን፣ ኒውትሮን እና ፎቶን የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል።
  4. እኑስ (particle) ከሚለው ቃል በመነሳት “ኦን” ለሚለው የንግሊዘኛ ኋልጡፍ “ኑስ” የሚለውን ያማረኛ አቻ ፈጥሬለታለሁ።
  5. ወንታ (positive) እና ተልኑስ (electron) ከሚሉት ወተልኑስ (positron) የሚለውን ቃል እናገኛለን። 
  6. ወተልኑስ (positive) ማለት ተልኑስን (electron) የመሰለ ጸውሪኩ (charge) ግን የተልኑስን ጸውሪክ ተቃራኒ የሆነ፣ ማለትም ወንታ ጸውሪክ (positive charge) ያለው እኑስ ማለት ነው። 
  7. በሌላ አባባል ወተልኑስ (positron) ማለት ወንታ ተልኑስ (positive electron) ማለት ነው።  
  8. መሃል (መካከል) ከሚለው ቃል ማል (meso) የሚለውን ፊልጡፍ (prefix) እና ማልኑስ (meson) የሚለውን ስም እናገኛለን።
  9. ፓሌፍ ከሚለው የፊደል ፐ ስም እና ማልኑስ (meson) ከሚለው ፓሌፍ ማልኑስ ወይም ባጭሩ ፓልኑስ (pion, pi-meson) የሚለውን ስም እናገኛለን።
  10. ሙ ከሚለው ፊደል ሙኑስ (muon) የሚለውን ስም እናገኛለን።  
  11. ሙጫ (glue) ከሚለው ቃል ሙጫኑስ (gluon) የሚለውን ስም እናገኛለን።
  12. ዲክሶ (ከባድ) ከሚለው የወላይትኛ ቃል ዲክሶ (bary) እና ዲክሶኑስ (baryon) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። 
  13. ለምሳሌ ያህል ዲክሶማል (barycenter)፣ ዲክሶሉል (barysphere) ይሆናሉ።  
  14. ኦላ (የበላይ)  ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ኦላኑስ (hyperon) የሚለውን ስም እናገኛለን።
  15. ጥቅጥቅ (የተጠቀጠቀ) ከሚለው ጥቅኑስ (hadron) የሚለውን ስም እናገኛለን።  
  16. ቀላል ከሚለው ቀልኑስ (lepton) የሚለውን ስም እናገኛለን።
  17. ብርሃን ከሚለው ብራኑስ (photon) የሚለውን ስም እናገኛለን።
  18. በሕንዳዊው ጉሲነኛ ሳቴንድራ ቦዝ (Satyendra Nath Bose) ስም የተሰየመው እኑስ ቦዝኑስ (boson) ይባላል።
  19. በጣልያናዊው ጉሲነኛ ኤንሪኮ ፈርሚ (Enrico Fermi) ስም የተሰየመው እኑስ ፈርሚኑስ (fermion) ይባላል።
  20. ዋልታ (pole) ከሚለው ቃል ዋልታኑስ (polaron) እና ዋልትማኑስ (polariton) የሚሉትን ስሞች እናገኛለን።
  21. ሃይታ (ጆሮ) ከሚለው የወላይትኛ ቃል ፓታ (-phone) የሚለውን ኋልጡፍ (suffix) እና ፓታኑስ (phonon) የሚለውን ስም እናገኛለን።
  22. ለምሳሌ ያህል ሩቅ ከሚለው ቃል የተገኘውን ሩ (tele) የሚለውን ፊልጡፍ (prefix) ፓታ (phone) ከሚለው ኋልጡፍ (suffix) ጋር በማጣመር ሩፓት (telephone) የሚለውን ቃል እናገኛለን።  
  23. ጦፈ ማለትም ነደደ፣ ተቃጠለ ከሚለው ቃል ጦፈለ (excited) የሚለውን ግስ እና ጦፈልኑስ (exciton) የሚለውን ስም እናገኛለን።
  24. ለምሳሌ ያህል ጡፈላ ጉልበት (excitation energy) ማለት ለመጦፈል የሚያስፈልግ ጉልበት ማለት ነው።
  25. ማግኔት (magnet) ከሚለው ቃል ማግኑስ (magnon) የሚለውን ስም እናገኛለን። 
  26. ቁስበት (gravity) ከሚለው ቃል ቁስበትኑስ (graviton) የሚለውን ስም እናገኛለን።   
  27. ከጠፈር እየመነጩ ለብርሃን ፍጥነት በተቃረበ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት እየበረሩ ወደ ምድር የሚዘንቡ ከፍተኛ ጉልበታም እኑሶች (high energy particles) ጠፈርኑሶች (astroparticles) ወይም ካይጋ ጨረሮች (cosmic rays) ይባላሉ። 
  28. ጠፈርኑስ (astroparticle) የሚለው ቃል የተገኘው ጠፈር (astro) ከሚለው ፊልጡፍ (prefix) እና ኑስ (on) ከሚለው ኋልጡፍ (suffix) ነው።
  29. ካይጋ (cosmos) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ ማኪዮጋ (ማስማማት፣ ማስታረቅ) ከሚለው የወላይትኛ ቃል ነው።
  30. ጠፈርኑስ (astroparticle) እና ጠፈርሲን (astronomy) እንዳይምታቱብወት።  ጠፈርሲን (astronomy) ማለት የጠፈር ጥናት ማለት ነው።
  31. አሌፍ የፊደል አ ስም ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግም አልፍ አ ከሚለው ነው።  ይህም ቃል alpha የሚለውን የግሪክ ፊደል ስም ይተካልናል።
  32. አሌፍ (alpha) ከሚለው አልፋ እኑስ (alpha particle) ወይም ባጭሩ አሌፍኑስ የሚለውን ስም እናገኛለን።
  33. አሌፍ የሚለውን ስያሜ በመከተል የፊደልን በ ስም ባሌፍ እንለዋለን።  ይህም ቃል beta የሚለውን የግሪከኛ ፊደል ስም ይተካልና። 
  34. ባሌፍ (beta) ከሚለው ባሌፍ እኑስ (beta particle) ወይም ባጭሩ ባሌፍኑስ የሚለውን ስም እናገኛለን።
  35. ኑርከን (quantum) እና እኑስ (particle) ከሚሉት ኑርከን እኑስ (quantum particle) ወይም ባጭሩ ኑርከኑስ የሚለውን ስም እናገኛለን።
  36. የተለያዩ እኑሶችን በማቀናበር የሚፈጠርን እኑስ (particle) ቅንብር እኑስ (composite particle) ወይም ባጭሩ ቅንብርኑስ እንለዋለን።   

ውስጠታዊ (Intrinsic) እና ውጨታዊ (Extrinsic) ጠባዮች

  1. ውስጥ ከሚለው ውስጠታዊ (intrinsic)፣ ውጭ ከሚለው ደግሞ ውጨታዊ (extrinsic) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
  2. ውስጠታዊ ጠባይ (intrinsic property) ማለት የተፈጥሮ ጠባይ፣ ማለትም አብሮ የሚፈጠረና አብሮ የሚሞት ጠባይ ማለት ነው። 
  3. ስለዚህም ውስጠታዊ ጠባይ (intrinsic property) ተፈጥሯዊ ጠባይ ሊባልም ይችላል። 
  4. ለምሳሌ ያህል ቁሰት (mass) እና ጸውሪክ (charge) የተልኑስ (electron) ውስጠታዊ ጠባዮች (intrinsic properties) ወይም ተፈጥሯዊ ጠባዮች ናችው።
  5. ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ የተልኑስን ቁሰትና ጸውሪክ ከተልኑስ ነጥሎ ማውጣት ስለማይቻል፣ ማለትም ቁሰት የሌላት ተልኑስ ወይም ጸውሪክ የሌላት ተልኑስ ልትኖር ስለማትችል ነው። 
  6. በሌላ በኩል ደግሞ ውጨታዊ ጠባይ (extrinsic property) ማለት ከዘከብ (environment) ማለትም ካካባቢ ወይም ከሚገኙበት ሁኔታ (state) የሚመነጭ ጠባይ ማለት ነው።
  7.  ስለዚህም ውጨታዊ ጠባይ (extrinsic property) ዘከባዊ ጠባይ ሊባልም ይችላል። 
  8. ለምሳሌ ያህል የተልኑስ (electron) ፍጥነት (speed) እና ጉልበት (energy) ተልኑሷ ባለችበት ሁኔታ ላይ የሚመይፉ (depend) ማለትም የሚመኩ የተልኑስ ውጨታዊ ጠባዮች (extrinsic properties) ወይም ዘከባዊ ጠባዮች ናቸው።

intrinsic = ውስጠታዊ
intrinsic property = ውስጠታዊ ጠባይ፣ ተፈጥሯዊ ጠባይ
extrinsic = ውጨታዊ
extrinsic property = ውጨታዊ ጠባይ፣ ዘከባዊ ጠባይ

