ጉሲን እና ቁነና (Physics & Measurement) ክፍል 7(ሀ)፤ ፍጥነት፣ ሶፊሳ እና ጠደፋ (Part 7(A): Speed, Velocity & Acceleration)

ማሳሰቢያ

ጉሲን እና ቁነና (Physics & Measurement) በሚለው ዋና ርዕስ ውስጥ የክፍል 7 ዓላማ ካልቪን (Kelvin) የሚባለውን የቤቶስ የሙቀት ቶካድ (SI unit of temperature) መበየን (define) ነው።  ይህን ለማድረግ ግን ከቶካዱ ጋር ስለተዛመዱ ፀንሳቦች (concepts) በግርድፉ ማለትም በጥልቀት ሳይሆን በተወሰነ መጠን ማውሳት አለብን።  ወደፊት ደግሞ በሌሎች ጦማሮች ላይ እነዚሁኑ ፅንሳቦች በጥልቀት እናወሳቸዋለን።    

  1. በዚህ ክፍል ማለትም ክፍል 7(ሀ) ላይ ስለ ፍጥነት (speed)፣ ሶፊሳ (velocity) እና ጠደፋ (acceleration) እናወሳለን።
  2. ክፍል 7(ለ) ላይ ስለ ቶኪማ ክባዊ ሑሰት (Uniform Circular Motion) እናወሳለን። 
  3. ክፍል 7(ሐ) ላይ ስለ ግሳብ (force) እና ሑሰት (motion) እናወሳለን። 
  4. ክፍል 7(መ) ላይ ስለ ግሳብ (force) እና ሥራ (work) እናወሳለን። 
  5. ክፍል 7(ሰ) ላይ ስለ ጉልበት (energy) እና ሃይል (power) እናወሳለን።
  6. ክፍል 7(ረ) ላይ ስለ ሙቀት (temperature)፣ ግለት (heat) እና ውስጣዊ ጉልበት (internal energy) እናወሳለን። 
  7. ክፍል 7(ሠ) ላይ ስለ ሙቀትልካት (thermometry) እና ሙቀትለኪወች (therometers) እናወሳለን። 
  8. ክፍል 7(ቀ) ላይ ስለ ጋስ ሕጎች (gas laws) እናወሳለን። 
  9. በመጨረሻም ክፍል 7(በ) ላይ በክፍሎች 7(ሀ) እስከ ክፍሎች 7(ቀ) ላይ ያወሳናቸውን ፅንሳቦች (concpts) በመጠቀም ካልቪን (kelvin) የሚባለውን የቤቶስ የሙቀት ቶካድ (SI unit of temperature) እንበይናለን። 

የጉሲን መሠረታዊ ዱሪወች (Fundamental Topics of Physics)

  1. ጉሲን (physics) የሰገል (science) ዘርፍ ሲሆን፣ የሁንዳ መሠረታዊ ሕጎች ስርካታዊ ጥናት (the systematic study of the fundamental laws of the universe) ነው ተብሎ በጥቅሉና ባጭሩ ሊበየን (defined) ይችላል። 
  2. ሁንዳ (universe) ማለት ሁለንተና ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ሁንዳ (ሁሉም) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው። 
  3. ሁንዳ (universe) ከሚለው ቃል ሁንዳዊ (universal)፣ ሁንዳዊ ሕግ (universal law) የመሳሰሉትን እናገኛለን።
  4. በጉሲን (physics) ውስጥ የሚጠኑት መሠረታዊ ዱሪወች (fundamental topics) ዐራት ሲሆኑ፣ እነሱም ሑሰት (motion)፣ ግሳብ (force)፣ ጉልበት (energy) እና ቁስ (matter) ናቸው።
  5. ዱሪ (topic) ማለት የመወያያ ርዕስ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ዱሬ (ርዕስ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው። 
  6. ዱሪ  (topic) እና ድሪ (ያንገት ጌጥ) እንዳይምታቱብወት።

ወንታ (positive)፣ ሉንታ (negative) እና ገልታ (neutral) 

  1. አወንታ ከሚለው ወንታ (positive) የሚለውን ቃል፣ አሉታ ከሚለው ሉንታ (negative) የሚለውን ቃል፣ ገለልታ ከሚለው ደግሞ ገልታ (neutral) የሚለውን ቃል እናገኛለን። 
  2. የገልታ (neutral) ግስ ሲረባ ገለተዘ (neutralize)፣ ግልትዝ (ግልቱዝ) [neutralized]፣ ገልታዚ (ገልታዥ) [neutralizer]፣ ግልተዛ (neutralization)፣ ግልትዘት፣ ግልታዜ፣ ግልታዞሽ እያለ ይሄዳል። ገለተዘ (neutralize) ማለት ገልታ (neutral) አደረገ ማለት ሲሆን፣ ግልትዝ (ግልቱዝ) ማለት ደግሞ የተገለተዘ ማለት ነው። 
  3. በተመሳሳይ መንገድ የወንታ (positive) ግስ ሲረባ ወነተዘ፣ ውንትዝ (ውንቱዝ)፣ ወንታዚ (ወንታዥ) ፣ ውንተዛ፣ ውንትዘት፣ ውንታዜ፣ ውንታዞሽ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ ግን የለውም።  ወነተዘ ማለት ወንታ (positive) አደረገ ማለት ሲሆን፣ ውንትዝ (ውንቱዝ) ማለት ደግሞ የተወነተዘ ማለት ነው።
  4. እንዲሁም የሉንታ (negative) ግስ ሲረባ፣ ለነተዘ፣ ልንትዝ (ልንቱዝ)፣ ለንታዚ (ለንታዥ)፣ ልንተዛ፣ ልንት ዘት፣ ልንታዜ፣ ልንታዞሽ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ ግን የለውም። ለነተዘ ማለት ሉንታ (negative) አደረገ ማለት ሲሆን፣ ልንትዝ (ልንቱዝ) ማለት ደግሞ የተለነተዘ ማለት ነው።    

positve = ወንታ
positive (verb) = ወነተዘ
negative = ሉንታ
negative (verb) = ለነተዘ
neutral =  ገልታ
neutralize = ገለተዘ

ምልክት (Sign)፣ ወመል (Symbol) እና ወሉንታ (Sign)

