ማሳሰቢያ
ይህ ጦማር ማለትም ክፍል 6(ለ) ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው በሚቀድሙት ጦማሮች ማለትም ከፍሎች 1 እስከ 6(ሀ) ላይ ስለሆነ፣ ይህን ክፍል ከማንበብወ በፊት ክፍሎችን 1 እስክ 6(ሀ) በተለይም ደግሞ ስለ ቁነና ስርካቶች አሰረካከት (construction of measurement systems) የሚያወሳውን ክፍልን 3፣ ስለ ኑሲቃ ብያኔ (definition of the second) የሚያወሳውን ክፍልን 4 ፣ ስለ ሜትር ብያኔ (definition of the meter) የሚያወሳውን ክፍልን 5 እንዲሁም ስለ ሃጃኖግራም እና ሞል ብያኔወች (definitions of the kilogram and the mole) የሚያወሳውን ክፍልን 6(ሀ) ቢያንስ ቢያንስ በገረፍታ ይመልከቱ።
የቤቶስ ፊልጡፎች (SI Prefixes)
ክፍል 3 ላይ እንደተመለከተነው፣ ቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካትን (International System of Units) ከሌሎች የቶካድ ስርካቶች (Systems of Units) ይልቅ ለሰገል (science) እና ለምንደሳ (engineering) ተመራጭ ያደረገው ዋናው ጠባዩ የሚከተሉትን ያስር ርቢወች (powers of ten) እንደ ፊልጡ ፍ (prefix) በመጠቀም የማናቸውንም ቶካድ (unit) መጠን በተፈለገው ደረጃ ማተለቅ (increase) ወይም ማሳነስ (decrease) መቻሉ ነው።
ወርከፍ (Size)፣ ስፋት (Area) እና ጽሐር (Volume)
ወርከፍ (size) ማለት መጠን፣ ትልቅነት፣ ግዝፈት ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ወርድ ፣ ርዝመት እና ከፍታ ከሚሉት ነው። ለምሳሌ ያህል የምድር ወርከፍ ከጨረቃ ወርከፍ የበለጠ ሲሆን፣ ከፀሐይ ወርከፍ ያነሰ ነው።
ጽሐር (volume) ማለት ይዘት እንደ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ጽሐርት (ማለትም ድስት) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው። ለምሳሌ ያህል የሳጥን ጽሐር ማለት የሳጥኑ ይዘት ማለት ሲሆን፣ የሚገኘውም የሳጥኑን ወርድ፣ ርዝመትና ከፍታ በመበዘር (multiply) ማለትም በማባዛት ነው።
ዓይነተኛ የጽሐር ቶካዶች (units of volume) ሜትር ሳልቶና (meter cubed, cubic meter)፣ ቶሲሜትር ሳልቶና (centimeter cubed, cubic centimeter) እና ሃድጢኖሜትር ሳልቶ ና (millimeter cubed, cubic millimeter) ናቸው።
ሜትር ሳልቶና (meter cubed) ባጭሩ ሜሳ ፣ ቶሲሜትር ሳልቶና (centimeter cubed, cc) ባጭሩ ቶሲሜሳ ፣ ሃድጢኖሜትር ሳልቶና (millimeter cubed) ደግሞ ባጭሩ ሃጢሜሳ ይባላል።
ዓይነተኛ የስፋት ቶካዶች (units of area) ሜትር ካልቶና (meter squared, square meter)፣ ቶሲሜትር ካልቶና (centimeter squared, square centimeter) እና ሃድጢኖሜትር ካልቶና (millimeter squared, square millimeter) ናቸው።
ሜትር ካልቶና (meter squared) ባጭሩ ሜካ ፣ ቶሲሜትር ካልቶና (centimeter squared) ባጭሩ ቶሲሜካ ፣ ሃድጢኖሜትር ካልቶና (millimeter squared) ደግሞ ባጭሩ ሃጢሜካ ይባላል።
ሌላው የስፋት ቶካድ ቶሳር (hectare) ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ቶሳ (hecto) ከሚለው የቁጥር ፊልጡፍ ነው።
ቶሳር ( hectare) ማለት መቶ ሜትር (100 meter) በመቶ ሜትር (100) የሆነ ካልቶና (square) ስፋት (area) ማለት ነው።