ኳርኮች (Quarks) እና ጣዕሞቻቸው (flavors)

  1. በንግሊዘኛ quark የሚባለውን ባማረኛም ኳርክ እንለዋለን። 
  2. የንግሊዘኛው ኳርክ የተገኘው ቋ፣ ቋ (croak) ከሚለው የጩኸት ስም ስለሆነ፣ ካማረኛውም ጋር አብሮ ይሄዳል።
  3. ኳርኮች (quarks) በቁስ (matter) ውስጥ የሚገኙ የመጨረሻወቹ መሠረታዊ እኑሶች (the most basic fundamental particles) ወይም ቶስመካዊ እኑሶች (elementary particles) ናቸው።
  4. በሌላ አባባል ኳርኮችን በመቀናበር የሚሠሩ ከኳርክ ያነሱ እኑሶች የሉም።
  5. የኳርክ ዓይነቶች (types) የኳርክ ጣዕሞችም (flavors) ይባላሉ። 
  6. የኳርክ ዓይነቶች ወይም ጣዕሞች ስድስት ሲሆኑ፣ እነሱም ቅናት (up)፣ ድፋት (down)፣ ራስ (top)፣ እግር (bottom)፣ ማራኪ (charm) እና ግሩም (strange) ይባላሉ። 

የኳርኮች ውስጠታዊ ጠባዮች (Intrinsic Properties)

  1. ኳርኮች ሲባሉ ቁልፍ የሆኑ አራት ውስጠታዊ ጠባዮች (intrinsic properties) ወይም ተፈጥሯዊ ጠባዮች አሏቸው። 
  2. እነሱም ቁሰት (mass)፣ ሌትሪክ ጸውሪክ (electric charge)፣ ቀለም ጸውሪክ (color charge) እና ሹረት (spin) ናቸው። 
  3. ሌትሪክ ጸውሪክ (electric charge) ባጭሩ ጸውሪክ (charge) ይባላል።
  4. ቀለም ጸውሪክ (color charge) ደግሞ ባጭሩ ቀለምሪክ ይባላል።

የኳርኮች ቁሰቶች (Masses)

  1. ቅናት ኳርክ (up quark) እና ድፋት ኳርክ (down quark) ከሁሉም ኳርኮች ያነሰ ቁሰት (mass) ያላቸው ኳርኮች ናቸው።
  2. የበለጠ ቁሳም (massive) የሆኑት ሌሎቹ ኳርኮች እኑስ ብስከት (particle decay) በሚባል ሂደት አማካኝነት ወደ ቅናት እና ድፋት ኳርኮች ይለወጣሉ።
  3. በዚህም ምክኒያት ቅናት ኳርክ እና ድፋት ኳርክ ርጉ (stable) ከመሆናቸውም በላይ በተፈጥሮ ውስጥ በብዛት የሚገኙት እነሱ ናቸው።
  4. በሌላ በኩል ደግሞ ራስ (top)፣ እግር (bottom)፣ ግሩም (strange) እና ማራኪ (charm) ኳርኮች የሚፈጠሩት በከፍተኛ ጉልበታም ግጨቶች (high energy collision) አማካኝነት ነው።
  5. ለምሳሌ ያህል ካይጋ ጨረሮች (cosmic rays) ወይም ጠፈርኑሶች (astroparticles) የሚባሉትን፣ ከጠፈር እየመነጩ ለብርሃን ፍጥነት በተቃረበ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር የሚዘንቡትን ከፍተኛ ጉልበታም እኑሶችን (high energy particles) የሚያካትቱ ግጭቶች ከፍተኛ ጉልበታም ግጭቶች (high energy collisions) ናቸው።
  6. በተጨማሪ ደግሞ በእኑስ ጠዳፊወች (particle accelerators) የተጠደፉ ከፍተኛ ጉልበታም እኑሶችን የሚያካትቱ ግጭቶች ከፍተኛ ጉልበታም ግጭቶች ናቸው።    

የኳርኮች ጸውሪኮች (Electric Charges)

  1. የኳርኮች ሌትሪክ ጸውሪኮች (electric charges) ባጭሩ ጸውሪኮች (charges) ይባላሉ።
  2. የኳርኮች ጸውሪኮች በቶስመካዊ ጸውሪክ (elementary charge) e አንጻር ሲገለጹ እሴታቸው (2/3)e ወይም (-1/3)e ነው።
  3. ስለዚህም የኳርኮች ጸውሪኮች በቶስመካዊ ጸውሪክ አንጻር ሲገለጹ ጉተማዊ (integral) ሳይሆኑ ነሻናዊ (fractional) ናቸው ማለት ነው።   
  4. በሌላ በኩል ደግሞ በጸውሪክ ንርከና (charge quantization) ደንብ መሠረት፣ በተፈጥሮ ውስጥ የሚነጸሩ ወይም የሚሰፈሩ ጸውሪኮች የቶስመካዊ ጸውሪክ ጉተማ ብዜሮች (integral multiples) መሆን አለባቸው፣ ማለትም ±1e, ±2e,  ±3e, …መሆን አለባቸው።   
  5. የኳርኮች ጸውሪኮች ጉተማዊ (integral) ሳይሆኑ ነሻናዊ (fractional) መሆናቸው ግን፣ የጸውሪክ ንርከናን (charge quantization) ደንብ አይጥስም።
  6. ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ በሚቀጥለው ክፍል ላይ በምንመለከተው የቀለም ተከርቸም (color confinement) መርሕ መሠረት፣ ኳርኮች ሲባሉ የሌትሪክ ጸውሪካቸውን ጉተማዊ በሚያደርጉ ጥምረቶች (combinations) ብቻ እንጅ በተናጠል (in isolation) መችም ቢሆን ሊከሰቱ ስለማይችሉ ነው።      
  7. የቅናት (up)፣ ራስ (top) እና ማራኪ (charm) ኳርኮች ጸውሪክ (2/3)e ነው። 
  8. በዚህም ምክኒያት ቅናት (up)፣ ራስ (top) እና ማራኪ (charm) ኳርኮች በወል ስም (common name) ቅናትመሰል ኳርኮች (up-type quarks) ወይም ቅናትመሳይ ኳርኮች ይባላሉ።  
  9. የድፋት (down)፣ እግር (bottom) እና ግሩም (strange) ኳርኮች ጸውሪክ (–1/3)e ነው። 
  10. በዚህም ምክኒያት ድፋት (down)፣ እግር (bottom) እና ግሩም (strange) ኳርኮች በወል ስም (common name) ድፋትመሰል ኳርኮች (down-type quarks) ወይም ድፋትመሳይ ኳርኮች ይባላሉ።  