  1. ምልክት (sign) ማለት ለማመልከት የሚያገለግል ማለት ነው፣ የእኩልነት ምልክት (equality sign)፣ የመደመር ምልክት (addition sign)፣ የመቀነስ ምልክት (subtraction sign) እንዲሉ።  ስለምልከት መረዳት የመረዳት ምልክት ነው (understanding signs is a sign of understanding)። 
  2. ወካይ ምልክት ከሚለው ሐረግ ወመል (symbol) የሚለውን ቃል እናገኛለን።  ወመል (symbol) ከምልክት (sign) ጋር ተመሳሳይነት ያለውና አብዛኛውን ጊዜ የሚተካካ (interchangeable) ቃል ነው።
  3. የወመል (symbol) ግስ ሲረባ ወመለ (symbolize)፣ ውምል (symbolized)፣ ወማሊ (ወማይ) [symbolizer]፣ ውመላ (symbolization) እያለ ይሄዳል።  ወመለ (symbolize) ማለት ወመል (symbol) ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ውምል (symbolized) ማለት ደግሞ የተወመለ ማለትም ወመል (symbol) የተደረገ ማለት ነው። 
  4. ወንታ (positive) እና ሉንታ (negative) ከሚሉት ወሉንታ (positive or negative sign) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ወሉንታ ማለት ወንታ ምልክት (positive sign) ወይም ሉንታ ምልከት (negative sign) ማለት ነው።
  5. ለምሳሌ ያህል ወሉንታ ቀዘድ (sign function, signum function) ማለት የወናብ ቁጥርን (rean number) ወንታ (positive) መሆን ወይም ሉንታ (negative) መሆን የሚያመለከት ቀዘድ (function) ማለት ነው።
    • ወንታ ለሆነ ወናብ ቁጥር (positive real number) የወሉንታ ቀዘድ (sign function) እሴት ወንታ ቶኮ (+1) ነው።
    • ሉንታ ለሆነ ወናብ ቁጥር (negative real number) ደግሞ የወሉንታ ቀዘድ (sign function) እሴት ሉንታ ቶኮ (-1)     

sign = ምልክት
sign (positive or negative sign) = ወሉንታ
sign function (signum function) = ወሉንታ ቀዘድ
symbol = ወመል
symbolize =  ወመለ
symbolization = ውመላ

ስተና፣ ስትነት (Rate)

  1. ባማረኛ ሳተነ ማለት ሮጠ፣ ፈጠነ፣ ቀለጠፈ ማለት ነው፣ ሳተናው እንዲሉ ፈጣኑ፣ ቀልጣፋው ሊሉ። 
  2. ሳተነ ከሚለው ያማረኛ ቃል ስተና፣ ስትነት (rate) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። 
  3. ስተና ወይም ስትነት (rate) የሚለው ቃል የለውጥን መጠን የሚያመለክት ቃል ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ የሚገለጸው በመቶኛ (percentage) ነው።
  4. የስተና (rate) ግስ ሲረባ ሳተነ፣ ስቱን፣ ሳታኒ (ሳተኝ)፣ ስተና፣ ስትነት፣ ስታኔ፣ ስታኖሽ እያለ ይሂዳል።
  5. ሳተነ ማለት በተወሰነ ስተነት (rate) ተለወጠ ማለት ነው።

rate = ስተና፣ ስትነት
rate of change =  የለውጥ ስተና
interest rate = የወለድ ስተና
birth rate = ውልደት ስተና
death rate (mortality rate) =  ሙተት ስተና
child mortality rate = ሕፃን ሙተት ስተና (ሕሙስ)
annual percentage rate (APR) = ዓመታዊ መቶኛ ስተና (ዓመስ)
bank rate = ባንክ ስተና (ባስ)
bit rate = አልቦንድ ስተና
byte rate = ሳሞንድ ስተና
data rate = ቱማ ስተና (ቱስ)
flow rate = የፍሰት ስተና

ባተሜ (Initial) እና ፍጻሜ (Final)

  1. በግእዝ ባተ ማለት ጀመረ ማለት ነው፣ አባተ እንዲሉ አስጀመረ ሊሉ።  ይህን ቃል በመጠቀምና ፍጻሜ (final) የሚለው ቃል አካሄድ በመከተል ባተሜ (initial) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
  2. ባተሜ (initial) ማለት የመጀመረያ ወይም መነሻ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ በተመ (initialize)፣ ብትም (ብቱም) [initialized]፣ በታሚ (initializer)፣ ብተማ (initialization)፣ ብትመት፣ ብታሜ፣ ብታሞሽ እያለ ይሄዳል።
  3. በተመ (initialize) ማለት ጀመረ (አስጀመረ) ማለት ሲሆን፣ ብትም (ብቱም) [initialized] ማለት ደግሞ የተበተመ ማለት ነው። 

initial = ባተሜ
initial value = ባተሜ እሴት
initialize = በተመ
final = ፍጻሜ
final value = ፍጻሜ እሴት
finalize =  ፈጸመ

አዴት (Position) እና ፍልሰት (Displacement)

  1. ኢዶ (ማለትም ቦታ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል አዴት (location, position) የሚለውን ቃል እናገኛለን።  አዴት (location, position) ማለት መገኛ ቦታ፣ ያሉበት ቦታ ማለት ነው።
  2. የአዴት (position, location) ግስ ሲረባ አደተ (locate)፣ እድት (እዱት) (located)፣ አዳቲ (አዳች) [locating, locator]፣ እደታ (locating)፣ እዳቴ፣ እዳቶሽ እያለ ይሄዳል።
  3. ፈለሰ ማለትም ተሰደደ፣ ቦታውን ለቆ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው ፍልሰት (displacement) የሚለውን ቃል እናገኛለን። 
  4. የፍልሰት (displacement) ግስ ሲረባ አፈለሰ (displace)፣ ፍልስ (/ፍሉስ\) [displaced]፣ አፍላሲ (አፍላሽ) [displacing]፣ ፈለሳ (displacement)፣ ፍልሰት (displacement) እያለ ይሄዳል።
  5. /ፍሉስ\ ማለት የፈለሰ ወይም የተፈለሰ የተፈለሰ ማለት ነው። 

location (position) = አዴት፣ ቅምጠት
locate = አደተ
initial position = ባተሜ አዴት
final position = ፍጻሜ አዴት
displacement = ፍልሰት
displace = አፈለሰ
displaced = /ፍሉስ\፣ ተፈናቃይ
displaced (the displaced) =  /ፍሉሳን\፣ ተፈናቃዮች

ፍጥነት (Speed) እና ሶፊሳ (Velocity)

