ማሳሰቢያ
ይህ ጦማር (ማለትም ክፍል 5) ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው በሚቀድሙት ጦማሮች (ማለትም ከፍሎች 1 እስከ 4) ላይ ስለሆነ፣ ይህን ክፍል ከማንበብወ በፊት ክፍሎችን 1 እስክ 4 በተለይም ደግሞ ስለ ቁነና ስርካቶች አወቃቀር (construction of measurement systems) የሚያወሳውን ክፍልን 3 እንዲሁም ስለ ኑሲቃ ብያኔ (definition of the second) የሚያወሳውን ክፍልን 4 ቢያንስ ቢያንስ በገረፍታ ይመልከቱ።
ሜትር ወይም ሚትር (Meter)
- በቤንቤራዊ የቶካዶች ስርካት (international system of units) ወይም ቤቶስ (SI system) ላይ የርዝመት ደርክ ቶካድ (the standard unit of length) በልዩ ስም meter ይባላል።
- ባማረኛ ደግሞ meter የሚለውን እንዳመችነቱ ሜትር ወይም ሚትር እንለዋለን።
- በሌላ አባባል ባማረኛ ላይ ሜትር እና ሚትር የሚሉት ቃሎች ያውቴ (same) ትርጉም ያላቸው ተመሳሳይ ቃሎች ናቸው።
- ሜትር (meter, metre) የሚለው ቃል የተገኘው ሜትሮን (metron) ማለትም መለካት (መቆነን) ከሚለው የግሪክኛ ቃል ነው።
የሜትር (Meter) ብያኔ በፕላቲነም ዘንግ (Platinum Rod)
- ሜትር (meter) የሚባለው የርዝመት ደርክ ቶካድ (standard unit of length) የተበየነው (defined) በ1786 ዓ. ም ላይ በፈረንሳይ የሰገሎች ዋሸራ (French Academy of Sciences) ነበር።
- በዚህ ብያኔ መሠረት አንድ ሜትር (one meter) ማለት በፈረንሳይ አገር በተቀመጠ የብረት ዘንግ (metal rod) ዳር እና ዳር አካባቢ በተጫሩ (scratches)) ወርቅ ቅብ ጭረቶች (extremely fine scratches) መካከል ያለ ርዝመት ማለት ነው።
- ዘንጉ የተሠራበት ብረት የፕላቲነም ኢሪድየም ቅይጥ (platinum-iridium alloy) ሲሆን ቅይጠቱ ደግሞ 90% ፕላቲነም (platinum) 10% ኢሪድየም (iridium) ነው። ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ ቅይጡ (alloy) የማይዝግ (does not rust) እና ባየር ላይ በሚገኙ የተለያዩ ፓካሮች (chemical) በቀላሉ የማይጠቃ መሆኑ ነው።
- በዘንጉ ዳር እና ዳር አካባቢ የተጫሩት ጭረቶች እጅግ በጣም ቀጫጭኖች ከመሆናቸው የተነሳ የሚታዩ በጢኖፓይፋ (microscope) ማለትም ባጉሊ መነጽር ብቻ ነው። ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ የጭረቶቹ ውፍረት (thickness) በሜትር ብያኔ (definition) ላይ የሚፈጥረውን ፍዳግ (error) ማለትም ስሕተት በተቻለ መጠን ለመቀነስ ነው።
- ዘንጉ የተቀመጠው ርዝመቱ በሙቀት (temperature) እና በሌሎች የተለያዩ ምክኒያቶች እንዳይታወክ፣ ማለትም እንዳይቀንስ ወይም እንዳይጨምር ተደርጎ በልዩ ሳጥን ውስጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው።