አረንጓዴ (Green) ወይም ረንጓዴ 

  1. አረንጓዴ (green) በሚለው ቃል ላይ የመጀመርያው ፊደል “አ” የማያስፈልግ ትርፍ ነው።  ስለዚህም አመች በማይሆንበት ጊዜ ሊገደፍ (ማለትም ሊጣል) ይችላል።
  2. ያረንጓዴ ግስ ሲረባ አረነጎደ (ረነጎደ) [to green]፣ እርንጉድ (ርንጉድ) [greened]፣ አረንጓጅ (ረንጓጅ) [greening]፣ እርንጉደት (ርንጉደት) []greening፣ እርንጓዴ (ርንጓዴ)፣ እርንጓዶሽ እያለ ይሄዳል።
  3. ለምሳሌ ያህል የጦቢያ ርንጎዳ (the greening of Ethiopia)፣ ማለት ጦቢያን ማረንጎድ ማለትም ጦቢያን አረንጓዴ ማድረግ ማለት ነው።
  4. አረንጓዴ እና ቤት ከሚሉት ቃሎች ደግሞ አረንጌት (greenhouse) የሚለውን ቃል እናገኛለን።   

green = አረንጓዴ፣ ረንጓዴ
green (verb) = አረነጎደ፣ ረነጎድ
green-collar = አረንጓዴከሳድ፣ አረንጓዴለባሽ
green laser = አረንጓዴ በርጋኝ
green revolution =  አረንጓዴ አብዮት
greenhouse = አረንጌት
greenhouse effect = አረንጌት ጦስ

ኒል (Blue)

  1. ባማረኛ ኒል ማለት ሰማያዊ ቀለም (blue) ማለት ነው። 
  2. ሰማያዊ የሚለው የቀለም ስም በመጠኑ የተንዛዛ ከመሆኑም በላይ ሰማያዊ (heavenly) ማለትም የሰማይ ወይም ሰማይነክ (of heaven) ከሚለው ቃል ጋር ሊምታታ ይችላል። 
  3. በተጨማሪ ደግሞ ሰማያዊ የሚለው ቃል ለማርባት አይመችም። 
  4. ስለዚህም ኒል እና ሰማያዊ የሚሉትን እንዳመችነታቸው እየቀያየርን እንጠቀምባቸዋለን፣ ሰማያዊ የሚለውን ቃል ለቀለም ስም አለመጠቀም ተመራጭ ቢሆንም። 
  5. የኒል (blue) ግስ ሲረባ ነለመ፣ ንልም (ንሉም)፣ ነላሚ፣ ንለማ፣ ንልመት፣ ንላሜ፣ ንላሞሽ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም። 
  6. ነለመ ማለት ኒል ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ንልም (ንሉም) ማለት ደግሞ የተነለም ማለት ነው።
  7. ጨለመ እንደምንል ነለመ እንላለን።   
  8. ለምሳሌ ያህል ሰማዩ ነለመ (the sky turns blue) ማለት ሰማዩ ኒል ሆነ (ሰማዩ ሰማያዊ ሆነ) ማለት ነው። 

blue = ኒል፣ ሰማያዊ
blue (verb) = ነለመ
blueish (bluish) = ኒልማ
blue-collar = ኒልክሳድ፣ ኒለባሽ (ኒልለባሽ)
blue nile = ኒላባይ (ኒል አባይ)፣ ጥቁር ዐባይ
blue pages = ኒል ገጾች
blue sky = ኒል ሰማይ፣ ሰማያዊ ሰማይ
blue whale =  ኒላንበር (ኒል አንበር)
blueberry = ኒላጋም (ኒል አጋም)
blue-green = ኒላረንጓዴ፣ ኒልንጓዴ
blue-green algae = ኒልንጓዴ ዋረም
blueprint = ኒል እትም

ቀዳማይ ቀለሞች (Primary Colors)

  1. ቀዳማይ ቀለሞች (primary colors) ማለት ተቀላቅለው ሌሎቹን ሁሉንም ቀለሞች መሥራት የሚችሉ፣ ሌሎች ቀለሞች ግን ተቀላቅለው ሊሠሯቸው የማይችሉ መሠረታዊ ቀለሞች ማለት ነው። 
  2. ለምሳሌ ያህል ቀይ (red)፣ አረንጓዴ (green) እና ኒል (blue) ተዳማሪ ቀዳማይ ቀለሞች (additive primary colors) ናቸው፣ በተለያዩ መጠኖች እየተደመሩ ነጭን (white) ጨምሮ ሌሎች አልደማቅ ቀለሞችን (light colors) መሥራት ይችላሉና።
  3. ቀዳማይ ቀለሞች ተቀላቅለው የሚፈጥሯቸው ቀለሞች ካልዓይ ቀለሞች (secondary colors) ይባላሉ።
  4. ለምሳሌ ያህል አረንጓዴ (green) እና ኒል (blue) ሲቀላቀሉ ራሜ (cyan) የሚባለውን ካልዓይ ቀለም (secondary color) ይሠራሉ። 
  5. ራሜ (cyan) የሚለው ቃል የተገኘው ራማ (ሰማይ) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው።
  6. ቀይ (red) እና ኒል (blue) ሲቀላቀሉ ደግሞ ዲማ (magenta) የሚባለውን ካልዓይ ቀለም (secondary color) ይሠራሉ። 
  7. በኦሮምኛ ዲማ ማለት ቀይ ማለት ነው። 

primary color = ቀዳማይ ቀለም
additive primary color = ተደማሪ ቀዳማይ ቀለም
subtractive primary color = ተቀናሽ ቀዳማይ ቀለም
secondary color = ካልዓይ ቀለም

የኳርኮች ቀለምሪኮች  (Color Charges)

  1. የኳርኮች ቀለም ጸውሪኮች (color charges) ባጭሩ ቀለምሪኮች (colorcharges) ይባላሉ።
  2. ኳርኮች በሌክትሮማኔታዊ ግሳቦች (electromagnetic forces) የሚገሳሰቡት በሌትሪክ ጸውሪካቸው (electric charges) ሳቢያ እንደሆነ ሁሉ፣ ከዚህ በታች በምንመለከተው ብርቱ ቡኒጣዊ  ግሳብ (strong nuclear force) በሚባለው ግሳብ የሚገሳሰቡት ደግሞ በቀለም ጸውሪካቸው (color charges) ሳቢያ ነው።
  3. ሌትሪክ ጸውሪኮች (electric charges) ሁለት ዓይነት ናቸው።
  4. እነዚህም ሁለት ዓይነት ሌትሪክ ጸውሪኮች ወንታ ጸውሪክ (postive charge) እና ሉንታ ጸውሪክ (negative charge)።
  5. በሌላ በኩል ደግሞ ቀለም ጸውሪኮች  (color charges) ወይም ቀለምሪኮች ሦስት ዓይነት ናቸው።
  6. እነዚህም ሦስት ዓይነት ቀለም ጸውርኮች (color charges) ወይም ቀለምሪኮች በቀዳማይ ቀለሞች (primary colors) ስም ቀይ (red)፣ አረንጓዴ (green) እና ኒል (blue) በመባል ይታወቃሉ። 
  7. የኳርኮች ቀለም ጸውሪኮች (color charges) ቀለሞች ቢባሉም ቡናማ፣ ተልብማ፣ ገብስማ እያለን ከምንጠራቸው ቀለሞች ከሚባሉት ነገሮች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላቸውም።
  8. የኳርኮች ቀለም ጸውሪኮች (color charges) ቀለሞች የተባሉትና ቀይ፣ አረንጓዴ እና ኒል የሚባሉ ስያሜወች የተሰጣቸው የቀለም ጸውሪክ ጠባይ ከቀዳማይ ቀለሞች ጠባይ ጋር በተወሰነ ደረጃ ተመሳሳይ በመሆኑ ምክኒያት ብቻ ነው።
  9. ኳርኮች ሲባሉ ቁሰት (mass) እና ሌትሪክ ጸውሪክ (electric charge) ሁልጊዜም እንዳላቸው፣ ቀለምጸውሪክ (color charge) ሁልጊዜም አላቸው፣ ውስጠታዊ ጠባያቸው (intrinsic property) ነውና። 
  10. ኳርኮች በመጣመር የሚፈጥሩት እኑስ (particle) ግን ቀለም ጸውሪክ የሌለው ነጭ ሊሆን ይችላል። 
  11. ለምሳሌ ያህል ቀይ ፣ አረንጓዴና ኒል ኳርኮች በመጣመር የሚሠሩት እኑስ (particle) ቀለምጸውሪክ አይኖረውም።  በዚህም ምክኒያት እኑሱ ቀለምቢስ (colorless) ወይም ቀለምገልታ (color-neutral) ነው ይባላል። 