  1. ሰፊሳ (ማለትም ፍጥነት) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ሶፊሳ (velocity) የሚለውን ቃል እናገኛለን። 
  2. ግሱም ሲረባ ሶፈሰ፣ ሱፍስ፣ ሶፋሲ፣ ሱፈሳ፣ ሱፍሰት፣ ሱፋሴ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም። 
  3. ፍጥነት (speed) የሚለው ቃል ምን ያህል ርቀት በምን ያህል ጊዜ መጓዘን የሚያመለከት አቅጣጫን የማያካትት ቃል ነው። 
  4. በሌላ በኩል ደግሞ ሶፊሳ (velocity) ፍጥነትን ከአቅጣጫ ጋር የሚያጣምር ቃል ነው። 
  5. ስለዚህም ፍጥነት (speed) ብክረት (magnitude) ብቻ ያለው፣ አቅጣጫ (direction) ግን የሌለው (በትክክል ለመናገር ደግሞ አቅጣጫን የማያጣምር) ናይባ (quantity) ስለሆነ፣ ሐዝተን ናይባ (scalar quantity) ነው። 
  6. በሌላ በኩል ደግሞ ሶፊሳ (velocity) ብክረትም (magnitude) አቅጣጫም (direction) ያለው ፍላስተን ናይባ (vector quantity) ነው። 
  7. ለምሳሌ ያህል 50 ሃጃኖሜትር በሰዓት (50 kilometer per hour) የሚጓዝ ሞጭላፊ (pick-up truck) የሚጓዘው ወደ ሐራምባም ሆነ ወደ ቆቦ ፍጥነቱ ያው ሲሆን፣ ሶፊሳው ግን የተለያየ ነው፣  አቅጣጫው የተለያየ ነውና።
  8. ሐራምባ ማለት የሐር ተራራ ወይም መንደር ማለት ሲሆን፣ የሚገኘውም ይፋት ውስጥ ነው። ቆቦ ደግሞ ባንኮበር በኩል የሚገኝ መንደር ሲሆን፣ ስያሜው የተገኘው ቆበበ (ጉብ አለ፣ ጎብታ መሰለ) ከሚለው ቃል ነው። ሐራምባና ቆቦ ማለት ገማዘንጋዊ ተቃራኒ (diametrically opposite) ማለትም ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ማለት ሲሆን፣ ጦሳና አዝዋ ወይም እንጦጦና የረር ልንለውም እንችላለን።  ጦሳ እና አዘዋ እንደቅደምተከተላቸው በደሴ ምዕራብና ምሥራቅ የሚገኙ ተራሮች ናቸው።    

speed –  ፍጥነት
speedometer – ፍጥነትለኪ
velocity – ሶፊሳ
velocity (verb) – ሶፈሰ
velocity vector – ሶፊሳ ፍላስተን
diametrically opposite = ገማዘንጋዊ ተቃራኒ፣ ሐራምባና ቆቦ፣ ጦሳና አዘዋ፣ እንጦጦና የረር

የፍጥነት (Speed) እና የሶፊሳ (Velocity) ቀመሮች

  1. ፍጥነት (speed) የሚገኘው የተጓዙትን ርቀት (distance travelled) ርቀቱን ለሚጓዝ በፈጀው ጊዜ (time of travel) በመደሸር (divide) ማለትም በማካፈል ነው።
  2. በሌላ አባባል ፍጥነት ማለት ምን ያህል ርቀት በምን ያህል ጊዜ እንደተጓዙ የሚያመለከት እሴት ነው።
  3. በዚህም ምክኒያት ፍጥነት ማለት ርቀት በጊዜ የሚለወጥበት ስትነት ነው (speed is the time rate of change of distance) ወይም ባጭሩ ፍጥነት የርቀት ለውጥ ስትነት ነው (speed is the rate of change of distance) ይባላል።
  4. በተመሳሳይ መንገድ ሶፊሳ (velocity) የሚገኘው የፈለሱትን ፍልሰት (displacement) ፍልሰቱን ለመፍለስ በፈጀው ጊዜ (time) በመደሸር (divide) ማለትም በማካፈል ነው።
  5. በሌላ አባባል ሶፊሳ ማለት ምን ያህል ፍልሰት በምን ያህል ጊዜ እንደተፈለሰ የሚያመለከት እሴት ነው።
  6. በዚህም ምክኒያት ሶፊሳ ማለት ፍልሰት በጊዜ የሚለወጥበት ስትነት ነው (velocity is the time rate of change of displacement) ወይም ባጭሩ ሶፊሳ የፍልሰት ለውጥ ስትነት ነው (velocity is the rate of change of displacement) ይባላል።

የፍጥነት (Speed) ቤቶስ ቶካድ (SI Unit) እና አልቤቶስ ቶካዶች (Non-SI Units)

  1. ቤቶስ ቶካድ (SI unit) ማለት ቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት (International System of Units) የሚባለው ባጭሩ ሲጠራ ነው።
  2. ርቀት (distance) እና ፍልሰት (displacement) ርዝመቶች (lengths) ስለሆኑ፣ ቤቶስ ቶካዳቸው (SI Unit) ሜትር ወይም ሚትር (meter) ነው።
  3. የጊዜ (time) ቤቶስ ቶካድ (SI Unit) ደግሞ ኑሲቃ (second) ነው። 
  4. ስለዚህም የፍጥነት (speed) እንዲሁም የሶፊሳ (velocity) ቤቶስ ቶካድ (SI unit) ሜትር በኑሲቃ (meter per second) ነው ማለት ነው። 

ቶካድ ቅየራ (Unit Conversion)

  1. የፍጥነት (speed) ቤቶስ ቶካድ (SI Unit) ሜትር በኑሲቃ (meter per second) ቢሆንም፣ አብዛኛውን ጊዜ ግን ፍጥነት የሚሰጠው ወይም የሚገለጸው የቤቶስ ቶካድ ባልሆኑት ሃጃኖሜትር በሰዓት (kilometer per hour) እና ማይል በሰዓት (mile per hour) ነው።
  2. አንድ ሃጃኖሜትር (one kilometer) አንድ ሺ ሜትር (1000 m) ሲሆን፣ አንድ ሰዓት (one hour) ደግሞ ሦስት ሺ ስድስት መቶ ኑሲቃ (3600 s) ነው።  ስለዚህም በሃጃኖሜትር በሰዓት (kilometer per hour) የተሰጠን ፍጥነት ወደ ሜትር በኑሲቃ (meter per second) ለመቀየር (convert) የሚያስፈልገው በ 10/36 መበዘር (multiply) ማለትም ማባዛት ብቻ ነው።
  3. በተመሳሳይ መንገድ አንድ ማይል (one mile) አንድ ሺ ስድስት ሜትር (1600m) ሲሆን፣ አንድ ሰዓት ደግሞ ሦስት ሺ ስድስት መቶ ኑሲቃ (3600 s) ነው።  ስለዚህም በማይል በሰዓት (mile per hour) የተሰጠን ፍጥነት ወደ ሜትር በኑሲቃ (meter per second) ለመቀየር (convert) የሚያስፈልገው በ 16/36 መበዘር (multiply) ማለትም ማባዛት ብቻ ነው።