- ዘንጉ የተቀመጠበት ቦታ ደግሞ በፈረንሳይ አገር ፓሪስ (Paris) አቅራቢያ ሰቭሩዝ (Sevres) በሚባል ከተማ የሚገኘው ቤንቤራዊ የክብደቶችና የቁነናወች ቢሮ (International Bureau of Weight and Measures) ነው።
- ሜትር (meter) ማለት በቅርበዛ (approximately) ሲገለጽ ካፍንጫ ጫፍ (tip of nose) እስከተዘረጋ እጅ ጣቶች ጫፍ ያለው ርዝመት ማለት ነው።
- በነገራችን ላይ ያውራ ጣት (thumb) የላይኛው ክፍል ርዝመት በቅርበዛ (approximately) 1 ኢንች (one inch) ወይም 2.54 cm መሆኑ ነው።
- ባማረኛ ደግሞ ጋት የሚባለው ርዝመት ኢንች (inch) ከሚባለው ርዝመት ጋር ተቀራራቢ ነው።
- ያውራ ጣት ደንብ (rule of thumb) የሚባለው ደንብ (rule) የተፈጠረው ያውራጣት የላይኛው ክፍል ርዝመት በቅርበዛ (approximately) አንድ ኢንች ወይም አንድ ጋት መሆኑን መሠረት በማድረግ ነው።
- ያውራጣት ደንብ (rule of thumb) ማለት በገጠመኝ (experience) ላይ የተመሠረተ በቀላሉ ሊተገበር የሚችል ግርድፍ (coarse) ደንብ (rule) ወይም መመሪያ (guideline) ማለት ነው።
የሉል ዐብይና ንዑስ ክቦች
- ሉል (sphere) ማለት ሁሉም ነጥቦቹ ከመሃሉ (center) እኩል ርቀት ላይ የሚገኙ ሶስት ሚሃዊ ሱርፊክ (three dimensional figure) ማለትም ወርድ፣ ርዝመትና ከፍታ ያለው ሱርፊክ (figure) ነው።
- ያንድ ሉል አክዘንግ (radius) በሉሉ ላይ የሚገኝን ማናቸውንም ነጥብ ከሉሉ መሃል (center) ጋር የሚያገናኝ የቀጤ መስመር ዐጸቅ (straight line segment) ነው። አክዘንግ (radius) የሚለው ቃል የተገኘው አክባቢ ዘንግ ከሚለው ሐረግ ነው።
- በሉሉ መሃል (center) ላይ በማለፍ በሉሉ ላይ የሚገኙን ማናቸውንም ሁለት ነጥቦች የሚያገናኝ የቀጤ መስመር ዐጽቅ (straight line segment) የሉሉ ገማዘንግ (diameter) ይባላል። ገማዘንግ (diameter) የሚለው ቃል የተገኘው ገማሽ ዘንግ ከሚለው ሐረግ ነው።
- በሉል ጸጸፍ (surface) ማለትም ገጽ ላይ የተለያዩ ወርከፎች (sizes) ማለትም መጠኖች ያሏቸውን ክቦችን (circle) መክበብ ይቻላል።
- በሉል ገጽ ላይ ሊከበብ የሚችለው ዥትልቅ (largest) ክብ፣ ማለትም ትልቅነቱ ከሁሉም የበለጠ ክብ አክዘንጉ ከሉሉ አክዘንግ ጋር እኩል የሆነ ክብ ነው። ይህም ክብ ዐብይ ክብ (great circle) ይባላል።
- ዐብይ ያልሆነ ክብ (ማለትም ትልቅነቱ ከዐብይ ክብ ያነሰ ክብ) ደግሞ ንዑስ ክብ ( small circle) ይባላል።
- ልክ እንደ ማናችውም ክብ (circle) የሉል ዐብይ ክብ (great circle) እንዲሁም የሉል ንዑስ ክብ (small circle) ዙርያውን ያለው ጠቅላላ ርዝመት በልዩ ሥም ሠቅርመት (circumference) ይባላል።