በሌላ አባባል ቶሳር (hectare) ማለት እሴቱ አስር ሺ ሜካ (10,000 meter squared) የሆነ ስፋት ማለት ነው።
ለምሳሌ ያህል አንድ ጋሻመሬት በቅርበዛ 40 ቶሳ (40 hectar) ነው።
ለስሌት (calculation) እንዲመቸን ግን ጋሻን እንዳዲስ በመበየን (define) አንድ ጋሻ እቅጩን (exactly) 100 ቶሳር (100 hectare) ነው ልንል እንችላለን።
በዚህ ብያኔ መሠረት ደግሞ አንድ ጋሻ መሬት ማለት አንድ ሃጃኖሜትር (one kilometer) በአንድ ሃጃኖሜትር (one kilometer) የሆነ ካልቶና (square) ስፋት (area) ማለት ይሆናል።
ይህ ብያኔ በሜትር ካልቶና (meter squared) ሲገለጽ ደግሞ አንድ ጋሻ ሜትር ማለት አንድ ካልጃኖ ሜካ (one million meter squared) ማለት ይሆናል።
ዘከብ (Environment)
ዙርያ እና ክብ ከሚሉት ዘከብ (environment, environ) የሚለውን እናገኛለን። ዘከብ (environment) ማለት አካባቢ የምንለው ነው።
የዘከብ (environment) ግስ ሲረባ ዘከበ (to environ)፣ ዝክብ ( ዝኩብ ) [environed]፣ ዘካቢ (environing)፣ ዝከባ (environing)፣ ዝክበት፣ ዝካቤ፣ ዝካቦሽ እያለ ይሄዳል።
ዘከበ (to environ) ማለት ዘከብ ሠራ፣ ዙርያ ከበበ እንደ ማለት ሲሆን፣ ዝክብ ( ዝኩብ ) ማለት ደግሞ የተዘከበ ማለት ነው።
ዘከብ (environment) ከሚለው ዘከብ ሰገል (environmental science)፣ ዘከብ ጉሲን (environmental physics)፣ ዘክብ ፓካርሲን (environmental chemistry)፣ ዘከበኛ (environmentalist)፣ ዘከበኛነት (environmentalism) የመሳሰሉትን ቃሎች እናገኛለን።
environment (environ) = ዘከብ environmental = ዘከባዊ environmental science = ዘከብ (ዘከባዊ) ሰገል environ (verb) = ዘከበ
ብዘራ (Multiplication)፣ ድሸራ (Division) እና ርሻር (Ratio)
ማባዛት የሚለው ቃል ግሱን ለማርባት የሚያስቸግር ከመሆኑም በላይ፣ ብዙ አደረገ የሚል ተጨማሪ ትርጉም ስላለውና ሊያደናግር ስለሚችል፣ ብዘራ (multiplication) እንለዋለን።
ብዘራ (multiplication) የሚለው ቃል የተገኘው አበዛ እና ደመረ ከሚሉት ነው፣ ማባዛት ማለት በተከታታይ መደመር ማለት ነውና።
የብዘራ (multiplication) ግስ ሲረባ በዘረ (multiply)፣ ብዝር (ብዙር ) [multiplied]፣ በዛሪ (multiplier)፣ ብዘራ (multiplication)፣ ብዝረት ፣ ብዛሬ ፣ ብዛሮሽ እያለ ይሄዳል።
የብዘራ (multiplication) ውጤት ማለትም በመበዘር የሚገኝ እሴት ብዜር (product, multiple) ይባላል።
በተመሳሳይ መንገድ ማካፈል የሚለው ቃል ግሱን ለማርባት የሚያስቸግር ከመሆኑም በላይ፣ አከፋፈለ የሚል ተጨማሪ ትርጉም ስላለውና ሊያደናግር ስለሚችል፣ ድሸራ (division) እንለዋለን።
ድሸራ (division) የሚለው ቃል የተገኘው ድርሻ ከሚለው በመነሳትና ድመራ እና ብዘራ የሚሉትን ቃሎች አካሄድ በመከተል ነው።
የደሸራ (division) ግስ ሲረባ ደሸረ (divide)፣ ድሽር (ድሹር ) [divided]፣ ደሻሪ (divider)፣ ድሸራ (division)፣ ድሽረት ፣ ድሻሬ ፣ ድሻሮሽ እያለ ይሄዳል።
የድሸራ (division) ውጤት ማለትም በመደሸር የሚገኝ እሴት ድሻር (quotient) ይባላል።
ሬሽዮ ከሚለው የንግሊዘኛ ቃል በመነሳትና ድሻር (divide) የሚለውን ቃል አካሄድ በመከተል ርሻር (ratio) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ርሻር (ratio) ከድሻር (quotient) ጋር ተምሳሳይ ስሌት ( same calculation) ያለው ቢሆንም፣ አጠቃቀሙ ግን የተለየ ነው።