ምሳሌ፤ አንድ ተማሪ ከቡሻ (cafe) ተነስቶ በሰሜን አቅጣጫ 4 ሃጃኖሜትር (4 kilometer) በመጓዝ ጃንሱቅ (supermarket) ከገባ በኋላ የሚገዛውን ገዛዝቶ በደቡብ አቅጣጫ 6.3 ሃጃኖሜትር (6.5 kilometer) በመጓዝ ቤቱ ከሚግኝበት ደረባ (condominium) ደረሰ።  ተማሪው ከመነሻው ተነስቶ መድረሻው ለመድረስ የፈጀበት ጠቅላላ ጊዜ 2 ሰዓት (2 hours) ቢሆን፣ የተማሪውን ፍጥነት (speed) እና ሶፊሳ (velocity) ፈልግ።  ቡሻ (cafe) የሚለው ቃል የተገኘው ቡና እና ሻሂ ከሚሉት ሲሆን፣ ደረባ (condominium) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ ደርብ (ማለትም ፎቅ፣ ሰገነት) ከሚለው ያማረኛ ቃል ነው።

ቃዳ (Interval)  

  1. ቃዳ (interval) ማለት በሁለት እሴቶች (values) መካከል ያለ የእሴት ርዝመት ማለት ነው። 
  2. ለምሳሌ ያህል የጊዜ ቃዳ (time interval) ማለት በሁለት ጊዜወች መካክል ያለ የጊዜ ርዝመት (length of time, duration of time) ማለት ነው።
  3. ቃዳ (interval) የሚለው ቃል የተገኘው ቃዳ  (ማለትም የተለየ፣ የተከፈለ፣ መም፣ ትልም) ከሚለው ያማረኛ ቃል ነው።

interval = ቃዳ
time interval = የጊዜ ቃዳ
open interval = ክፍት ቃዳ
closed interval = ዝግ ቃዳ
half-open interval = ግማሽ ክፍት ቃዳ
half-closed interval = ግማሽ ዝግ ቃዳ
finite interval = ወዳኢ ቃዳ
infinite interval = ኢወዳኢ ቃዳ

ያንድ ስፍረታዊ ሑሰት ሶፊሳ (Velocity in One Dimensional Motion)

  1. በቀጤ መስመር (straight line) ላይ የሚካሄድ ሑሰት (motion) አንድ ስፍረታዊ ሑሰት (one dimensional motion) ወይም ቄጠማ ሑሰት (rectilinear motion) ይባላል። 
  2. አንድ ስፍረታዊ ሑሰትን( one dimensional motion) ለመተንተን (analyze) ያገለግለን ዘንድ የሚከተለውን ስምምነት (convention) እንጠቀማለን።
    • ሑሰቱ የሚካሂደበትን ቀጤ መስመር (straight line) አግዳሚ መስመር (horizontal line) እናደርገውና ስሙን x-ረቲድ (x-axi) እንለዋለን። 
    • በ x-ረቲድ ላይ ከፈጅር (origin) ወደ ቀኝ (to the right) የሚያመለክተውን አቅጣጫ (direction) ወንታ አቅጣጫ (positive direction) እንለውና ወደ ግራ (to the left) የሚያመለክተውን አቅጣጫ ደግሞ ሉንታ አቅጣጫ (negative direction) እንለዋለን። 

የሶፊሳ ወሉንታ (Sign of Velocity)

ባንድ ስፍረታዊ ሑሰት (one dimensional motion) ላይ የሶፊሳ አቅጣጫ (direction of velocity) የሚገለጸው በሶፊሳው ወንታ (positive) ወይም ሉንታ (negative) መሆን ነው። በሌላ አባባል ባንድ ስፍረታዊ ሑሰት ላይ የሶፊሳ አቅጣጫ የሚገለጸው በሶፊሳው ወሉንታ (sign of velocity) ነው።  

  1. የሶፊሳ (velocity)  v = Δx/Δt እሴት (value) ወንታ (positive) የሚሆነው ፍልሰት (displacement) Δx = x2 – x1 ወንታ (positive) ሲሆን፣ ማለትም Δx > 0  ሲሆን ነው።   
  2. ፍልሰት (displacement) Δx = x2 – x1 ወንታ (positive) የሚሆነው ደግሞ x2 > x1 ሲሆን፣ ማለት ፍጻሜ አዴት (final position, x2) ከባተሜ አዴት (initial position, x1) በስተቀኝ (to the right) ሲሆን ነው። 
  3. ስለዚህም ወንታ ሶፊሳ (positive velocity) ማለት ፍልሰቱ ወደ ቀኝ (displacement to the right) የሆነ ሶፊሳ (velocity) ማለት ነው። 
  4. በሌላ በኩል ደግሞ የሶፊሳ (velocity) v = Δx/Δt እሴት (value) ሉንታ (negative) የሚሆነው ፍልሰት (displacement) Δx = x2 – x1 ሉንታ (negative) ሲሆን፣ ማለትም Δx < 0  ሲሆን ነው። 
  5. ፍልሰት (displacement) Δx = x2 – x1 ሉንታ (negative) የሚሆነው ደግሞ x2 < x1 ሲሆን፣ ማለት ፍጻሜ አዴት (final position, x2) ከባተሜ አዴት (initial position, x1) በስተግራ (to the left) ሲሆን ነው። 
  6. ስለዚህም ሉንታ ሶፊሳ (negative velocity) ማለት ፍልሰቱ ወደ ግራ (displacement to the left) የሆነ ሶፊሳ (velocity) ማለት ነው። 

ቀሳን (Slow) እና ፈጣን (Fast)

  1. ቀስ አለ (በቀስታ ሄደ) የሚለውን ፈጣን (fast) ከሚለው ጋር በማመሳሰል ቀሳን (slow) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
  2. ቀሳን (slow) ማለት ቀስተኛ፣ በቀስታ የሚሄድ ማለት ነው።  በሌላ አባባል ቀሳን የፈጣን ተቃራኒ ነው። 
  3. የቀሳን (slow) ግስ ሲረባ ቀሰነ (to slow) ፣ ቅስን (ቅሱን) [slowed]፣ ቀሳኒ (ቀሳኝ) [slowing]፣ /ቅሰና\ (slowing)፣ \ቅስነት/ እያለ ይሄዳል።
  4. ቀሰነ የፈጠነ ተቃራኒ ሲሆን፣ ቅሰና የፈጠና፣ ቅስነት ደግሞ የፍጥነት ተቃራኒወች ናቸው።  
  5. የሚጠብቀው /ቅሰና\ እና የማይጠበቀው \ቅስና/ (ቄስነት) እንዳይምታቱብወት አደራ፣ ምንም ግንኙነት የላቸውምና።   

fast = ፈጣን
fast (verb) = ፈጠነ
slow = ቀሳን
slow (verb) = ቀሰነ

ጠደፋ (Acceleration) እና አልጠደፋ (Non-acceleration)