- ሠቅ (circum) የሚለው ፊልጡፍ (prefix) የተገኘው ሠቅ (ቀበቶ) ከሚለው የግእዝ ቃል ሲሆን፣ ሠቅርመት (circumference) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ ሠቅ (circum) እና ርዝመት ከሚሉት ነው።
የምድር ዋልታዊ ሠቅርመት (Polar Circumference)
- ምድር ፍጹም ሉል (perfect sphere) ሳትሆን ከወደ ዋልታወቿ በኩል በትንሹ ጠፍጠፍ ያለች ሙጌርማ ሉልቴ (oblate spheroid) ናት።
- ባጠቃላይ አነጋገር ደግሞ ምድር የፉንባቴ (ellipsoid) ልዩ ረገድ (special case) ናት። ስለ ሉል (sphere) እና ፉንባቴ (ellipsoid) የበለጠ ለመረዳት ሉል እና ፉንባቴ (Sphere & Ellipsoid) የሚለውን ጦማር ይመልከቱ።
- ምድር ፍጹም ሉል (perfect sphere) ሳትሆን፣ ከወደ ዋልታወቿ በኩል ጠፍጠፍ ያለች ሙጌርማ ሉልቴ (oblate spherioid) የሆነችበት ምክኒያት ደግሞ በዋልታወቿ ላይ በስቷት በሚያልፍ ውስጣዊ ረቲድ (internal axis) ዙርያ በከፍተኛ ፍጥነት ስለምትሽከረከር እና ፍጹም ድድር (perfectly rigid) ስላልሆነች ማለትም የተወሰነ ተለማጭነት ስላላት ነው።
- ምድር ፍጹም ሉል (perfect sphere) ባትሆንም ግን ለፍጹም ክብነት የተቃረበች ስለሆነች ላብዛቹ ግልጋሎቶች ሉል (sphere) እንደሆነች ተደርጋ በቅርበዛ (approximately) ልትወሰድ ትችላለች።
- በምድር በሰሜን ዋልታ (north pole) እና በደቡብ ዋልታ (south pole) ላይ የሚያልፍ የምድር ሉል (sphere) ዐብይ ክብ (major circle) ዋልታዊ ዐብይ ክብ (polar major circle) ወይም ቋሚገር (longitude) ይባላል። ቋሚገር (longitude) የሚለው ቃል የተገኘው ቋሚ እና ማገር ከሚሉት ነው።
- የምድር ዋልታዊ ዐብይ ክብ (polar major circle) ዙርያውን ያለው ጠቅላላ ርዝመት የምድር ዋልታዊ ሠቅርመት (polar circumference of the Earth) ይባላል።
ሜትር እና የምድር ዋልታዊ ሠቅርመት
- የምድር ዋልታዊ ሠቅርመት (polar circumference of the Earth) ማለት በሰሜን ዋልታ (north pole) እና በደቡብ ዋልታ (south pole) ላይ የሚያልፈው የምድር ሉል (sphere) ዐብይ ክብ (major circle) ወይም ቋሚገር (longitude) ዙርያውን ያለው ጠቅላላ ርዝመት ማለት ነው።
- የፈረንሳይ ሰገለኛወች (French scientists) የሜትርን (meter) ርዝመት የመረጡት የምድር ዋልታዊ ሠቅርመት (polar circumference of the Earth) እቅጩን (exactly) 40 ካልጃኖ ሜትር (40 million meters) ወይም 40 ሺ ሃጃኖሜትር (40 thousand kilometer) እንዲሆን በማሰብ ነበር።
- በተለይም ደግሞ በፓሪስ (Paris) ላይ የሚያልፈው የምድር ቋሚገር (longitude) ከሰሜን ዋልታ (North pole) እስከ አኳይ (Equator) ድርስ ያለው ርዝመት እቅጩን (exactly) አስር ካልጃኖ ሜትር (10 million meter) ወይም አስር ሺ ሃጃኖሜትር (10 thousand kilometer) እንዲሆን በማሰብ ነበር።