ቅንብረት እና ቅንብራ (composing) 

  1. አቀናበረ የሚለውን ቃል ለማርባት ይመች ዘንድ ቀነበረ እንለዋለን። 
  2. ይህም ቃል compose የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
  3. የቀነበረ ግስ ሲረባ ቀነበር (compose)፣  ቅንብር (ቅንቡር) [composed, composite]፣ ቀንባሪ (composing, composer)፣ ቅንበራ (composing)፣ ቅንብረት፣ ቅንባሬ፣ ቅንባሮሽ እያለ ይሄዳል።
  4. \ቅንብር/ (composite) ማለት የተቀናበረ ወይም የቅንብረት ውጤት ማለት ነው። 
  5. ለምሳሌ ያህል ቅንብር እኑስ (composite particle) ወይም ባጭሩ ቅንብርኑስ ማለት በተለያዩ እኑሶች ቅንብረት የተፈጠረ እኑስ ማለት ነው።
  6. የማይጠበቀው \ቅንብር/ ትርጉሙ የተቀናበረ ማለት ሲሆን፣ የሚጠብቀው /ቅንብር\ ደግሞ ማቀናበር ማለት ነው።  

compose = ቀነበረ
composite = \ቅንብር/ (ሲነበብ አይጠብቅም)
composite number = ቅንብር ቁጥር
composite function = ቅንብር ቀዘድ
composite particle = ቅንብር እኑስ

ተከርቸም እና ክርቸማ (Confinement) 

  1. ባማረኛ ከረቸመ ማለት አሰረ፣ አፍኖ፣ ሸፍኖ ያዘ ማለት ነው። 
  2. ይህም ቃል confine የሚለውን የንግሊዛኛ ቃል ይተላልናል።
  3. የከረቸመ ግስ ሲረባ ከረቸመ (confine)፣ ክርችም (ክርቹም) [confined]፣ ከርቻሚ (confining)፣ ክርቸማ (confining, confinement)፣ ክርችመት፣ ክርቻሜ፣ ክርቻሞሽ እያለ ይሄዳል። 
  4. ተከርቸም (confinement) ማለት የመከርቸም ሁኔታ ማለት ነው፣ ተከርቸም ገባ እንዲሉ። 

confine = ከረቸመ
confinement (confining) = ክርቸማ
confinement (state) = ተከርቸም

ቀለም ተከርቸም (Charge Confinement)

  1. ኳርኮች በቅንብር (composite) መልክ እንጅ በተናጠል (in isolation) ሊከሰቱ አይችሉም። 
  2. ይህም ሐቅ የኳርኮች ቀለም ተከርቸም (charge confinement) ይባላል። 
  3. ኳርኮች በመቀናበር የሚሠሯቸው ቅንብር እኑሶች (composite particles) ጥቅኑሶች (hadrons) ይባላሉ።
  4. ጥቅኑስ (hadron) የሚለው ቃል የተገኘው ጥቅጥቅ እና እኑስ ከሚሉት ቃሎች ነው።
  5. ዋናወቹ ጥቅኑሶች (hadrons) በቀኒጥ (atom) ቡኒጥ (nucleus) ውስጥ የሚገኙት ቀዳምኑስ (proton) እና ገልኑስ (neutron) ናቸው። 
  6. ቀዳምኑስ (proton) የሁለት ቅናት ኳርኮች (two up quarks) እና ያንድ ድፋት ኳርክ (one down quark) ቅንብር (composite) ነው።
  7. ገልኑስ (neutron) ደግሞ የሁለት ድፋት ኳርኮች (two down quarks) እና ያንድ ቅናት ኳርክ (one up quark) ቅንብር (composite) ነው።

ሦስቱ የቁስ (Matter) ቶስመካዊ እኑሶች (Elementary Particles)

  1. ሁሉም የተለምዶ ቁስ (ordinary matter) የተሠራው ከቀኒጦች (atoms) ነው።
  2. ቀኒጦች የተሠሩት ደግሞ ከቀዳምኑሶች (protons)፣ ግልኑሶች (neutrons) እና ተልኑሶች (electrons) ነው።
  3. ቀዳምኑሶች (protons) እና ገልኑሶች (neutrons) የተሠሩት ደግሞ ቅናት ኳርኮች (up quarks) እና ድፋት ኳርኮች (down quarks) ከሚባሉት ቶስመካዊ እኑሶች (elementary particles) ነው።
  4. ተልኑስ (electron) ደግሞ ከሌላ እኑስ ያልተሠራች በራሷ ቶስመካዊ እኑስ (elementary particle) ናት።
  5. በሌላ አባባል በመቀናበር ተልኑስን የሚሠሩ ከተልኑስ ያነሱ እኑሶች የሉም።     
  6. ስለዚህም ሁሉም የተለምዶ ቁስ (ordinary matter) የተሠራው ከሶስት ቶስመካዊ እኑሶች (three elementary particles) ሲሆን፣ እነሱም ቅናት ኳርክ (up-quark)፣ ድፋት ኳርክ (down-quark) እና ተልኑስ (electron) ናቸው ማለት ።

ሰበብ (Cause)፣ ጦስ (Effect) እና ፋርዳ ጦስ (Net Effect)

  1. ባማረኛ ሰበብ (ሳቢያ) ማለት ምክኒያት ማለት ነው ሰበበኛ እንዲሉ ምክኒያተኛ ሊሉ። 
  2. ሰበበ ማለት ደግሞ ምክኒያት ፈጠረ ማለት ነው፣ አሳባበ ምክኒያት ፈጠረ ሊሉ።
  3. ይህም ሰበበ የሚል ቃል cause የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
  4. ግሱም ሲረባ ሰበበ (to cause)፣ ስብብ (ስቡብ) [caused]፣ ሰባቢ (causing)፣ ሰበባ (causing, casuation)፣ ስባቤ፣ ስባቦሽ እያለ ይሄዳል።
  5. ባማረኛ ጦስ ማለት መዘዝ ማለት ነው፣ ጦሴን አታብዛው እንዲሉ፣ መከራየን አታብዛው፣ ችግሬን አታክፋው ሊሉ። 
  6. ይህም ጦስ የሚል ቃል effect የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካለናል። 
  7. ግሱም ሲረባ ጦሰሰ (to effect, effectuate)፣ ጡስስ (effected, effectuated)፣ ጦሳሲ (ጦሳሽ) [effecting, effectuating, effective]፣ ጡሰሳ (effecting, effectuation)፣ ጡሳሴ፣ ጡሳሶሽ እያለ ይሄዳል። 
  8. ባማረኛ ፋርዳ ማለት የተጣራ ማለት ነው፣ ፋርዳ ትርፍ እንዲሉ የተጣራ ትርፍ ሊሉ። 
  9. ይህም ፋርዳ የሚል ቃል net የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል። 
  10. ፋርዳ ጦስ (net effect) ማለት የተጣራ ጦስ ወይም የጦሶች አጠቃላይ ውጤት እንደ ማለት ነው። 

cause  = ሰበብ፣ ሳቢያ
effect = ጦስ
net = ፋርዳ
net effect = ፋርዳ ጦስ

ግሳብ (Force)