  1. አጣደፈ (አቻኮለ) ከሚለው ጠደፋ (acceleration) የሚለውን እናገኛለን። 
  2. የጠደፋ (acceleration) ግስ ሲረባ ጠደፈ (accelerate)፣ ጥድፍ (ጥዱፍ) [accelerated]፣ ጠዳፊ (አጠዳፊ) [accelerator]፣ ጠደፋ (accelerating)፣ ጥድፈት፣ ጥዳፌ፣ ጥዳፎሽ እያለ ይሄዳል።

accelerate  = ጠደፈ፣ አጠደፈ
acceleration (non-acceleration)  = ጠደፋ፣ አልጠደፋ
accelerating  (non-accelerating) = ጠዳፊ፣ አልጠዳፊ
accelerated (non-accelerated) = ጥዱፍ፣ አልጥዱፍ
accelerating (accelerated) particle = ጠዳፊ (ጥዱፍ) እኑስ
accelerating (accelerated) reference frame = ጠዳፊ (ጥዱፍ) ዋቢ መቃን
accelerator = ጠዳፊ፣ አጠዳፊ
particle accelerator = እኑስ ጠዳፊ
acceleratometer = ጠደፋለኪ

ቋሚ (Constant) እና ጠዋጢ (Variable)

  1. ቋሚ (constant) ማለት የማይለዋወጥ እሴት ያለው ማለት ሲሆን፣ አልቋሚ (non-constant, nonconstant) ማለት ደግሞ ቋሚ ያልሆነ፣ ማለትም እሴቱ የሚለዋወጥ ማለት ነው። 
  2. ከዚህም ቋሚነት (constancy)፣ አልቋሚነት (non-constancy) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
  3. ጠዋጢ (variable) ማለት ተለዋዋጭ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ተለዋወጠ ከሚለው ነው።
  4. ግሱም ሲረባ ጠወጠ (vary)፣ ጥውጥ (varied)፣ ጠዋጢ (varying, variable)፣ ጥወጣ (variation) እያለ ይሄዳል። 
  5. ጠወጠ (vary) ማለት ተለዋወጠ ወይም ተለዋዋጭ ሆነ ማለት ሲሆን፣ ጥውጥ (varied) ማለት ደግሞ የተለዋወጠ ማለት ነው።  

constant (non-constant) = ቋሚ፣ አልቋሚ
constancy (non-constancy) = ቋሚነት፣ አልቋሚነት
vary = ጠወጠ
variation = ጥወጣ፣ ጥውጠት፣ ጥዋጤ፣ ጥዋጦሽ
variable  (variability) = ጠዋጢ፣ ጠዋጢነት

ቶኪማ (Uniform) እና  አልቶኪማ (Non-Uniform)

  1. ቶኮ ማለትም አንድ ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ቶኪማ (uniform) የሚለውን ቃል እናገኛለን። 
  2. ቶኪማ (uniform) ማለት አንድ ዓይነት ወይም አንድ ወጥ እንደ ማለት ነው።
  3. የቶኪማ  (uniform) ግስ ሲረባ ቶከመ፣ ቱክም፣ ቶካሚ፣ ቱከማ፣ ቱክመት፣ ቱካሜ፣ ቱካሞሽ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
  4. ቶከመ ማለት ቶኪማ (uniform) ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ቱክም ማለት ደግሞ የተቶከመ ማለት ነው።
  5. ቶኪማ (uniform) ያልሆነ አልቶኪማ (nonuniform, non-uniform) ይባላል።  ስለዚህም አልቶኪማ ማለት አንድ ወጥ ያልሆነ ማለት ነው።
  6. ቶኪማ (uniform) እና ቶካድ (unit) እንዳይምታቱብወት።

uniform = ቶኪማ
uniform (verb) = ቶከመ
uniformity = ቶኪማነት
non-uniform = አልቶኪማ

ቶኪማ ሑሰት  (Uniform Motion)

  1. ሶፊሳ (velocity) ማለት ፍጥነትን (speed) ካቅጣጫ (direction) ጋር ያጣመረ ፍላስተን ናይባ (vector quantity) ነው ብለናል። 
  2. ስለዚህም ቋሚ ሶፊሳ (constant velocity) ማለት ቋሚ ፍጥነት (constant speed) እና ቋሚ አቅጣጫ (constant direction) ማለት ነው። 
  3. ስለዚህም በቋሚ ሶፊሳ የሚካሄድ ሑስት (motion with constant velocity) ማለት በቋሚ ፍጥነት (constant speed) እና በቋሚ አቅጣጫ (constant direction) የሚካሄድ ሑስት (motion) ማለት ነው።
  4. በሌላ አባባል በቋሚ ሶፊሳ የሚካሄድ ሑሰት (motion with constant velocity) ማለት በቀጤ መስመር (straight line)) ላይ ባንድ አቅጣጫ (in one direction) እና በቋሚ ፍጥነት (constant speed) የሚካሄድ ሑሰት (motion) ማለት ነው።
  5. በቋሚ ሶፊሳ የሚካሄድ ሑሰት (motion with constant velocity) በልዩ ስም ቶኪማ ሑሰት (uniform motion) ይባላል።
  6. ስለዚህም ቶኪማ ሑሰት (uniform motion) ማለት በቀጤ መስመር (straight line) ላይ ባንድ አቅጣጫ (in one direction) እና በቋሚ ፍጥነት (constant speed) የሚካሄድ ሑሰት (motion) ማለት ነው።

አልቶኪማ ሑሰት  (Non-uniform Motion) ወይም ጠደፋ ሑሰት (Accelerated Motion)

  1. ቶኪማ (uniform) ያልሆነ ሑሰት (motion) አልቶኪማ ሑሰት (non-uniform motion) ወይም ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ጥዱፍ ሑሰት (accelerated motion) ወይም  ጠደፋ ሑሰት  ይባላል። 
  2. ስለዚህም ጠደፋ ሑሰት (accelerated motion) ማለት በቋሚ ሶፊሳ (constant velocity) ሳይሆን በጠዋጢ ሶፊሳ (variable velocity) የሚካሄድ ሑሰት (motion) ማለት ነው።

የጠደፋ ዓይነቶች  (Types of Accelerations)