- የምድር ዋልታዊ ሠቅርመት (polar circumference of the Earth) በዘመናዊ መሣርያወች ሲለካ ግን እሴቱ እቅጩን (exactly) 40, 000 ሃጃኖሜትር (kilometer) ሳይሆን፣ 40,007.863 ሃጃኖሜትር (kilometer) መሆኑ፣ ማለትም ከ 40,000 ሃጃኖሜትር (kilometer) በ 0.02% መቶኛ (percent) ብቻ የሚበልጥ መሆኑ ተደረሰበት።
- ይህ የሚያሳየው ደግሞ ከ250 ዓመታት በፊት የነበሩት የጊዜው የፈረንሳይ ሰገለኛወች (scientists) በተለይም ደግሞ ቀናቂወች (surveyors) የምድርን ዋልታዊ ሠቅርምት (polar circumference) ያሰሉብት መንገድ (method of calculation) ከፍተኛ እቅጭነት (high accuracy) የነበረው መሆኑን ነው።
- ከፈረንሳይ ሰገለኛወች በፊት ግን ኑባውያን (Nubians) ከብዙ ሺ ዓመታት በፊት የምድርን ሉልነት (sphere) ብቻ ሳይሆን የሉሉን አክዘንግ (radius) በከፍተኛ እቅጭነት (very high accuracy) ለማስላት ችለው ነበር። ይህን ስሌት ያካሂዱት ደግሞ የፀሐይ ጨረር በተለያዩ የምድር ቦታወች ላይ ከምድር ገጽ ጋር የሚሠራቸውን ዘዌወች (angles) በማነጻጸር ነበር። ለተጨማሪ ማብራሪያ ጋድምገር፣ ቋሚገር እና ጅጋንሲን (Longitude, Latitude & Geodesy) የሚለውን ጦማር ይመልከቱ።
- ቀናቂ (surveyor) የሚለው ቃል የተገኘው ቀነቀነ (መረመረ፣ ፈተሸ) ከሚለው ያማረኛ ቃል ሲሆን፣ ግሱም ስረባ ቀነቀ (survey)፣ ቅንቅ (ቅኑቅ) [surveyed]፣ ቀናቂ (surveyor)፣ ቅነቃ (surveying)፣ ቅንቀት፣ ቅናቄ፣ ቅናቆሽ እያለ ይሄዳል።
የሜትር ብያኔ በብርሃን ሞግርመት
- የርዝመትን ደርክ (standard of length) በብረት ዘንግ (metal rod) መበየን (define) የተለያዩ እንከኖች አሉት።
- ዘንጉ ሊጠፋ፣ ሊሰረቀ አለያ ደግሞ በእሳት፣ በጦርነትና በሌሎች ተመሳሳይ ምክኒያቶች ሊወድም ይችላል።
- የዘንጉ ርዝመት በተለያዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክኒያቶች ሊቀየር ይችላል።
- ዘንጉን በከፍተኛ እቅጭነት (accuracy) ማራባት (reproduce) እና በስፋት ማከፋፍል ቀላል አይደለም፣ ማለትም ዘንጉ በቀላሉ ተራቢ (easily reproducible) አይደለም።
- ከሁሉም የባሰው ደግሞ በዘንጉ የሚበየነው (defined) ሜትር (meter) ርዝመት ዘንጉ ላይ በተጫሩት ፊኖ ጭረቶች (fine scraches) ቅጥነት (thickness) የሚወሰን መሆኑ ነው።
- ፊኖ ጭረቶቹ የፈለገውን ያህል ቢቀጥኑም ቅጠነታቸው ዳዶ (zero) ስላልሆነ፣ የሜትሩን ርዝመት በከፍተኛ እቅጭነት (accuracy) መለካት አይቻልም።
- በነዚህና በሌሎች ምክኒያቶች ሳቢያ ሰገለኛወች (scientists) ከብረት ዘንግ (metal rod) የበለጠ እቅጭነትን (accuracy) እና ተራቢነት (reproducibility) ያለው የርዝመት ደርክ (standard of length) መበየኛ (define) ክስተት (phenomenon) መፈለጋቸውን ቀጠሉ።