  1. ግፋ (push) እና ሳብ (pull) ከሚሉት ግሳብ (force) የሚለውን ቃል እናገኛለን። 
  2. ግሳብ (force) ማለት መገፋት (to push) ወይም መሳብ (to pull) ማለት ነው።
  3. ግሱም ሲረባ ገሰበ (to force)፣ ግስብ (ግሱብ) [forced]፣ ገሳቢ (forcing)፣ ግሰባ (forcing)፣ ግስበት፣ ግሳቤ፣ ግሳቦሽ እያለ ይሄዳል፣ ግሳቡ ገሰበ እንዲሉ።
  4. በጉሲናዊ (physics) ብያኔው ግሳብ (force) ማለት መገፋት (push, repel) ወይም መሳብ (pull, attract) የሚችል ማናቸውም ሰበብ (cause) ማለት ነው።   
  5. የመግፋት ወይም የመሳብ ውጤት በመግፋቱ ወይም በመሳቡ ጥንካሬ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ባቅጣጫውም ላይ ይመይፋል (depened) ማለትም ይመካል። 
  6. ስለዚህም ግሳብ (force) ሲባል የራሱ ብክረት (magnitude) እና አቅጣጫ ያለው፣ በፈላስተኖች ድመራ (vector addition) ዘዴወች የሚደመር ፍላስተን ናይባ (vector quantity) ነው ማለት ነው።

ኑሃት (Range)

  1. በግእዝ ኑሃት ማለት ርዝመት ማለት ነው። 
  2. ይህም ቃል range የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
  3. ኑሃት ማለት በመነሻና በመድረሻ ያለ ርርቀት እንደ ማለት ነው። 

range = ኑሃት
short range = አጭር ኑሃት
long range = ረዥም ኑሃት
medium range =  መካከለኛ ኑሃት
range finder = ኑሃትለኪ፣ ኑሃታሳሽ (ኑሃት አሳሽ)
ranger = ኑሃተኛ፣ ኑሃች

አራቱ መሠረታዊ ግሳቦች (The Four Fundamental Forces)

  1. በተፈጥሮ ውስጥ የሚገኙት መሠረታዊ ግሳቦች (fundamenta forces) አራት ብቻ ናቸው።
  2. በተፈጥሮ ውስጥ የሚገኙት ሌሎቹ ሁሉም ግሳቦች የነዚህ አራት መሠረታዊ ግሳቦች ጥምረቶች (combinations) ወይም ግውጸቶች (manifestations) ማለትም የሚከሰቱባቸው መልኮች ናቸው። 
  3. እነዚህም አራት መሠረታዊ ግሳቦች ቁስበታዊ ግሳብ (gravitational force)፣ ሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ (electromagnetic force)፣ ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) እና ደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (weak nuclear force) ይባላሉ።

ቁስበታዊ ግሳብ (Gravitational Force)

  1. ቁስበት (gravity) የሚለው ቃል የተገኘው ቁሰት (mass) እና ስበት ከሚሉት ነው።
  2. የቁስበታዊ ግሳብ (gravitational force) መንስዔው ቁሰት (mass) ነው። 
  3. ቁሰት ያላቸው አካሎች ሁሉ በቁስበታዊ ግሳብ ይገሳሰባሉ።
  4. በብክረት (magnitude) ማለትም በጥንካሬ (strength) አንጻር፣ ቁስበታዊ ግሳብ ካራቱ መሠረታዊ ግሳቦች ዠደካማ (weakest) ማለትም የመጨረሻው ደካማ ግሳብ ነው። 
  5. በዚህም ምክኒያት ቁስበታዊ ግሳብ ባካሎች ድርረጋ (interaction) ላይ ጦስ (effect) የሚኖረው፣ ቢያንስ አንዱ አካል እጅግ ከፍተኛ ቁሰት (mass) ያለው ምድርን፣ ጨረቃን፣ ፀሐይንና ከዋክብትን የመሰለ ጠፈርሲናዊ አካል (astronomical object) ከሆነ ብቻ ነው።
  6. ስለዚህም ቁስበታዊ ግሳብ ዐብዩን ሚና (main role) የሚጫወተው በሁንዳ ትልቁ ስዕል (big picture of the universe) ወይም ጠፈርሲናዊ ስዕል (astronomical picture) ላይ ብቻ ነው ማለት ነው።
  7. ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ ጠፈረሲናዊ አካሎች (astronomical objects) ሲባሉ፣ እያንዳንዳቸው በጥቅሉ ሲታዩ ፋርዳ ጸውሪካቸው (net charge) ከሞላ ጎደል ዳዶ (zero = 0) የሆነ ገልታ አካሎች (neutral objects) በመሆናቸው ሳቢያ በሌክትሮማግኒታዊ ግሳቦች (electromagnetic forces) ሊገሳሰቡ ስለማይችሉ ነው።   በብርቱ (strong) ወይም በደካማ (weak) ቡኒጣዊ ግሳቦች (nuclear forces) እንዳይገሳሰቡ ደግሞ ርርቀታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ነው። 
  8. ቁስበታዊ ግሳብ (gravitational force) ይስባል (attract, pull) እንጅ አይገፋም (repel, push)።  ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ የቁስበት (mass) እሴት ሁሌንም ወንታ (always positive) ስለሆነ ብቻ፣ ማለትም ገልታ ቁስበት (negative mass) ስለሌለ ነው።
  9. የቁስበታዊ ግሳብ (gravitational force) ኑሃት (range)፣ ማለትም ቁስበታዊ ግሳብ ሊገስብ የሚችልበት ርርቀት (distance) ኢወዳኢ (infinite) ነው። 
  10.  በሌላ አባባል አካሎች በማናቸውም ረቀት ቢራራቁም በቁስበታዊ ግሳብ ይገሳሰባሉ (ይሳሳባሉ) ማለት ነው፣ ምንም እንኳን ርርቀታቸው እየጨመረ ሲሄድ ግስስበታቸው (መሳሳባቸው) እየቀነሰ ቢሄድም።
  11. ቁበስታዊ ግሳብ የኒውተን ሁንዳዊ የቁስበት ሕግ (Newton’s law of universal gravitation) ወይም ባጭሩ የቁስበት ሕግ (the law of gravitation) በሚባል፣ ለሁሉም ቁስት አካሎች (massed objects) ማለትም ቁሰት ያላቸው አካሎች በሚያገለግል ሁንዳዊ ሕግ (universal law) /ይገዛል\።   

ሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ (Electromagnetic Force)