ርሻር (ratio) የሚያገለግለው እንደ ድሻር (quotient) የደሸራ ውጤትን (result of division) ለመወከል ሳይሆን፣ ንጽጽራዊ ትልቀትን (comparative size) ለመግለጽ ነው።
የርሻር (ratio) ግስ ሲረባ ረሸረ፣ ርሽር (ርሹር)፣ ረሻሪ፣ ርሸራ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘና አቻ የለውም።
ረሸረ ማለት በርሻር መልክ ገለጸ ማለት ሲሆን፣ ርሽር (ርሹር) ማለት ደግሞ የተረሸረ ማለት ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ የሆስሌት መሠረታዊ ሁጀማወች (The Fundamental Operations of Algebra) የሚለውን ጦማር ይመልከቱ።
የብዘራ ነታኖች (Multiplication Factors)
በማናቸውም ብዘራ (multiplier) ላይ የሚበዝረው ክፍል በዛሪ (multiplier) ሲባል የሚበዘረው ክፍል ደግሞ ተበዛሪ (multiplicand) ይባላል።
በዛሪ (multiplier) እና ተበዛሪ (multiplicand) ሁለቱም የብዘራ ነታኖች (multiplication factors) ወይም ባጭሩ ነታኖች (factors) ይባላሉ።
ነታን (factor) የሚለው ቃል የተገኘው ተነተነ ከሚለው ቃል ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ነተነ (to factor)፣ ንትን ( ንቱን ) [factored]፣ ነታኒ ( ነታኝ ) [factoring, factorizing]፣ ንተና (factoring, factorization)፣ ንትነት፣ ንታኔ፣ ንታኖሽ እያለ ይሄዳል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ የሆስሌት መሠረታዊ ሁጀማወች (The Fundamental Operations of Algebra) የሚለውን ጦማር ይመልከቱ።
factor = ነታን factor (factorize) = ነተነ factoring (factorization) = ንተና common factor = ወል ነታን greatest common factor (GCF) = መልዕል ወል ነታን (መልነታን) factorial = ነታኔት
እፍግ (Dense) እና እፍገት (Density)
ባማረኛ አፈገ ማለት አጠጋጋ፣ ጠቀጠቀ፣ አቸፈገ ማለት ነው። ይህም ያማረኛ ቃል make dense የሚለውን እንግሊዘኛ ይተካልናል።
አፈገ ከሚለው ደግሞ እፍግ (dense) እና እፍገት ( እፍጋት ) [density] የሚሉት ቃሎች እናገኛለን።
የተለያዩ ዓይነት እፍገቶች (densities) አሉ። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።
dense = እፍግ፣ እፉግ density = እፍገት፣ እፍጋት atmospheric density = ከባየር እፍገት population density = አሕዛብ እፍገት mass density = ቁሰት እፍገት current density = ጀማ እፍገት energy density = ጉልበት እፍገት flux density = ጉርፈት እፍገት charge density = ጸውሪክ እፍገት linear density = ቄጠማዊ እፍገት surface density = ጸጸፋዊ እፍገት volume density = ጽሐራዊ እፍገት
ቁሰት እፍገት (Mass Density)
ቁሰት እፍገት (mass density) የቁሰትን (mass) ትፍፍገት ማለትም ጠቅጥቀት ወይም ችፍገት የሚገልጽ ቃል ነው።
የማናቸም አካል ቁሰት እፍገት (mass density) የሚገኘው የአካሉን ቁሰ ት (mass) በአካሉ ጽሐር (volume) በመደሸር (divide) ማለትም በማካፈል ነው።
በሌላ አባባል የማናቸውም አካል ቁሰት እፍገት (mass density) ያካሉ ቁሰት (mass) እና ጽሐር (volume) ርሻር (ratio) ነው።
በዚህም ምክኒያት ቁሰት እፍገት (mass density) ቁሰት በቶካድ ጽሐር (mass per unit volume) ነው ይባላል።