- በ1953 ዓ.ም ላይ የርዝመት ደርክ ቶካድ(the standard unit of length) ማለትም ሜትር (meter) በብርሃን ሞግርመት (wavelength) ማለትም ሞገድ ርዝመት አንጻር እንደሚከተለው ተበየነ (defined)።
- የብርሃኑ ሞገድ (light wave) የሚመነጨው በቀጭን ሚሆል ቱቦ (thin glass tube) ውስጥ ታሽጎ በፈሳሽ ናይትሮጅን (liquid nitrogen) እንዲቀዘቀዝ (cooled) ከተደረገ የክሪፕቶን-86 ጋስ (krypton-86 gas) ነው። ሚሆል (glass) የሚለው ቃል የተገኘው ምሆ (መስታወት) ከሚለው ያማረኛ ቃል ነው።
- ጋሱ (gas) ብርሃን የሚያመነጨው ለከፍተኛ ቮልቴጅ (high voltage) ተጋልጦ ከከላፊነት (insulator) ወደ ፈላፊነት (conductor) ተለወጦ ሌትሪክ (electric) ሲያልፍበት ነው።
- የብርሃኑ ቀለም (color) ብርቱካንማ-ቀይ (orange-red) ነው።
ብያኔ (definition)፤ አንድ ሜትር (one meter) ማለት ከክሪፕቶን-86 ጋስ (krypton-86 gas) የሚመነጭ ብርቱካንማ-ቀይ ብርሃን 1,650,763.73 ሞግርመቶች (wavelengths) ያላቸው ጠቅላላ ርዝመት ማለት ነው።
በሌላ አባባል ከክሪፕቶን-86 ጋስ (krypton-86 gas) የሚመነጭ ብርቱካንማ-ቀይ (orange-red) ብርሃን ያለው ሞግርመት (wavelength) እቅጩን (exactly) 605.78 ሳልጢኖሜትር (nanometer) ነው ተብሎ ተበይኗል (defined) ማለት ነው።
ብያኔ (definition)፤ ከክሪፕቶን-86 ጋስ (krypton-86 gas) የሚመነጭ ብርቱካንማ-ቀይ ብርሃን ሞግርመት (wavelength) እቅጩን (exactly) 605.78 ሳልጢኖሜትር (nanometer) ነው።
የሜትር ብያኔ በብርሃን ፍጥነት
- የርዝመትን ደርክ (standard of length) ማለትም ሜትር (meter) በልዩ ሁኔታ ከተዘጋጀ ልዩ ዓይነት ቀኒጥ (atom) በሚመነጭ ብርሃን ሞግርመት (wavelength) አንጻር ከመበየን (define) ይለቅ ማናችወም ዓይነት ብርሃን (any type of light) ወና (vacuum) ውስጥ ባለው ፍጥነት (speed) መበየን፣ ብየናውን የበለጠ ተራቢ (reproducible) ያደርገዋል።
- በዚህም ምክኒያት በ1977 ዓ.ም ላይ የርዝመት ደርክ (standard of length) ማለትም ሜትር (meter) ብርሃን ወና (vacuum) ውስጥ ባለው ፍጥነት (speed) አንጻር እንደሚከተለው ተበየነ።
ብያኔ (definition)፤ አንድ ሜትር (one meter) ማለት ብርሃን ወና (vacuum) ውስጥ በ 1/299,792,458 ኑሲቃ (second) ውስጥ የሚጓዘው ርቀት (distance) ማለት ነው።
በሌላ አባባል የብርሃን ወና ፍጥነት (speed of light in vacuum) ማለትም ብርሃን ወና (vacuum) ውስጥ ያለው ፍጥነት (speed) እቅጩን (exactly) 299,792,458 ሜትር በኑሲቃ (meter per second) ነው ተብሎ ተበይኗል (defined) ማለት ነው።