  1. አልቶኪማ ሑሰት (non-uniform motion) ወይም ጠደፋ ሑሰት (accelerated motion) ማለት በጠዋጢ ሶፊሳ (variable velocity) ማለትም በተለዋዋጭ ሶፊሳ (changing velocity) የሚካሄድ ሑሰት (motion) ማለት ስለሆነ፣ ከሚከተሉት ሦስቱ አንዱን ሊሆን ይችላል።
    • ፍጥነት (speed) የሚጠውጥበት (vary) ማለትም ፍጥነት የሚለወጥበት ወይም የሚለዋወጥበት ሑሰት፣
    • አቅጣጫ (direction) የሚጠውጥበት (vary) ማለትም አቅጣጫ የሚለወጥበት ወይም የሚለዋወጥበት ሑሰት፣
    • ፍጥናትና አቅጣጫ (speed and direction) ሁለቱም የሚጠውጡበት (vary) ማለትም የሚለወጡበት ወይም የሚለዋወጡበት ሑሰት፣
  2. ስለዚህም የሚከተሉት ሁሉ ጠደፋ ሑሰቶች (accelerated motions) ናቸው ማለት ነው።
    • ሑሰት መጀመር (starting from rest)
    • ሑሰት ማቆም  (coming to stop)
    • መፍጠን ማለትም ፍጥነትን እየጨመሩ መሖስ (speeding up)
    • መቀሰን ማለትም ፍጥነትን እየቀነሱ መሖስ (slowing down)
    • አቅጫን መጠወጥ ማለትም አቅጣጫን መለወጥ ወይም መለዋወጥ (varying direction)

የጠደፋ ቀመር (Acceleration Formula)

  1. ጥዱፍ ሑስት (accelerated motion) ወይም ጠደፋ ሑሰት ማለት በጠዋጢ ሶፊሳ (variable velocity) ማለትም በተለዋዋጭ ሶፊሳ (changing velocity) የሚካሄድ ሑሰት (motion) እንደሆነ ተመልክተናል። 
  2. የጥዱፍ ሑሰቱ (accelerated motion) ጠደፋ (acceleration) እሴት የሚገኘው ደግሞ በሑሰቱ ላይ የተከሰተውን የሶፊሳ ለውጥ (change in velocity) የሶፊሳው ለውጥ ለመከሰት በፈጀበት ጊዜ (time) በመደሸር (divide) ማለትም በማካፈል ነው።
  3. በዚህም ምክኒያት ጠደፋ ማለት ሶፊሳ በጊዜ የሚለወጥበት ስትነት ነው (acceleration is the time rate of change of velocity) ወይም ባጭሩ ጠደፋ ማለት የሶፊሳ ለውጥ ስትነት ነው (acceleration is the rate of change of velocity) ይባላል።   

የጠደፋ ወሉንታ (Sign of Acceleration)  

  1. ጠደፋ (acceleration) ማለት የሶፊሳ ለውጥ ስትነት (rate of change of velocity) ማለት ስለሆነ፣ ልክ እንደ ሶፊሳ (velocity) ብክረት (magnitude) እና አቅጣጫ (direction) ያለው ፍላስተን ናይባ (vector quantity) ነው። 
  2. ባንድ ስፍረታዊ ሑሰት (one dimensional motion) ላይ የጠደፋ አቅጣጫ (direction of acceleration) የሚገለጽው) በጠደፋው ወንታ (positive) ወይም ሉንታ (negative) መሆን ነው። በሌላ አባባል ባንድ ስፍረታዊ ሑሰት ላይ የጠደፋ አቅጣጫ የሚገለጸው በጠደፋው ወሉንታ (sign of acceleration) ነው። 
  3. የጠደፋ (acceleration) a = Δv/Δt እሴት (value) ወንታ (positive) የሚሆነው የሶፊሳ ለውጥ (change in velocity) Δv = v2 – v1 ወንታ (positive) ሲሆን፣ ማለትም Δv > 0 ሲሆን ነው። 
  4. የጠደፋ (acceleration) a = Δv/Δt እሴት (value) ሉንታ (negative) የሚሆነው ደግሞ የሶፊሳ ለውጥ (change in velocity)  Δv = v2 – v1 ሉንታ (negative) ሲሆን፣ ማለትም Δv < 0 ሲሆን ነው። 

ዘገማ (Deceleration)

  1. አጣደፈ (አቻኮለ)  ከሚለው ቃል ጠደፋ (acceleration) የሚለውን ቃል እንዳገኘን ሁሉ፣ አዘገመ (በቀስታ ሄደ ) ከሚለው ቃል ደግሞ ዘገማ (deceleration) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
  2. የዘገማ (deceleration) ግስ ሲረባ ዘገመ (decelerate)፣ ዝግም (ዝጉም) [decelerated]፣ ዘጋሚ (decelerator)፣ ዘገማ (ዝገማ) [deceleration]፣ ዝግመት፣ ዝጋሜ፣ ዝጋሞሽ እያለ ይሄዳል።  

decelerate = ዘገማ
decelerated = ዝግም
decelerated motion = ዝግም ሑሰት፣ ዘገማ ሑሰት
deceleration (decelerating) = ዘገማ
decelerator = ዘጋሚ፣ አዘጋሚ

ዘገማ (Deceleration) እና የጠደፋ ወሉንታ (Sign of Acceleration)