ከሌሎች ዓይነት እፍገቶች (other types of densities) ጋር መደናገር (confusion) ሊፈጠር በማይችልበት ሁኔት ላይ ቁሰት እፍገት (mass density) አብዛኛውን ጊዜ የሚታወቀው ባጭሩ እፍገት (density) በመባል ነው።
በሌላ አባባል እፍገት (density) በሚባልበት ጊዜ ሌላ ዓይነት እፍገት መሆኑ በግልጽ እስካልተቀመጠ ድረስ ቁሰት እፍገት (mass density) ማለት ነው።
የቁስ እፍገት (mass density) ወይም ባጭሩ እፍገት (density) ወመል (symbol) ማለትም ወካይ ምልከት የግሪክ ፊደል (ρ) ሲሆን፣ ስሙም ሮ (rho) ነው።
ዘንዳቢ (Extensive) እና አልዘንዳቢ (Intensive) ናይባወች (Quantities)
ባማረኛ ዘንደበ ማለት አረዘመ፣ በሩቅ መታ ማለት ነው። ይህም ያማረኛ ቃል extend የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
ግሱም ሲረባ ዘነደበ (extend)፣ ዝንድብ (ዝንዱብ) [extended]፣ ዘንዳቢ (extending)፣ ዝንደባ (exten)፣ ዝንድበት፣ ዝንዳቤ፣ ዝንዳቦሽ እያለ ይሄዳል።
ዘነደበ (extend) ከሚለው ቃል ዘንዳቢ ናይባ (extensive quantity) እና አልዘንዳቢ ናይባ (intensive quantity) እንዲሁም ዘንዳቢ ጠባይ (extensive property) እና አልዘንዳቢ ጠባይ (intensive property) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
ዘንዳቢ ናይባ (extensive quantity) ወይም ዘንዳቢ ጠባይ (extensive property) ማለት በወርከፍ (size) ማለትም በግዝፈት ላይ የሚመይፍ (depend) ማለትም የሚመካ ናይባ (quantity) ወይም ጠባይ (property) ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል
ቁሰት (mass) ዘንዳቢ ናይባ (extensive quantity) ነው፣ የማናቸውም አካል ቁሰት (mass) ባካሉ ወርከፍ (size) ማለትም ግዝፈት ላይ ይመይፋልና።
ትንሽ ወርቅ እና ትልቅ ወርቅ ሁለቱም ወርቆች ቢሆኑም፣ ወርከፋቸው ስለሚበላለጥ ግን ቁሰታቸውም ይበላለጣል።
በሌላ በኩል ደግሞ አልዘንዳቢ ናይባ (intensive quantity) ወይም አልዘንዳቢ ጠባይ (intensive property) ማለት በወርከፍ (size) ማለትም በግዝፈት ላይ የማይመይፍ (independent) ማለትም የማይመካ ናይባ (quantity) ወይም ጠባይ (property) ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል በሚቀጥለው ክፍል ላይ
ቁሰት እፍገት (mass density) አልዘንዳቢ ናይባ (intensive) ነው፣ የማናችውም ቶታን (substance) ቁሰት እፍገት (mass density) በቶታኑ ወርከፍ (size) ማለትም ግዝፈት ላይ የማይመይፍ የቶታኑ ቋሚ ጉሲናዊ ጠባይ (constant physical property) ነውና።
ወርቅ ትንሽም ሆነ ትልቅ ቁሰት እፍገቱ (mass density) ያው ነው።
extend = ዘንደበ extensive = ዘንዳቢ extensive property = ዘንዳቢ ጠባይ extensive quantity = ዘንዳቢ ናይባ intensive property = አልዘንዳቢ ጠባይ intensive quantity = አልዘንዳቢ ናይባ
ቁሰት እፍገት (Mass Density) እንደ አልዘንዳቢ ናይባ (Intensive Quantity)
ቁሰት እፍገት (mass density) ቁሰትን (mass) በጽሐር (volume) በመደሸር (divide) ማለትም በማካፈል የሚገኝ የቁሰት እና የጽሐር ርሻር (the ratio of mass and volume) ነው ተብሎ ቢበየንም (defined)፣ በቁሰት (mass) እና በጽሐ ር (volume) ላይ ግን አልምይፍ (independent) ነው ማለትም አይመካም።