ብያኔ (definition)፤ የብርሃን ወና ፍጥነት (speed of light in vacuum) እቅጩን (exactly) 299,792,458 ሜትር በኑሲቃ (meter per second) ነው።
- የርዝመትን ደርክ (standard of length) ማለትም ሜትርን (meter) በብርሃን ፍጥነት (speed of light) የሚበይነው ብየና (definition)፣ በጊዜ ብየና (definition of time) ላይ እንደሚመይፍ (depend) ማለትም እንደሚመካ ማስተዋል ያስፈልጋል።
- ይህ ግን ችግር የለውም ምክኒያቱም ጊዜ (time) እና ከጊዜ ጋር የሚዛመደው ዝውተራ (frequency) በከፍተኛ እቅጭነት (high accuracy) ሊቆነኑ (measure) ማለትም ሊለኩ ከሚችሉት ግኡዝ ናይባወች (physical quantities) ውስጥ ዋናወቹ ናቸውና።
ሐብረም (Spectrum) እና ሐብረምፓይፋ (Spectroscope)
- ዐይፊያ (ማለትም ዓይን) ከሚለው የወላይትኛ ቃል ፓይፋ (scope)፣ ፓይፋዊ (scopic)፣ ፕየፋ (scopy) የሚሉትን ኋልጡፎች (suffixes) እናገኛለን።
- ሕብር (ማለትም ቀለም) ከሚለው የግእዝ ቃል እና ቀለም ከሚለው ያማረኛ ቃል ሐብረም (spectrum) የሚለውን ቃል እንዲሁም ሐብረም (spectro) የሚለውን ፍልጡፍ (prefix) እናገኛለን። የሐብረም ብዙ ሐብረሞች (spectra) ይባላል።
- የሐብረም (spectrum) ግስ ሲረባ ሐበረመ፣ ሕብርም (ሕብሩም)፣ ሐብራሚ፣ ሕብረማ፣ ሕብርመት፣ ሕብራሜ፣ ሕብራሞሽ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
- ሐብረም (spectral) ከሚለው ሐብረም መስመር (spectral line)፣ ሐብረም ወርድ (spectral widith) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
- ሐብረም (spectrum) እና ፓይፋ (scope) ከሚሉት ሐብረምፓይፋ (spectroscope)፣ ሐብረምፓይፋዊ (spectroscopic)፣ ሐብረምፕየፋ (spectroscopy)፣ ሐብረምፐያፊ (spectroscopist) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
- ሐብረምፕየፋ (spectroscopy) ማለት ብርሃን ከቀኒጦች (atoms) እንዴት እንደሚፈልቅ (emission) እንዲሁም በቀኒጦች እንዴት እንደሚመጠጥ (absorption) የሚጠናበት የጉሲን (physics) እንዲሁም የፓካርሲን (chemistry) ዘርፍ ነው።
- ሐብረምፐያፊ (spectroscopist) ማለት የሐብረምፕየፋ (spectroscopy) ባለሙያ ማለት ነው።
- ሐብረምፓይፋ (spectroscope) ማለት የሐብረምፕየፋ (spectroscopy) ሠያር (instrument) ማለትም መሣርያ ማለት ነው።
- ሩፓይፋ (telescope)፣ ጢኖፓይፋ (microscope) እንደምንል ሐብረምፓይፋ (spectroscope) እንላለን።
- ሐብረም (spectrum) ከሚለው የሚከተሉትን የመሳሰሉ ቃሎች እናገኛለን።
