ማሳሰቢያ
ይህ ጦማር (ማለትም ክፍል 3) ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው በሚቀድሙት ክፍሎች (ማለትም በክፍሎች 1 እና 2) ላይ ስለሆነ፣ ይህን ክፍል ከማንበብወ በፊት ክፍሎችን 1 እና 2 ቢያንስ ቢያንስ በገረፍታ ይመልከቱ።
ብሶላዊ አቅጣጫወች (Compass Directions)
- ብሶል (compass, navigation compass) ማለት የምድርን ማግኔታዊ ጠባይ (magnetic property) በመጠቀም ምድራዊ አቅጣጫወችን ለማመልከት የሚያገለግል ሠያር (instrument) ማለትም መሣርያ ነው።
- እግረ መንገዳችንን ደግሞ በገረ (ነደፈ፣ ለካ፣ መጠነ) ከሚለው ያማረኛ ቃል ቢጋር (compass, drafting compass) የሚለውን ቃል፣ ዘዌ (angle) ከሚለው ቃል ደግሞ ዘዋሚ (protractor) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
ባሁኑ ጊዜ ግን ብሶል (compass) ቀርቶ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በኖኖላዊ አዴት ስርካት (ኖአስ) [Global Positioning System, GPS] ወይም ባጭሩ ኖስ ተተክቷል ማለት ይቻላል። እንዲህም ሆኖ ግን ምድራዊ አቅጣጫወች አሁን ድረስ የሚባሉት ብሶላዊ አቅጣጫወች (compass directions) ነው።
- እቅጩን ወደ ሰሜን ዋልታ (North pole) የሚያመልከት አቅጣጨ ሰሜን (North) ሲባል፣ እቅጩን ወደ ደቡብ ዋልታ (South pole) የሚያመለክት አቅጣጫ ደግሞ ደቡብ (South) ይባላል።
- ከሰሜን በስተቀኝ 90o በመሥራት የሚገኘው አቅጣጫ ምሥራቅ (East) ሲባል፣ የምሥራቅ ተቃራኒ አቅጣጫ ደግሞ ምዕራብ (West) ይባላል።
- እቅጩን በሰሜን እና ምሥራቅ መካከል 45o ላይ የሚገኘው አቅጣጫ ሰሜን ምሥራቅ ወይም ባጭሩ ሰምራቅ (Northeast, North-east) ሲባል፣ እቅጩን በሰሜን እና ምዕራብ መካከል 45o ላይ የሚገኘው አቅጣጫ ደግሞ ሰሜን ምዕራብ ወይም ባጭሩ ሰምራብ (Northwest, North-west) ይባላል። በግእዝ ሰሜን ምሥራቅ መስዕ ሲባል፣ ሰሜን ምዕራብ ደግሞ ባሕር ይባላል።
- እቅጩን በደቡብ እና ምሥራቅ መካከል 45o ላይ የሚገኘው አቅጣጫ ደቡብ ምሥራቅ ወይም ባጭሩ ደምራቅ (Southeast, South-east) ሲባል፣ እቅጩን በደቡብ እና ምዕራብ መካከል 45o ላይ የሚገኘው አቅጣጫ ደግሞ ደቡብ ምዕራብ ወይም ባጭሩ ደምራብ (Southwest, South-west) ይባላል። በግእዝ ደቡብ ምሥራቅ ሊባ ሲባል፣ ደቡብ ምዕራብ ደግሞ አዜብ ይባላል።
በተጨማሪ ደግሞ
- ሰሜን ምሥራቅ (east of north) ማለት ከሰሜን ተነስቶ ወደ ምሥራቅ ዘዌ (angle) የሚሠራ ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል 75o ሰሜን ምሥራቅ (75o east of north) ማለት ከሰሜን ተነስቶ ወደ ምሥራቅ 70o ዘዌ የሚሠራ ማለት ነው።
- በተመሳሳይ መንገድ ሰሜን ምዕራብ (west of north) ማለት ከሰሜን ተነስቶ ወደ ምዕራብ ዘዌ (angle) የሚሠራ ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል 75o ሰሜን ምዕራብ (75o west of north) ማለት ከሰሜን ተነስቶ ወደ ምዕራብ 75o ዘዌ የሚሠራ ማለት ነው።
ኮንኮል (car)፣ ጨንኮል (truck) እና ግትሌ (Train)
- ኮንኮላታ (ማለትም መኪና) ከሚለው ቃል ኮንኮል (car, vehicle) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ኮንኮል (car) ማለት መኪና ማለት ነው። የቤት መኪና የሚለውን ደግሞ ባጭሩ ቤንኮል እንለዋለን።