  1. በቀጤ መስመር (straight line) ላይ ባንድ አቅጣጫ (one direction ) በሚቀንስ ፍጥነት (decreasing speed) የሚካሄድ ሑሰት (motion) ያለው ጠደፋ (acceleration) በልዩ ስም ዘገማ (deceleration) ይባላል። 
  2. የጠደፋ ወሉንታ (sign of acceleration) በሚለው ክፍል ላይ እንደተመለከትነው ደግሞ፣ በቀጤ መስመር(straight line) ላይ ባንድ አቅጣጫ(one direction ) በሚቀንስ ፍጥነት(decreasing speed) ለሚካሄድ ሑሰት (motion)
    • የሑሰቱ አቅጣጫ (direction of motion) ወንታ አቅጣጫ (positive direction) ከሆነ ጠደፋው ሉንታ ጠደፋ (negative acceleration) ይሆናል።
    • የሑሰቱ አቅጣጫ (direction of motion) ሉንታ አቅጣጫ (negative direction) ከሆነ ደግሞ ጠደፋው ወንታ ጠደፋ (positive acceleration) ይሆናል።
  3. ስለዚህም ዘገማ (deceleration) ሲባል እንደ ሑሰቱ አቅጣጫ (depending on the direction of motion) ወንታ ጠደፋ (positive acceleration) ወይም ሉንታ ጠደፋ (negative acceleration) ሊሆን ይችላል ማለት ነው። 
  1. ዘገማ (deceleration) ሲባል እንደ ሑሰቱ አቅጣጫ (depending on the direction of motion) ወንታ ጠደፋ (positive acceleration) ወይም ሉንታ ጠደፋ (negative acceleration) ሊሆን ስለሚችል፣ ድንግረት (confusion) ሊፈጥር ይችላል፣ ይፈጥራልም።
  2. በዚህም ምክኒያት ጉሲነኛወች (physicists) ዘገማ (deceleration) የሚባለውን ቃል አለመጠቀም ይመርጣሉ።
  3. በሌላ አባባል ዘገማ (deceleration) ለዘወትር ግልጋሎት (everyday use) የሚውል አዘቦታዊ ቃል (everyday word) እንጅ ጉሲናዊ ብያኔ (physics definition) የተሰጠው ጉሲናዊ ቃል (physics word) አይደለም።
  4. በጉሲን ውስጥ የሚታወቀው ዘገማ (deceleration) ሳይሆን ጠደፋ (acceleration) ብቻ ነው።  እሱም ወንታ ጠደፋ (positive acceleration)፣ ሉንታ ጠደፋ (negative acceleration) ወይም ዳዶ ጠደፋ (zero acceleration) ሊሆን ይችላል።

የጠደፋ ቤቶስ ቶካድ (SI Unit of Acceleration)

  1. ቤቶስ ቶካድ (SI unit) ማለት ቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት (International System of Units) የሚባለው ባጭሩ ሲጠራ ነው።
  2. የፍጥነት (speed) እንዲሁም የሶፊሳ (velocity) ቤቶስ ቶካድ (SI unit) ሜትር በኑሲቃ (meter per second, m/s) ነው። 
  3. የጊዜ (time) ቤቶስ ቶካድ (SI Unit) ደግሞ ኑሲቃ (second, s) ነው።
  4. ስለዚህም የጠደፋ (acceleration) ቤቶስ ቶካድ (SI unit) ሜትር በኑሲቃ (m/s) ሲደሸር (divided) ማለትም ሲካፍል በኑሲቃ (s) ይሆናል ማለት ነው። 
  5. በሌላ አባባል የጠደፋ (acceleration) ቤቶስ ቶካድ (SI unit) ሜትር በኑሲቃ፣ በኑስቃ [meter per second per second] ሲሆን፣ የሚጻፈውም በመልክ  (m/s)/s ነው ማለት ነው። 
  6. አብኛውን ጊዜ ግን (m/s)/s ባጭሩ m/s2 በሚል መልክ ይጻፋል። 

ምሳሌ፤ ሎን መብራት (traffic light) ላይ የቆመ ኮንኮል (car) መብራቱ ሲለቀው፣ ከቆመበት ተነስቶ በመጠደፍ (accelerate) ባራት ኑሲቃ (4 seconds) ውስጥ ፍጥነቱ (speed) 60 ሃጃኖሜትር በሰዓት (60 kilometer per hour) ቢደርስ፣ የኮንኮሉ ጠደፋ (acceleration) ምን ያህል ነው?  ሎን (traffic) የሚለው ቃል የተገኘው ሎን (መንጋ) ከሚለው የአሮምኛ ቃል ነው።  ከዚህም ሎን ውጀ (traffic police) ወይም ባጭሩ ሎንጀ (traffic) የሚለውን ቃል እናገኛለን።  ውጀ (police) ማለት ባራዳ ቋንቋ ፖሊስ (police) ማለት ነው። 

ምሳሌ፤ በ 120 km/h ይግለበለብ የነበረ ሞከኛ (motorcyclist) ከፊት ለፊቱ አደጋ አየና በሁለት ኑሲቃ (2 seconds) ውስጥ ብቻ ፍጥነቱን ከ 120 km/h ወደ 40 km/h ቢያወርድ፣ የሞከኛው ጠደፋ (acceleration) ምን ያህል ነው?   ክሌ (ሁለት)[bi] እና ኡዋጅ (የሚኦድ) [cycle] ከሚለው ክሏጅ (bicycle) የሚለውን ቃል እናገኛለን።  ከዚህ ሞተር ክሏጅ (motorcycle) ወይም ባጭሩ ሞክ (motorcycle) የሚለውን ቃል እናገኛለን። 

ምሳሌ፤ 30 m/s በሆነ ፍጥነት ወደ ግድግዳ በራኬት (racquet, racket) የተለጋ የቴኒስ ኳስ (tennis ball) ከግድግዳው ጋር 90o በመሥራት ተጋጨና በ 26 m/s ፍጥነት በተቃራኒ አቅጣጫ ነጥሮ ተመለሰ።  የግጨቱ ጊዜ (collision time) 20 ሃጢኖኑሲቃ (20 millisecond) ብቻ ቢሆን፣ በዚህ ግጭት ላይ የኳሱ ጠደፋ (acceleration of the ball) ምን ያህል ነው?

ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት (Uniformly Accelerated Motion, UAM)

  1. ቶኪማ ሑሰት (uniform motion) ማለት በቋሚ ሶፊሳ የሚካሄድ ሑሰት (motion with constant velocity) ማለት እንደሆነ ተመልክተናል። 
  2. በሌላ አባባል ቶኪማ ሑሰት (uniform motion) ማለት በቀጥታ መስመር (straight line)) ላይ ባንድ አቅጣጫ (in one direction) እና በቋሚ ፍጥነት (constant speed) የሚካሄድ ሑሰት (motion) ማለት ነው።
  3. በሌላ በኩል ደግሞ ቶኪማ ሑሰት (uniform motion) ያልሆነ ሑሰት (motion) ጥዱፍ ሑሰት ወይም ጠደፋ ሑሰት (accelerated motion) እንደሚባል ተመልክተናል።
  4. በሌላ አባባል ጠደፋ ሑሰት (accelerated motion) ማለት በጠደፋ (accelerating) የሚካሄድ፣ ማለትም ጠደፋ (acceleration) ያለው ሑሰት ማለት ነው። 
  5. በጠደፋ  ሑሰት (accelerated motion) ላይ ጠደፋው በብክረትም (magnitude) ባቅጣጫም (direction) ቋሚ (constant) ከሆነ፣ ሑሰቱ በልዩ ስም ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት (uniformly accelerated motion, UAM) ወይም ቋሚ ጠደፋ ሑሰት (constant acceleration motion) ወይም ባጭሩ ቋጠሑ ይባላል።
  6. በሌላ አባባል ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት (uniformly acceleratd motion) ማለት በቶኪማ ጠደፋ (uniform acceleration) ወይም ቋሚ ጠደፋ (constant acceleration) የሚካሄድ ሑሰት ማለት ነው። 