- ሌክትሮማግኔት ሐብረም (electromagnetic spectrum)፣ ግሃድ ሐብረም (visible spectrum)፣ ቀኒጣዊ ሐብረም (atomic spectrum)
- ሐብረምለኪ (spectrometer)፣ ሐብረምልካት (spectrometry)
- ቁሰት ሐብረምለኪ (mass spectrometer)፣ ቁሰት ሐብረምልካት (mass spectrometry)
- ቁሰት ሐብረምለኪ (mass spectrometer) አብዛኛውን ጊዜ ቁሰት ሐብራሚ (mass spec) ወይም ባጭሩ ቁሐ (mass spec) ይባላል።
ሜትር እና አንግስትረም (Angstrom)
- አንግስትረም (Angstrom) ወይም አንግስትሮም አጭር የርዝመት ቶካድ (unit of length) ነው።
- አንግስትረም የሚያገለግለው በቀኒጣዊ ጉሲን (atomic physics) እና ፀምሪቃዊ ጉሲን (molecular physics) ውስጥ የቀኒጦችን (atoms) እና ፀምሪቆችን (molecules) ወርከፎች (sizes)፣ በሐብረምፕየፋ (spectroscopy) ላይ ደግሞ የብርሃንን ሞግርመቶች (wavelengths) ባጭሩ ለመግለጽ ነው።
- ያንግስትረም ወመል (symbol) ማለትም ወካይ ምልክት Å ሲሆን፣ እሴቱ ደግሞ በሜትር (meter) ሲገለጽ 1Å = 10-10 m ነው።
- ስለዚህም አንድ አንግስትረም (one angstrom) ማለት አንድ አስረኛ ሳልጢኖሜትር (one-tenth of nanometer) ማለትም 1Å = (1/10) nm = 0.1 nm ነው።
- በዚህም ምክኒያት አንግስትሮም በሳልጢኖሜትር እየተተካና እየቀረ ነው ማለት ይቻላል።
- አንግስትሮም የተሰየመው በሐብረምፕየፋ (spectroscopy) ጀማሮ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ባደረገው በስዊድናዊው ጉሲናኛ (physicist) ዮናስ አንግስትርም (Anders Jonas Angstrom) ስም ነው።
ጠፈርሲናዊ ርቀቶች በብርሃን ወና ፍጥነት
- ጠፈር ማለት በግእዝ ሰማይ ማለት ነው። ይህም ጠፈር የሚል ቃል astro የሚለውን የንግሊዘኛ ፊልጡፍ (prefix) ማለትም ከቃል ፊትጌ የሚለጠፍ ባዕድ መነሻ ይተካልናል።
- ጠፈር (astro) ከሚለው ፊልጡፍ (prefix) እና ሲን (logy) ከሚለው ኋልጡፍ (suffix) ጠፈርሲን (astronomy)፣ ጠፈርሲናዊ (astromomical)፣ ጠፈርሲንኛ (astronomer) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
- ጠፈርሲን (astronomy) ማለት የጠፈር ጥናት ማለት ሲሆን፣ ጠፈርሲነኛ (astronomer) ማለት ደግሞ የጠፈርሲን ባለሙያ ማለት ነው።
- ጠፍርሲናዊ ርቀቶች እና ርርቀቶች በተለይም ደግሞ ኮኮቦች ከምድር ያሏቸው ርቀቶች አብዛኛውን ጊዚ የሚገለጹት የብርሃንን ወና ፍጥነት (speed of light in vacuum) መሠረት በማድረግ ነው።
- የብርሃን ወና ፍጥነት (speed of light in vacuum) በቅርበዛ (approximately) 3 x 108 m/s ወይም 300 ካልጃኖሜትር በኑሲቃ (300 million meter per second) ነው።