በሌላ አባባል የማናቸውም ቶታን (substance) ቁሰት እፍገት (mass density) በቶታኑ ቁሰት (mass) ወይም ጽሐር (volume) ላይ የማይመይፍ (independent) ማለትም የማይመካ የቶታኑ ቋሚ ጉሲናዊ ጠባይ (constant physical property) ነው።
አሁንም በሌላ አባባል የማናቸውም ቶታን (substance) ቁሰት እፍገት (mass density) በቶታኑ ወርከፍ (size) ላይ የማይመይፍ (independent) የቶታኑ አልዘንዳቢ ጠባይ (intensive property) ነው።
ለምሳሌ ያህል ከንጽሕ ወርቅ (pure gold) የተሠሩ ነገሮች ሁሉ እንደ ወርከፋቸው (size) ማለትም ግዝፈታቸው መለያየት ቁሰታቸው (masses) ቢለያይም፣ ቁሰት እፍገታቸው ( mass density) ግን የሁሉም እኩል ነው።
የማናቸውም ቶታን (substance) ቁሰት እፍገት (mass density) የቶታኑን ቁሰት (mass) በቶታኑ ጽሐር (volume) በመደሸር (divide) ማለትም በማካፈል የሚገኝ እሴት ቢሆንም፣ በቶታኑ ቁሰት ወይም በቶታኑ ጽሐር ላይ የማይመይፍ ቋሚ እሴት የሆነበት ምክኒያት፣
የቶታኑ ጽሐር ( volume) በሆነ ነታን (factor) ቢለወጥ፣ የቶታኑ ቁሰትም በዚያው ነታን (same factor) ስለሚለወጥ ነው።
ማለትም የቶታኑ ጽሐር (volume) በሆነ ቁጥር ተበዝሮ (ተባዝቶ) ቢጨምር ወይም ቢቀንስ፣ የቶታኑ ቁሰትም (mass) በዚያው ቁጥር ተበዝሮ (ተባዝቶ) ስለሚጨምር ወይም ስለሚቅንስ ነው።
ለምሳሌ ያህል የቶታኑ ጽሐር (volume) በሁለት እጥፍ (two times) ቢጨምር ፣ የቶታኑ ቁሰትም (mass) በሁለት እጥፍ (two times) ስለሚጨምር ፣ የቶታኑ ቁሰት እና ጽሐር ርሻር (ratio of mass and volume) አይለወጥም ።
የቁሰት እፍገት ቤቶስ ቶካድ (SI Unit of Mass Density)
የቁስ እፍገት (mass density) እሴት የሚገኘው ቁስን (mass) በጽሐር (volume) በመደሸር (divide) ማለትም በማካፈል ነው።
ስለዚህም የቁስ እፍገት ቤቶስ ቶካድ (SI unit of mass density) የሚገኘው የቁስን ቤቶስ ቶካድ (SI unit of mass) በጽሐር ቤቶስ ቶካድ (SI unit of volume) በመደሸር (divide) ማለትም በማካፈል ነው።
የቁስ ቤቶስ ቶካድ (SI unit of mass) ሃጃኖግራም (kilogram) ሲሆን፣ የጽሐር ቤቶስ ቶካድ (SI unit of volume) ደግሞ ሜትር ሳልቶና (meter cubed) ነው።
ስለዚህም የቁስ እፍገት ቤቶስ ቶካድ (SI unit of mass density) ሃጃኖግራም በሜትር ሳልቶና (kilogram per meter cubed, kg/m3 ) ነው ማለት ነው።
በሌላ አባባል በቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት (International System of Units) ወይም ቤቶስ (SI system) ላይ የቁስ እፍገት (mass density) የሚገለጸው በሃጃኖግራም ሜትር ሳልቶና ነው።
በሌላ በኩል ግን የቁስ እፍገት (mass density) አብዛኛውን ጊዚ የሚገለጸው በሃጃኖግራም ሜትር ሳልቶና (kilogram per meter cubed, kg/m3 ) ሳይሆን በግራም ቶሲሜትር ሳልቶና (gram per centimeter cubed, g/cm3 ) ነው።
በግራም ቶሲሜትር ሳልቶና (gram per centimeter cubed, g/cm3 ) የተገለጸን የቁስ እፍገት (mass density) በሃጃኖግራም ሜትር ሳልቶና (kilogram per meter cubed, kg/m3 ) ለመግለጽ የሚያስፈልገው ባንድ ሺ (1000) መበዘር (multiply) ማለትም ማባዛት ብቻ ነው።