- ጭነት እና ኮንኮል (car) ከሚሉት ቃሎች ጨንኮል (truck) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ጨንኮል (truck) ማለት የጭነት ኮንኮል ማለት ሲሆን፣ ጨንኮለኛ (truck driver, trucker) ማለት ደግሞ ጨንኮል ነጅ ማለት ነው። የጨንኮል (truck) ግስ ሲረባ ጨነኮለ (to truck)፣ ጭንኩል (trucked)፣ ጨንኳይ (trucker)፣ ጭንኮላ (trucking) እያለ ይሄዳል።
- እኑስ እና ጨንኮል (truck) ከሚሉት ኑስጨንኮል (pick-up truck) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ኑስጨንኮል (pick-up truck) ማለት አነስተኛ ጨንኮል ማለት ነው። ኑስ ጨንኮል የሚያገለግለው ጭነትን ላፍ አድርጎ ለመውሰድ ስለሆነ፣ ሞጭላፊ (pick-up truck) ልንለው እንችላለን።
- ጅሪስ (ቀረጥ) ከሚለው የወላይተኛ ቃል ጀሪሳ (taxi, cab, cabby) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ጀሪሳ (taxi) ማለት ታክሲ ማለት ሲሆን፣ ጀሪሰኛ (taxi driver) ማለት ደግሞ ጀሪሳ ነጅ ማለት ነው። የጀሪሳ (taxi) ግስ ሲረባ ጀረሰ፣ ጅርስ (ጅሩስ) [taxied] ፣ ጀራሲ (taxiing) ፣ ጅረሳ (taxiing) እያለ ይሄዳል።
- ሁንዳ (ማለት ሁሉም) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ሆልፓ (bus, autobus) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ሆልፓ (bus, autobus) ማለት አቶብስ ማለት ሲሆን፣ ሆልፐኛ (bus driver) ማለት ደግሞ ሆልፓ ነጅ ማለት ነው። የሆልፓ (bus) ግስ ሲረባ ሆለፐ (to bus)፣ ሁልፕ (bused, bussed)፣ ሆላፒ (busing, bussing)፣ ሁለፓ (busing, bussing) እያለ ይሄዳል።
- እኑስ እና ሆልፓ (bus) ከሚሉት ቃሎች ኑሶልፓ (minubus) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ኑሶልፓ (minibus) ማለት ሳይቸግረን ጤፍ በመበደር ሚኒባስ የምንለው ሲሆን፣ ኑሶልፐኛ (minibus driver) ማለት ደግሞ ኑሶልፓ ነጅ ማለት ነው።
- ግትልትል (ማለትም ቅጥልጥል) ከሚለው ቃል ግትሌ (train) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ግትሌ (train) ማለት ባቡር ማለት ሲሆን፣ ግትለኛ (train driver) ማለት ደግሞ ግትሌ ነጅ ማለት ነው።
car (vehicle) = ኮንኮል
car driver = ኮንኮለኛ
የቤት መኪና = ቤንኮል
truck = ጨንኮል
truck driver = ጨንኮለኛ
truck (verb) = ጨነኮለ
trucking = ጭንኮላ
pick-up truck = ኑስጨንኮል፣ ሞጭላፊ
taxi (cab, cabby) = ጀሪሳ
taxi driver = ጀሪሰኛ
taxi (verb) = ጀረሰ
taxiing = ጅረሳ
bus (autobus) = ሆልፓ
bus driver = ሆልፐኛ
bus (verb) = ሆለፐ
busing (bussing) = ሁለፓ
minibus = ኑሶልፓ
minibus driver = ኑሶልፐኛ
train = ባቡር፣ ግትሌ
train driver = ባቡረኛ ፣ ግትለኛ
ድብድ (Fixed) እና ርፍቅ (Stationary)