- አንድ ብርሃን ኑሲቃ (one light second) ማለት ብርሃን ባንድ ኑሲቃ (second) ወና (vacuum) ውስጥ የሚጓዘው ርቀት ማለት ሲሆን፣ እሴቱ ደግሞ 300 ካልጃኖሜትር (300 Megameter) ነው።
- አንድ ብርሃን ደቂቃ (onel light minute) ማለት ብርሃን ባንድ ደቂቃ (minute) ወና (vacuum) ውስጥ የሚጓዘው ርቀት ማለት ሲሆን፣ እሴቱ ደግሞ 18 ሳልጃኖሜትር (18 Gigameter) ነው።
- አንድ ብርሃን ዓመት (one light year) ማለት ብርሃን ባንድ ዓመት (year) ወና (vacuum) ውስጥ የሚጓዘው ጠቅላላ ርቀት ማለት ሲሆን፣ እሴቱ ደግሞ በቅርበዛ (approximately) 9.46 ሃምጃኖሜትር (9.46 Petameter) ነው።
የጀንበራዊ ስርካት ርቀቶች በጠፈርሲናዊ ቶካድ (Astronomical Unit)
- ጀንበር ማለት ፀሐይ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ጃን ብርሃን (ትልቁ ብርሃን) ከሚለው ሐረግ ነው፣ ፀሐይ ትልቋ ብርሃን ስትሆን ኮኮቦች ደግሞ ትናንሾቹ ብርሃኖች ናቸውና።
- ጀንበር ከሚለው ቃል ጀንበራዊ (solar, helio-) የሚለውን ቃል እንዲሁም ፊልጡፍ (prefix) [ማለትም ባዕድመነሻ] እናገኛለን።
- ለምሳሌ ያህል ጀንበራዊ ጉልበት (solar energy)፣ ጀንበራዊ ኃይል (solar power)፣ ጀንበርማከላዊ ሞዴል (heliocentric model) ይሆናሉ።
- ጀንበራዊ ስርካት (solar system) ማለት ጀንበር እና በጀንበር ዙርያ የሚገኙ ራማዊ አካሎችን (heavenly bodies) የሚያጠቃልል ስርካት (system) ነው።
- ጀንበራዊ ስርካት ጀንበራዊ የተባለበት ምክኒያት የስርካቱ ዋና አበጋዝ ማለትም አዛዥና ናዛዥ ወይም አድራጊና ፈጣሪ ጀንበር ስለሆነች ነው። በሌላ አባባል በጀንበራዊ ስርካት ውስጥ የሚገኙት የሁሉም ራማዊ አካሎች ሑሰት (motion) ባብዛኛው የሚወሰነው በፀሐይ ቁስበት (gravity) ነው። ለተጨማሪ ማብራሪያ ጀንበራዊ ስርካት (Solar System) የሚለውን ጦማር ይመልከቱ።
- ምድር ከፀሐይ ያላት አማካይ ርቀት ጠፈርሲናዊ ቶካድ (astronomical unit) ወይም ባጭሩ ጠቶ (AU) ይባላል። በሌላ አባባል ምድር ከፀሐይ ያላት አማካይ ርቀት 1ጠቶ (1 AU) ነው ማለት ነው።
- ያንድ ጠቶ (one AU) እሴት በሜትር (meter) ሲገለጽ በቅርበዛ (approximately) 1.5 x 1011 ሜትር ወይም 150 x 109 ሜትር ማለትም 150 ሳልጃኖ ሜትር (150 Gigameter) ነው።
- በጀንበራዊ ስርካት (solar system) ውስጥ ርቀቶችና ርርቀቶች የሚጠቀሱት አብዛኛውን ጊዜ በጠፈርሲናዊ ቶካድ (ጠቶ) ነው።
- ለምሳሌ ያህል ከፀሐይ ባራተኛ ርቀት ላይ ከምድር ጀርባ የምትገኘው የራቤተል (Mars) እና የፀሐይ አማካይ ርርቀት 1.5 AU ነው። ይህ ማለት ደግሞ ራቤተል (Mars) ከፀሐይ ያላት አማካይ ርቀት ምድር ከፀሐይ ያላትን አማካይ ርቀት አንድ ከግማሽ ነው ማለት ነው።
መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com