ለምሳሌ ያህል የአሉሚነም (Aluminum) የቁስ እፍገት (mass density) በግራም ቶሲሜትር ሳልቶና (gram per centimeter cubed, g/cm3 ) ሲገለጽ 2.7 g/cm3 ስለሆነ፣ በሃጃኖግራም ሜትር ሳልቶና (kilogram per meter cubed, kg/m3 ) ሲገለጽ 2700 kg/m3 ይሆናል።
ምሳሌ፡ ጽሐሩ (volume) 0.2 cm3 በሆነ ንጹሕ የሱፒዛ (aluminum) ናሙና (sample) ውስጥ ስንት የሱፒዛ ቀኒጦች (atoms of aluminum) አሉ? ሱፒዛ (aluminum) የሚለው ቃል የተገኘው ሱጴ (ማለትም ሸክላ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው።
ፀናራዊ እፍገት (Relative Density)
አንጻር የሚለውን ቃል ለማርባት ይመቸን ዘንድ አብዛኛው ጊዜ ፀናር (relative) እንለዋለን።
ግሱም ሲረባ ፀነረ፣ ፅንር (ፅኑር)፣ ፀናሪ፣ ፀነራ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
ፀነረ ማለት አነፃፀረ ማለት ነው።
ፀናራዊ (relativistic) ማለት ንጽጽራዊ ማለት ነው።
ፀናራዊነት (relativity) ማለት ደግሞ ንጽጽራዊነት ማለት ነው፣ የፀናራዊነት ግንገና (theory of relativity) እንዲሉ።
የማናቸውም ቶታን (substance) ፀናራዊ እፍገት (relative density) ማለት የቶታኑ እፍገ ት (density of the substance) በውሃ እፍገት (density of water) ሲደሸር (divided) ማለትም ሲካፈል የሚገኘው እሴት ማለት ነው።
በሌላ አባባል የቶታን ፀናራዊ እፍገት (relative density of a substance) ማለት የቶታኑ እፍገት (density of the substance) እና የውሃ እፍገት (density of water) ርሻር (ratio) ማለት ነው።
የፀናራዊ እፍገት (Relative Density) እሴት
ፀናራዊ እፍገት (relative density) እፍገትን በእፍገት በመደሸር (dividing density by density) ማለትም በማካፈል የሚገኝ እሴት ስለሆነ፣ ቶካድ (unit) የሌለው ማለትም ቶካድቢስ (unitless) የሆነ ቁጥር ነው።
በዚህም ምክኒያት ፀናራዊ እፍገት (relative density) ስፍረታልባ ( dimensionless) ነው ይባላል።
የውሃ እፍገት (density of water) 1 g/cm3 ስለሆነ፣ የማናቸውም ቶታን (substance) ፀናራዊ እፍገት (relative density) የቶታኑ እፍገት (density) በግራም ቶሲሜትር ሳልቶና (gram per centimeter cubed, g/cm3 ) ሲገለጽ ያለው እሴት ይሆናል።
ለምሳሌ ያህል የወርቅ እፍገት (density of gold) በግራም ቶሲሜትር ሳልቶና (gram per centimeter cubed, g/cm3 ) ሲገለጽ 19.3 g/cm3 ስለሆነ፣ የወርቅ ፀናራዊ እፍገት (relative density of gold) 19.3 ይሆናል።
በተመሳሳይ መንገድ የመዳብ እፍገት (density of copper) በግራም ቶሲሜትር ሳልቶና (gram per centimeter cubed, g/cm3 ) ሲገለጽ 8.9 g/cm3 ስለሆነ፣ የመዳበ ፀናራዊ እፍገት (relative density of gold) 8.9 ይሆናል።
የፀናራዊ እፍገት (Relative Density) ሌላ ብያኔ (Another Definition)
የማናቸውም ቶታን (substance) ፀናራዊ እፍገት (relative density) ማለት የቶታኑ እፍገት (density of the substance) በውሃ እፍገት (density of water) ሲደሸር (divided) ማለትም ሲካፈል የሚገኘው እሴት ነው ተብሎ እንደሚበየን (defined) አይተናል።
ከዚህ ብያኔ (definition) ጋር አቻ (equivalent) በሆነ ሌላ አበያየን (definition) ደግሞ የማናቸውም ቶታን ፀናራዊ እፍገት (relative density of a substance) ማለት እኩል ጽሐር (equal volume) ያላቸው የቶታኑና የውሃ ቁቶች (masses) ርሻር (ratio) ነው ተብሎ ሊበየን (defined) ይችላል።