  1. ሌክትሮማግኔት (electromagnet) የሚለው ቃል የተገኘው ሌክትሮ (electro) ከሚለው ፊልጡፍ (prefix) እና ማግኔት (magnet) ከሚለው ቃል ነው።
  2. ሌክትሮ (electro) የሚለው ፊልጡፍ (prefix) የተገኘው ደግሞ ኤልክትሮ የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ለማርባት ይመች ዘንድ በማሳጠር ነው።
  3. የሌክትሮማገኒታዊ ግሳብ (electromagnetic force) መንስዔው ሌትሪክ ጸውሪክ (electric charge) ወይም ባጭሩ ጸውሪክ (charge) የሚባለው ናይባ (quantity) ነው።   
  4. ጸውሪክ ያላቸው አካሎች ሁሉ በሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ ይገሳሰባሉ።
  5. በብክረት (magnitude) ማለትም በጥንካሬ (strength) አንጻር ሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ  ከብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ይገኛል። 
  6. ለምሳሌ ያህል በሁለት ቀዳምኑሶች (protons) መካከል ያለው ሌክትሮማግኒታዊ  ግሳብ (electromagnetic force) በቀዳምኑሶቹ መካከል ካለው ቁስበታዊ ግሳብ (gravitational force) 1036 ግደማ ይበልጣል። 
  7. ስለዚህም ሌክትሮማገኔታዊ ግሳብ ባለበት ሁኔታ ላይ ቁስበታዊ ግሳብ እንደሌለ ሊቆጠር ይችላል ማለት ነው።  
  8. ባጠቃላይ አነጋገር ደግሞ በቀዳምኑስ (proton)፣ ተልኑስ (electron)፣ ቀኒጥ (atom) እና ፀምሪቅ (molecule) ደረጃ ያሉ ጥቃቅን አካሎችን በተመለከተ፣ ቁስቶቻቸው (masses) እጅግ አናሳወች ስለሆኑ በመካከላቸው ሊኖር የሚችለው ቁስበታዊ ግሳብ (gravitational force) እጀግ አናሳ ነው።  ስለዚህም እነዚህ ጥቃቅን አካሎች ሙሉ በሙሉ የሚገሳሰቡት በጸውሪካቸው (charges) አማካኝነት በሌትክትሮማግኔታዊ ግሳብ (electromagnetic force) ነው ማለት ይቻላል። 
  9. ስለዚህም ሊክትሮማግኔታዊ ግሳብ ዐብዩን ሚና (main role) የሚጫወተው በሁንዳ ትንሹ ስዕል (small picture of the universe) ወይም ቀኒጣዊ ስዕል (atomic picture) ላይ ብቻ ነው ማለት ነው።
  10. ሊክትሮማግኔታዊ ግሳብ (gravitational force) ሊስብም (attract, pull) ሊገፋም (repel, push) ይችላል። 
  11. ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ የጸውሪክ (charge) እሴት እንደ ቁሰት (mass) እሴት ሁልጊዜም ወንታ (always positive) ሳይሆን፣ ወንታ (positive) ወይም ሉንታ (negative) ሊሆን ስለሚችል ነው። 
  12. የሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ (electromagnetic force) ኑሃት (range)፣ ማለትም ሊክትሮማግኔታዊ ግሳብ ሊገስብ የሚችልበት ርርቀት (distance) ኢወዳኢ (infinite) ነው። 
  13. በሌላ አባባል አካሎች በማናቸውም ረቀት ቢራራቁም በሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ ይገሳሰባሉ (ይሳሳባሉ ወይም ይገፋፋሉ) ማለት ነው፣ ምንም እንኳን ርርቀታቸው እየጨመረ ሲሄድ ግስስበታቸው (መሳሳባቸው ወይም መገፋፋታቸው) እየቀነሰ ቢሄድም።
  14. ሊክትሮማግኔታዊ ግሳብ የሎረንዝ የግሳብ ሕግ (Lorentz Force Law) በሚባል፣ ለሁሉም ጽውርክ አካሎች (charged objects) ማለትም ጸውሪክ ያላቸው አካሎች በሚያገለግል ሁንዳዊ ሕግ (universal law) ይገዛል።   
  15. የሎረንዝ ግሳብ (Lorentz foce) ሌትሪካዊ ምንዝር (electric component) እና ማግኔታዊ ምንዝር (magnetic component) የሚባሉ ሁለት ምንዝሮች (components) ወይም ዘርፎች አሉት። 
  16. የሎረንዝ ግሳብ (Lorentz force) ሌትሪካዊ ምንዝር (electric component) ኩሎምብ ግሳብ (Coulomb force) ሲባል፣ ማግኔታዊ ምንዝር  (magnetic component) ደግሞ ማግኔታዊ ግሳብ (magnetic force) ይባላል።
  17. ኩሎምብ ግሳብ (Coulomb force) የኩሎምብ ሕግ (Coulomb’s Law) በሚባል በፈንሳዊው ጉሲነኛ ቻርለስ ኩሎምብ (Charles Coulomb) ስም በተሰየመ አጠቃላይ ሕግ /ይገዛል\።   

ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (Strong Nuclear Force)

  1. ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) ቀዳምኑስን (proton) እና ገልኑስን (neutron) በማስተሳሰር ቡኒጥ እንዲሰሩ (create nucleus) የሚያደርጋቸው ግሳብ (force) ነው።
  2. ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) አብዛኛውን ጊዜ ባጭሩ ቡኒጣዊ ግሳብ (nuclear force) ይባላል።
  3. ቀዳምኑሶች (protons) እጅግ በጣም አናሳ በሆነው የቀኒጦች ቡኒጥ (nucleus) ውስጥ እጅግ በጣም የተቀራረቡ ስለሆኑ፣ በሌትሪካዊ ጸውሪካቸው (electric charges) ሳቢያ የሚገፋፉበት ሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ (electromagnetic force) እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። 
  4. ስለዚህም፣ ቀዳምኑሶች (protons) ቡኒጥ (nucleus) ውስጥ እጅግ በጣም ተቀራርበው ይኖሩ ዘንድ፣ ቀዳምኑሱቹን የሚያስተሳስራቸው ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ ቀዳምኑሶቹ ከሚገፋፉበት ሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ መብለጥ አለበት።
  5. በርግጥም፣ የብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ ብክረት (magnitude) ማለትም ጠንካራነት ከሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ ብክረት 100 ጊዜ ገደማ ይበልጣል።
  6. በብክረት (magnitude) ማለትም በጥንካሬ አንጻር ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ ከሁሉም መሠረታዊ ግሳቦች በመብለጥ ባንደኛ ደረጃ ይገኛል። 
  7. ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) የሚከተሉት ጸባዮች አሉት።
    • መጠኑ በቅርበዛ (approximately) በ 0.7 ሃምጢኖሜትር (femtometer)  እና በ 2.5 ሃምጢኖሜትር (femtometer)  መካከል በሆነ ርርቀት ላይ ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) ሳቢ ግሳብ (attractive force) ነው።  የቀዳምኑሶችን (protons) ሌትርካዊ መገፋፋት (electrical repulsion) በመቋቋም ቡኒጥ ውስጥ እጅግ በጣም ተቀራርበው እንዲኖሩ የሚያደርጋቸው ይህ ሳቢ ግሳብ ነው። 
    • ከ 0.7 ሃምጢኖሜትር (femtometer) ባነሰ ርርቀት ላይ ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) ገፊ ግሳብ (repulsive force) ነው።  ቡኒጥኑሶች (nucleons) ማለትም ቀዳምኑሶች (protons) እና ገልኑሶች (neutrons) ተጨፈላልቀው ወደ አንድ  ነጥብ እንዳይመሽኩ (collapse) የሚያደረጋቸው ይህ ገፊ ግሳብ ነው።  በሌላ አባባል እጅግ በጣም አንሳ የሆነው የቡኒጥ (nucleus) ወርከፍ (size) ማለትም መጠን ጭራሹን ዳዶ (zero) እንዳይሆን የሚያደርገው ይህ ገፊ ግሳብ ነው። 
    • ከ 2.5 ሃምጢኖሜትር (2.5 femtometer) በበለጠ ርርቀት ላይ የብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) ብክረት (magnitude) ማለትም ጥንካሬ ከሞላ ጎደል ዳዶ (zero) ነው። 
    • ስለዚህም የብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ ኑሃት (range) 2.5 ሃምጢኖሜትር (emtometer) ነው ማለት ነው። 
    • በሌላ አባባል ቡኒጥኑሶች (nucleons) በብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ የሚገሳሳቡት ርርቀታቸው ከ 2.5 ሃምጢኖሜትር (femtometer) ያነሰ ከሆነ ብቻ ነው ማለት ነው። 
    • ስለዚህም የብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ ሚና (role) ያለው ቡኒጥ ውስጥ ብቻ ነው ማለት ነው።  ቡኒጣዊ የተባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው። 
  8. በተጨማሪ ደግሞ ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) ኳርኮችን (quarks) በማስተሳሰር ቀዳምኑሶችን (protons) እና ገልኑሶችን (neutrons) የመሳሰሉ ጥቅኑሶችን (hadrons) እንዲሠሩ የሚያደርጋቸው ግሳብ ነው።
    • በዚህ ሁኔታ ላይ ደግሞ ግሳቡ ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) መባሉ ቀርቶ ባጭሩ ብርቱ ግሳብ (strong force)  ወይም ብርቱ ድርረጋ (strong interaction) ይባላል። 
  9. ኳርኮች በብርቱ ግሳብ (strong force) የሚገሳሰቡት፣ በቀለም ጸውሪካቸው (color charge) አማካኝነት ሙጫኑሶች (gluons) የሚባሉትን አኑሶች  (particles) በቅጽለት (constantly) ማለትም ያለማቋረጥ በመሰጣጠት (exchange) ነው።