አንድ ስፍረታዊ ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት (One Dimensional UAM)

  1. በቀጤ መስመር (straight line) ላይ የሚካሄድ ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት (uniformly motion accelerated) አንድ ስፍረታዊ ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት (one dimensional uniformly accelerated motion) ወይም አንድ ስፍረታዊ ቋሚ ጠደፋ ሑሰት (one dimensional constant acceleration motion) ይባላል።
  2.  አንድ ስፍረታዊ ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት አብዛኛውን ጊዜ የሚባለው ባጭሩ ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት ነው።  እኛም ካሁን በኋላ ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት ስንል አንድ ስፍረታዊ ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት ማለታቸን ነው። 
  3. አንድ ስፍረታዊ ቶኪማ ጠደፋ ሑሰትን በተመለከተ የሑሰቱን ጠደፋ (acceleration)፣ ባተሜ ሶፊሳ (initial velocity)፣ ፍጻሜ ሶፊሳ (final velocity)፣ እና ፍልሰት (displacement) የሚያዛምዱ ሰታብ (simple)፣ ማለትም ወታብ (complex) ያልሆኑ ቀላል እኩልታወች (equations) አሉ።  እነዚህም እኩልታወች የቶኪማ ጠደፋ ሑሰት እኩልታወች (equations of uniformly accelerated motion) በመባል ይታወቃሉ። 
  4. የቶኪማ ጠደፋ ሑሰት እኩልታወችን ቅልብጭ ባሉ መልኮች ለመግለጽ የሚከተለውን ስምምነት (convention) እንጠቀማለን።
    • ሑሰቱ የሚካሄድበትን ቀጤ መስመር (straight line) x-ረቲድ (x-axis) እንለዋለን።
    • በ x-ረቲድ (x-axis) ላይ ወንታ አቅጣጫ (positive direction) ወደ ቀኝ ሲሆን፣ ሉንታ አቅጣጫ (negative direction) ደግሞ ወደ ግራ ነው እንላለን።
    • የሑሰቱን ባተሜ ጊዜ (intial time) ዳዶ (zero) እናደርገዋለን፣ ማለትም t1 = 0 እንላለን።  በሌላ አባባል ሑሰቱን መተንተን በመንጀምርበት ቅጽበት (instant) ላይ ጊዜን ሀ ብለን መቁጠር እንጀምራለን።
    • የሑሰቱን ፍጻሜ ጊዜ (final time) t2 = t እንለዋለን። 
    • ስለዚህም የሑሰቱ የጊዜ ቃዳ (time interval) ማለትም ሑሰቱ የፈጀው ጊዜ
    • Δt=t2−t1=t−0=t\Delta t = t_2 – t_1 = t – 0 = t ይሆናል ማለት ነው።
    • የሑሰቱን ባተሜ አዴት (intial position) ዳዶ (zero) እናደርገዋለን፣ ማለትም x1 = 0 እንላለን።  በሌላ አባባል ሑሰቱ በሚጀምርበት ቅጽበት (instant) ላይ x = 0 ነው እንላለን። 
    • የሑሰቱን ፍጻሜ አዴት (final position) x2 = x እንለዋለን። 
    • ስለዚህም የሑሰቱ ፍልሰት  (displacement)
    • Δx=x2−x1=x−0=x\Delta x = x_2 – x_1 = x – 0 = xይሆናል ማለት ነው።
    • የሑሰቱን ባተሜ ሶፊሳ (initial velocity) v0 እንለዋለን
    • የሑሰቱን ፍጻሜ ሶፊሳ (final velocity) ደግሞ v እንለዋለን።

የቶኪማ ጠደፋ ሑሰት እኩልታወች (Equations of UAM)

  1. ለማናችውም አንድ ስፍረታዊ ቶኪማ ጠደፋ ሑሰት (one dimensional uniformly accelerated motion)  የሚያገለገሉ አራት እኩልታወች (four equations) አሉ። 
  2. እነዚህም እኩልታወች የቶኪማ ጠደፋ ሑሰት እኩልታወች (equations of uniformly accelerated motion) በመባል ይታወቃሉ። 
  3. በቶኪማ ጠደፋ ሑሰት ስምምነቶች (conventions) መሠረት አራቱ የቶኪማ ጠደፋ ሑሰት እኩልታወች በሚከተሉት መልኮች ይጻፋሉ። 
  4. ስለነዚህ እኩልታወች አረቻቸግ (derivation) ማለትም አገኛኘት እንዲሁም አጠቃቀም ወደፊት በሌሎች ጦማሮች ላይ በስፋት እናወሳለን።  ላሁኑ ግን ጥቂት ምሳሌወችን ብቻ እናያለን። 

ምሳሌ (የመቅደም ጠደፋና ርቀት)፤ በቀጤ ጎዳና ላይ የሚጓዝ ቤንኮል (car) ማለትም የቤት ኮንኮል (የቤት መኪና)፣ በዝግታ የሚጓዘን ጨንኮል (truck) ለማለፍ ፍጥነቱን ከ 60 km/h ወደ 70 km/h በሁለት ኑሲቃ (2s) ውስጥ በቋሚ ጠደፋ (constant acceleration) ቢጨምር፣ የቤንኮሉን ጠደፋ (acceleration) እንዲሁም ቤንኮሉ በዚህ የጠደፋ ጊዜ ውስጥ የተጓዘውን ጠቅላላ ርቀት (total distance) ፈልግ።  ኮንኮል (car) ማለት መኪና ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ኮንኮላታ (መኪና) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው።  ቤንኮል ማለት የቤት ኮንኮል ማለት ሲሆን፣ ጨንኮል ማለት ደግሞ የጭነት ኮንኮል ማለት ነው። 

ምሳሌ (ግታት ርቀት) [Braking distance]፤ በቀጤ ጎዳና ላይ በ 45 km/h የሚጓዝ ቤንኮል (car)፣ ከፊት ለፊቱ ያለው ሎን መብራት (traffice light) ወደ ቀይ ሲለወጥ ዓየና የኮንኮሉን ገች (brake) ሲረግጠው፣ ኮንኩሉ 5 m/s2 በሆነ ቋሚ ጠደፋ (constant acceleration) ፍጥነቱን መቀነስ ጀመረ።  ኮንኩሉ ገቹ ከተረገጠ በኋላ እስከሚቆም ድረስ የሚጓዘውን ግታት ርቀት (braking distance) ፈልግ። 

መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com