በሌላ አባባል የቶታን ፀናራዊ እፍገት (relative density of a substance) ማለት የቱታኑ ቁሰት (mass of substance) ከቶታኑ ጋር እኩል ጽሐር (equal volume) ካለው የውሃ ቁስበት (mass of water) ምን ያህል እንደሚበልጥ የሚያሳይ እሴት ማለት ነው።
ለምሳሌ ያህል የሱፒዛ (aluminum) ፀናራዊ እፍገት (relative density) 2.7 ነው ማለት፣ የማናቸውም ሱፒዛ (aluminum) ናሙና (sample) ቁሰት (mass) ከሱፒዛው ናሙና ጋር እኩል ጽሐር (equal volume) ያለው ውሃ ካለው ቁሰት (mass of water) 2.7 ጊዜ ይበልጣል ማለት ነው።
ስንፈፋ (Floatation)
ተንሳፈፈ (float) የሚለውን ለማርባት ይመቸን ዘንድ ሰነፈፈ (float) እንለዋለን።
ግሱም ሲረባ ሰነፈፈ (to float)፣ ስንፍፍ ( ስንፉፍ ) [floated]፣ ሰንፋፊ (floating, floater)፣ ስንፈፋ (floating, floatation)፣ ስንፍፈት፣ ስንፋፌ፣ ስንፋፎሽ እያለ ይሄዳል።
float = ሰንፈፍ፣ ተንሳፋፊ float (verb) = ሰነፈፈ፣ ተንሳፈፈ floatable (floatability) = ሰንፋፊ፣ ሰንፋፊነት፣ ተንሳፋፊ፣ ተንሳፋፊነት floating = ሰንፋፊ፣ ተንሳፋፊ floating decimal = ሰንፋፊ አሴንታ፣ ተንሳፋፊ አሴንታ floatation = ስንፈፋ law of floatation = የሰንፈፋ ሕግ
ፈጋስ (Fluid) እና ፈጋሲን (Fluidics)
ፈሳሽ (liquid) እና ጋስ (gas) ከሚሉት ፈጋስ (fluid) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ፈጋስ (fluid) የፈሳሽ (liquid) እና የጋስ (gas) የወል ስም (common name) ማለትም የጋራ ስም ነው።
በሌላ አባባል ፈጋስ (fluid) ማለት ፍሳሽ (liquid) እና/ወይም (and/or) ጋስ (gas) ማለት ነው።
አሁንም በሌላ አባባል ፈጋስ (fluid) ስንል ፈሳሽ (liquid) ወይም ጋስ (gas) ወይም ሁለቱንም ማለታችን ሊሆን ይችላል።
የፈጋስ (fluid) ግስ ሲረባ ፈገሰ (fluidify, fluidize)፣ ፍግስ ( ፍጉስ ) [fludified, fludized]፣ ፈጋሲ ( ፈጋሽ ) [fludifier, fluidizer]፣ ፍገሳ (fluidification, fluidization)፣ ፍግሰት ፣ ፍጋሴ ፣ ፍጋሶሽ እያለ ይሄዳል።
ፈገሰ (fluidify, fluidize) ማለት ፈጋስ (fluid) ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ፍግስ (ፍጉስ) [fluidified, fluidized] ማለት ደግሞ የተፈገሰ ማለት ነው።
ፈጋሲን (fluidics) ማለት የፈጋስ (fluid) ጥናት ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ፈጋስ (fluid) እና ሲን (logy) ከሚሉት ነው።
ፈጋሲነኛ (one who studies fluidics) ማለት ደግሞ የፈጋሲን (fluidics) ባለሙያ ማለት ሲሆን፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም
fluid = ፈጋስ fluid dynamics = ፈጋስ ሒሲን fluid mechanics = ፈጋስ ሐምሲን fluidic = ፈጋስ፣ ፈጋሳዊ fluidics = ፈጋሲን fluidify (fluidize) = ፈገሰ fludification (fluidization) = ፍገሳ
ፀናራዊ እፍገት (Relative Density) እና የስንፈፋ ሕግ (Law of Floatation)
ማናቸውም አካል (object) ውሃ ላይ ይሰነፈፍ (float) ማለትም ይንሳፈፍ ዘንድ የሚያስፈልገው የአካሉ ፀናራዊ እፍገት (relative density of the object) ከቶኮ (one = 1) ያነስ መሆን ብቻ ነው።