ዙላ  (Chrome)

  1. ዙላ (ቀስተ ደመና) ከሚለው የወላይትኛ ቃል ዙላ (chrome) የሚለውን ቃል እንዲሁም ፊልጡፍ (prefix) እናገኛለን። 
  2. ዙላ (chrome) ማለት ቀለም እንደ ማለት ነው። 
  3. ለምሳሌ ያህል ሃዴዙላ (monochromatic) ማለት ባለ አንድ ቀለም ማለት ሲሆን፣ ክሌዙላ (dichromatic) ማለት ደግሞ ባለ ሁለት ቀለም ማለት ነው።  
  4. ማትዙላ (polychromatic) ማለት ደግሞ ሁለትና ከዚያ በላይ ቀለሞች ያሉት ማለት ነው። 

chromatic (achromatic)  = ዙላ፣ አልዙላ
chromatic aberration = ዙላ ቡዘት
achromatic lens = አልዙላ ምስሮ
achromatic doublet = አልዙላ ክሌቻን
chromatology (chromatics) = ዙላሲን
monochromatic = ሃዴዙላ
dichromatic = ክሌዙላ
polychromatic = ማትዙላ

ኑርከን ዙላሑሲን  (Quantum Chromodynamics)

  1. ዙላ (chromo) የሚለውን ፊልጡፍ (prefix) ሑሲን (dynamics) ከሚለው ጋር በማጣመር ዙላሑሲን (chromodynamics) የሚለውን ቃል እናገኛለን።   
  2. ኑርከን (quantum) እና ዙላሑሲን (chromodynamics) ከሚሉት ደግሞ ኑርከን ዙላሑሲን (quantum chromodynamics) የሚለውን ስያሜ እናገኛለን።
  3. ኑርከን ዙላሑሲን (quantum chromodynamics) ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) እና ደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (weak nuclear force) የሚጠኑበት፣ ኑርከን ጉሲንን (quantum physics) እና ሑሲንን (dynamics) የሚያጣምር የጉሲን ዘርፍ (branch of physics) ነው።
  4. ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ እንደ ቁስበታዊ ግሳብ (gravitaitonal force) እና ሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ (electromagnetic force) እጥር፣ ምጥን ያለ ሒሳብሲናዊ ቀመር (mathematical formula) የለው።
  5. ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ ብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ እንደ ቁስበታዊ ግሳብ እና ሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ በድርብርብት መርሕ (superposition principle) መሠረት በመደራረብ  (ማለትም ላይ በላይ በመከመር) የሚደመር ቄጠማ ግሳብ (linear force) ሳይሆን፣ አልቄጠማ ግሳብ (non-linear force) በመሆኑ ነው።

አሌፍ (Alpha)፣ ባሌፍ (Beta) እና ጋሌፍ (Gamma)

  1. አሌፍ የፊደል አ ስም ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግም አልፍ አ ከሚለው ነው። 
  2. ይህም አሌፍ የሚል ቃል alpha የሚለውን የግሪክ ፊደል ስም ይተካልናል።
  3. አሌፍ የሚለውን ስያሜ በመከተል የፊደልን በ ስም ባሌፍ እንለዋለን። 
  4. ይህም ባሌፍ የሚል ቃል beta የሚለውን የግሪከኛ ፊደል ስም ይተካልና።
  5. እንዲሁም አሌፍ የሚለውን ስያሜ በመከተል የፍደልን ገ ስም ጋሌፍ እንለዋለን። 
  6. ይህም ጋሌፍ የሚል ቃል gamma የሚለውን የግሪክ ፍደል ስምይ ይተካልናል። 

alpha = አሌፍ
alpha particle = አሌፍኑስ
alpha ray = አሌፍ ጨረር
beta = ባሌፍ
beta particle = ባሌፍኑስ
beta ray = ባሌፍ ጨረር
betatron = ባሌፍጠዳፊ፣ ተልኑስጠዳፊ፣ ባሌፍትሮን
gamma = ጋሌፍ
gamma ray = ጋሌፍ ጨረር

ብስከት (Decay)

  1. ባማረኛ በሰከ ወይም በሸከ ማለት በተከ፣ ቆረጠ፣ በጠሰ ማለት ነው፣  በሸካከተ እንዲሉ በጫጨቀ ሊሉ። 
  2. ይህም በሰከ የሚል ቃል decay የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
  3. የበሰከ ግስ ሲረባ በሰከ (to decay)፣ ብስክ (ብሱክ) [decayed]፣ በሳኪ (decaying)፣ ብሰካ (decaying)፣ ብስከት፣ ብሳኬ፣ ብሳኮሽ እያለ ይሄዳል።
  4. ብስከት (decay, decaying) ማለት መበሰክ ማለት ሲሆን፣ ብሳክ ወይም ብስካት ማለት ደግሞ የበሰከ ነገር ማለት ነው።

decay (verb) = በሰከ
decay (decaying) = ብሰካ፣ ብስከት
decay (decayed object) = ብሳክ፣ ብስካት
alpha decay = አሌፍ ብስከት
beta decay =  ባሌፍ ብስከት
beta plus decay = ባሌፍ ወንታ ብክስከት
beta minus decay = ባሌፍ ሉንታ ብስከት
gamma decay = ጋሌፍ ብስከት

ረጫሪ (Radioactive) እና ርጨራ (Radioactivity)

  1. ረጨ እና ጨረር ከሚሉት ረጨረ (make or be radioactive) የሚለውን ግስ እናገኛለን።
  2. ረጨረ ማለት ጨረር ረጨ ማለት ነው።
  3. የረጨረ ግስ ሲረባ ረጨረ፣ ርጭር (ርጩር)፣ ረጫሪ (radioactive)፣ ርጨራ (radioactivity)፣ ርጫሬ፣ ርጫሮሽ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ ግስ የለውም።

radioactive = ረጫሪ
radioactivity = ርጨራ
radioactivity (verb) = ረጨረ
radioactive decay = ረጫሪ ብስከት
radioactive beta decay = ረጫሪ ባቴፍ ብስከት
radioactive element = ረጫሪ ቶስመክ
radioactive radiaion = ረጫሪ ጨረር
radioactive fallout = ረጫሪ ዶፍ
radioactive series = ረጫሪ ተርምር
radioactive tracer (radiotracer) = ረጫሪ ደባዥ

ደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (Weak Nuclear Force)

  1. ደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (weak nuclear force) ለረጫሪ ባቴፍ ብስከት (radioactive beta decay) መንስዔ የሆነ ግሳብ ነው።
  2. ባሌፍ ብስከት (beta decay) ማለት የቀኒጥ ቡኒጥ (nucleus) ባቴፍኑሶችን (beta particles) ማለትም ከፍተኛ ፍጥነታም (high speed) ተልኑሶችን (electrons) ወይም ወተልኑሶችን (positrons) በመርጨት የሚበሰክትበት (decay) ማለትም ወደ ሌላ ዓይነት ቡኒጥ (nucleus) የሚለወጥበት ክስተት (phenomenon) ማለት ነው። 
  3. ለምሳሌ ያህል ገልኑስ (neutron) በባሌፍ ብስከት (beta decay) ሲበሰክት ተልኑስ (electron) እና ፀረገልኑሲት (antineutrino) በመርጨት ማለትም አንቅሮ በመትፋት ወደ ቀዳምኑስ (proton) ይለወጣል።  እንደዚህ ዓይነት ባሌፍ ብስከት (beta decay) ጸውሪኳ (charge) ሉንታ (negative) የሆነውን ተልኑስን (electron) ስለሚያመነጨ ባሌፍ ሉንታ ብስከት (beta minus decay) ይባላል። 
  4. በተቃራኒው ደግሞ ቀዳምኑስ (proton) በባሌፍ ብስከት (beta decay) ሲበሰክት ወተልኑስ (positron) እና ገልኑሲት (neutrino) በመርጨት ማለትም አንቅሮ በመትፋት ወደ ገልኑስ (neutron) ይለወጣል።  እንደዚህ ዓይነት ባሌፍ ብስከት (beta decay) ጸውሪኳ (charge) ወንታ (positive) የሆነውን ወተልኑስን (positron) ስለሚያመነጨ ባሌፍ ወንታ ብስከት (beta plus decay) ይባላል። 
  5. ገልኑስ (neutron) በባሌፍ ሉንታ ብስከት (beta minus decay) ሲበሰክት ገልኑሱ አንቅሮ የሚተፋቸው ተልኑስ (electron) እና ፀርገልኑሲት (antineutrino) በገልኑሱ ውስጥ አስቀደመው የነበሩ እኑሶች ሳይሆኑ በብስከታው ሒደት የሚፈጠሩ እኑሶች ናቸው።  
  6. በተመሳሳይ መንገድ ቀዳምኑስ (proton) በባሌፍ ወንታ ብስከት (beta plus decay) ሲበሰክት ቀዳምኑሱ አንቅሮ የሚተፋቸው ወተልኑስ (positron) እና ገልኑሲት (neutrino) በገልኑሱ ውስጥ አስቀደመው የነበሩ እኑሶች ሳይሆኑ በብስከታው ሒደት የሚፈጠሩ እኑሶች ናቸው።  
  1. በብክረት (magnitude) ማለትም በጥንካሬ አንጻር ደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ  (weak nuclear force) ከቁስበታዊ ግሳብ (gravitational force) እጅግ በጣም የበለጠ ቢሆንም፣ ከብርቱ ቡኒጣዊ ግሳብ (strong nuclear force) እና ከሌክትሮማግኔታዊ ግሳብ (electromagnetic force) ግን እጅግ በጣም ያነሰ ነው።  ደካማ የተባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው። 
  2. የደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (electromagnetic force) ኑሃት (range)፣ ማለትም ደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ ሊገስብ የሚችልበት ርርቀት (distance) 10-15 m ገደማ ነው። 
  3. የቀዳምኑስ (proton) እና የገልኑስ (neutron) ገማዘንግ (diameter) ደግሞ 1.6×10−15m1.6\times 10^{-15} m ገደማ ነው።
  4. ስለዚህም የደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (electromagnetic force) ኑሃት (range) ከቀዳምኑስ (proton) እና ገልኑስ (neutron) ገማዘንግ (diameter) ያነሰ ነው ማለት ነው። 
  5. በዚህም ምክኒያት ደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (weak nuclear force) ሚና ያለው በቀዳምኑሶች ወይም በገልኑሶች ውስጥ ብቻ ነው ማለት ነው። 
  6. ደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (weak nuclear force) እንደ ሌሎቹ ዓይነት ግሳቦች የሚስብ (pull, attract) ወይም የሚገፋ (push, repel) ግሳብ ሳይሆን፣ በቀዳምኑሶች (protons) እና ግልኑሶች (neutrons) ውስጥ የሚገኙን ኳርኮች  ዓይነቶቻቸውን (types) ወይም ጣእሞቻቸውን (flavors) የሚለውጥ ግሳብ ነው።
  7. ለምሳሌ ያህል በባሌፍ ሉንታ ብስከት (beta minus decay) ላይ ገልኑስ (neutron) ወደ ቀዳምኑስ (proton) የሚለወጠው፣ በገልኑሱ ውስጥ ከሚገኙት ሁለቱ ድፋት ኳርኮች (down quarks) ውስጥ እንዱ በደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (weak nuclear force) አማካኝነት ወደ ቅናት ኳርክ (up quark) ሲለወጥ ነው።   
  8. በተመሳሳይ መንገድ በባሌፍ ወንታ ብስከት (beta plus decay) ላይ ቀዳምኑስ (proton) ወደ ገልኑስ (neutron) የሚለወጠው፣ በቀዳምኑሱ ውስጥ ከሚገኙት ሁለቱ ቅናት ኳርኮች (up quarks) ውስጥ እንዱ በደካማ ቡኒጣዊ ግሳብ (weak nuclear force) አማካኝነት ወደ ድፋት ኳርክ (down quark) ሲለወጥ ነው።   

ፋኞ ግንገና (String Theory)

  1. በኦሮምኛ ፋኞ ማለት ሲባጎ ማለት ነው።
  2. ይህም ፋኞ የሚባል ቃል string የሚባለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልና።
  3. ግንገና (theory) የሚለው ቃል የተገኘው ገነገነ (ታዘበ፣ ጠረጠረ፣ መረመረ) ከሚለው ያማረኛ ቃል ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ገነገነ (theorize)፣ ግንግን (ግንጉን) [theorized]፣ ገንጋኒ (ገንጋኝ) [theorist]፣ ግንገና (theorizing)፣ ግንግነት፣ ግንጋኔ፣ ግንጋኖሽ እያለ ይሄዳል።
  4. ፋኞ ግንገና (string theory) ማለት መሠረታዊ ኑሶችን (fundamenta particles) እንደ ነጥብመሰል እኑሶች (point-like particles) ሳይሆን፣ እንደ አንድ ስፍረታዊ (one dimensional) ተርገብጋቢ ፋኞወች (vibrating strings)፣ ማለትም ርዝመት እንጅ ወርድም ሆነ ከፍታ እንደሌላቸው ተርገብጋቢ ፋኞወች (vibrating strings) በመመልከት የቁስበትን ግንገና (theory of gravity) ከኑርከን ግንገና  (quantum theory) ጋር በማዋሃድ የኑርከን ቁስበት ዋህድ ግንገና (unified theory of quantum gravity) የሚባል አንድ ነጠላ ዋህድ ግንገና (unified theory) ለመፍጠር የሚጥር ግንገና (theory) ነው። 
  5. ፋኞ ግንገና (string theory) በ1960ወቹ ላይ መገንገን የተጀመረው የቡኒጣዊ ግሳቦችን (nuclear forces) ጠባዮች በተለይም ደግሞ የኳርኮችን ድርርገቶች (quark interactions)  በግንገናው አማካኝነት ለመግለጽ በመሞከር ነበር።
  6. የቡኒጣዊ ግሳቦች ጠባዮች ግን በኑርከን ዙላሑሲን (quantum chromodynamics) አማካኝነት በሚያረካ ስኬት ስለተገለጹ፣ ፋኞ ግንገናን (string theory) ለዚህ ተግባር መገልገሉ ሙሉ በሙሉ ቀርቶ፣ ሙሉ ትኩረቱ ኑርከን ቁስበት (quantum gravity) ላይ ሁኗል።     

theory = ግንገና
theorist = ገንጋኝ
theorize = ገነገነ
theorizing = ግንገና፣ ግንግነት፣ ግንጋኔ፣ ግንጋኖሽ
string = ፋኞ
string theory = ፋኞ ግንገና
string theorist = ፋኞ ገንጋኝ
quantum gravity = ኑርከን ቁስበት
unified theory = ዋህድ ግንገና
unified theory of quantum gravity = የኑርከን ቁስበት ዋህድ ግንገና

መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com