ይህም ሐቅ (fact) የስንፈፋ ሕግ (law of floatation) ይባላል።
ባጠቃላይ አነጋገር ደግሞ ማናቸውም አካል (any object) በማናቸውም ፈጋስ (any fluid) ላይ ይሰነፍፍ (float) ማለትም ይንሳፈፍ ዘንድ፣ አካሉ ከዚያ ፈጋስ አንጻር (relative to the fluid) ያለው ፀናራዊ እፍገት (relative density) ከቶኮ ያነሰ (less than one) መሆን አለበት።
ማለትም የአካሉ እፍገት (density of the object) በፈጋሱ እፍገት (density of the fluid) ሲደሸር (divided) ማለትም ሲካፈል የሚገኘው እሴት ከቶኮ ያነሰ ( less than one) መሆን አለበት።
ለምሳሌ ያህል የቤንዚን (benzene) እፍገት (density) 0.88 g/cm3 ስለሆነ፣ ማናቸው አካል ቤንዚን ላይ የሰነፍፍ (float) ማለትም ይንሳፈፍ ዘንድ እፍገቱ (density) ከ 0.88 g/cm3 ያነሰ መሆን አለበት ።
በተመሳሳይ መንገድ ፀናራዊ እፍገቶቻቸው (relative densities) እየቀነሱ የሚሄዱ የተለያዩ ፈሳሻችን (liquids) ላይ በላይ በመደራረብ የእፍገት ፎቅ (density tower) ወይም የእፍገት ሃፊድ (density tower) መሥራት ይቻላል። ሃፊድ (tower) የሚለው ቃል የተገኘው መኅፊድ (ረዥም ግንብ) ከሚለው ቃል ነው።
ልይት (Specific) እና ሁልት (Generic )
ልዩ ከሚለው ልይት (specific) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ልየት (specific) ማለት በስም የተጠቀሰ፣ በግል የተለየ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ለየተ (specify)፣ ልይት (specified)፣ ለያቲ ( ለያች ) [specifying]፣ ልየታ (specifying)፣(specifying, specification)፣ ልያቴ፣ ልያቶሽ እያለ ይሄዳል።
ልይት (specific) የሚለውን ቃል አካሄድ በመከተል፣ ሁሉ ም ከሚለው ሁልት (generic) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ሁልት ( generic) ማለት የሁሉም፣ ለሁሉም ማለት ነው።
የሁልት (generic) ግስ ሲረባ ሆለተ፣ ሁልት፣ ሆላቲ፣ ሁለታ፣ ሁላቴ፣ ሁላቶሽ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
ሁልት (specific) እና ሁለት (two) እንዳይምታቱብወት።
specific (specified) = ልይት specify = ለየተ specificity = ልይትነት specifier = ለያቲ፣ ለያች specification = ልየታ specific gravity = ልይት ቁስበት specific heat capacity = ልይት የግለት ዐቅም specific humidity = ልይት ወበቅ generic = ሁልት generic medicine = ሁልት መድሐኒት
ልይት ቁስበት (Specific Gravity)
የፀናራዊ እፍገት (relative density) የቀድሞ ስሙ ልይት ቁስበት (specific gravity) ነበር።
ልይት (specific) የተባለበት ምክኒያት ማናቸውም ቶታን (any substance) ካለው እፍገት (density) ጋር ሳይሆን፣ ልይት (specific) የሆነ ቶታን (substance) ማለትም ውሃ (water) ካለው እፍገት (density) ጋር ስለሚነጻጸር ነው።
ቁስበት (gravity) የተባለበት ምክኒያት ደግሞ በቀድሞ ጊዜ ቁስበት (gravity) ሲባል ከብደት (weight) ወይም ከባድነት (heaviness) ማለት ስለነበረ ነው።
ልይት ቁስበት (specific gravity) እየተተወና መተውም ያለበት፣ ያረጀና ያፈጀ ስያሜ ነው።
መስፍን አረጋ mesfinamharic.com mesfin.arega@gmail.com