- ባማረኛ አደበ ማለት ረጋ፣ ሥርዓት ያዘ ማለት ነው፣ አደብ ግዛ እንዲሉ። በኦሮምኛም ዳቤዳ ማለት መቆም ማለት ነው። አደበ እና ዳቤዳ ከሚሉት ቃሎች ደበደ (fix) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ደበደ (to fix, fixate) ማለት ቸከለ፣ ባንድ ቦታ ላይ አቆመ፣ እንዳይንቀሳቀስ አደረገ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ደበደ (to fix, fixate)፣ ድብድ (ድቡድ) [fixed, fixated]፣ ደባዲ (ደባጅ) [fixing, fixating]፣ ድበዳ (fixing, fixation)፣ ድብደት፣ ድባዴ፣ ድባዶሽ እያለ ይሄዳል።
- ባማረኛ ረፈቀ ማለት ተቀመጠ፣ ተወዘፈ ማለት ነው፣ ርፍቅ እንዲሉ ውዝፍ ሊሉ። ይህም ርፍቅ የሚል ቃል stationary የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል። ግሱም ሲረባ ረፈቀ፣ ርፍቅ፣ ረፋቂ፣ ርፈቃ፣ ርፍቀት፣ ርፋቄ፣ ርፋቆሽ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
fix (fixate) – ደበደ
fixed (fixated) – ድብድ
fixed point – ድብድ ነጥብ
stationary – ረፈቅ፣ ርፍቅ
stationary (verb) – ረፈቀ
ድብድ ኮኮቦች (Fixed Stars)
- ምድር ከፀሐይ ያላት ርቀት በብርሃን ፍጥነት አንጻር ሲገለጽ 8 ደቂቃ (8 minutes) ብቻ ነው። በሌላ አባባል ብርሃን ከፀሐይ ተነስቶ ምድር ለመድረስ የሚፍጀበት ጊዜ 8 ደቂቃ ብቻ ነው።
- በሌላ በኩል ደግሞ ሰሬ (Sirius) ወይም ውሻ ኮኮብ (Dog Star) የሚባለውን ከሁሉም የሰማይ ኮኮቦች የበለጠ ብሩህ (the brightest star in the sky) የሆነውን ኮኮብ እንውሰድ። ሰሬ ማለት በኦሮምኛ ውሻ ማለት ነው። ብርሃን ከሰሬ ተነስቶ ምድር ለመድረስ የሚፈጅበት ጊዜ 8.6 ዓመት ወይም 4.5 ካልጃኖ ደቂቃ (4.5 million minutes) ነው። ይህ ማለት ደግሞ ሰሬ ከምድር ያለው ርቀት ፀሐይ ከምድር ያላትን ርቀት 565 ሺ ጊዜ ይበልጣል ማለት ነው።
- ስለዚህም ምድር በፀሐይ ዙርያ ስትዞር የምትጓዘው ርቀት፣ ምድር ከሰሬ ካላት ርቀት ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ስለሆነ፣ ምድር ከሰሬ አንጻር እንደማትንቀሳቀስ ተድረጎ ሊወሰድ ይችላል።
- በሌላ አባባል ከፀሐይ አንጻር ስትታይ ምድር በፀሐይ ዙርያ ብትዞርም፣ ከሰሬ አንጻር ስትታይ ግን ምድር ካለችበት የማትንቀሳቀስ ማለትም ቅምጠቷን (position) የማትለውጥ ረፍቅ (stationary) ናት ብሎ በከፍተኛ ቅርበዛ (very high approximation) መናገር ይቻላል ማለት ነው።
- አብዛኞቹ ሩቅ ኮኮቦች (distant stars) ደግሞ ከምድር ያሏቸው ርቀቶች በመቶ እንዲሁም በሺ የብርሃን ዓመታት የሚቆጠሩ ናቸው። ይህ ደግሞ ምድር ከሩቅ ኮኮቦች አንጻር ርፍቅ (stationary) ናት የሚለውን ቅርበዛ (approximation) የበለጠና የበለጠ ትክክለኛ ያደረገዋል።
- በሌላ አባባል ከምድር አንጻር ሲታዩ ሩቅ ኮኮቦች (distant stars) ቅምጠታቸውን (position) ሳይለውጡ ባሉበት የተቀመጡ ርፍቅ (stationary) ወይም ደግሞ ባሉበት የተደበዱ (fixed) ማለትም የተቸከሉ ድብድ ኮኮቦች (fixed stars) ናቸው ተብሎ በከፍተኛ ቅርበዛ (very good approximation) መናገር ይቻላል ማለት ነው።
- ሩቅ ኮኮቦች (distant stars) ከምድር አንጻር ርፍቅ (stationary) ወይም ድብድ (fixed) ናቸው ለማለት የሚያስደፍርበትን ሁኔታ በሚከተለው ምሳሌ መረዳት ይቻላል። አንድ አሞራ ባናታችን ላይ ስታልፍ በጣም ፈጣን ትመስለናለች። አሞራዋ ከኛ በጣም ርቃ ወደ አድማስ ስትጠጋ ግን፣ የምትንቀሳቀስ አይመስለንም። ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ አሞራዋ በፍጥነቷ ሳቢያ የምትጓዘው ርቀት፣ ከኛ ካላት ርቀት ጋር ሲነጻጸር ኢምንት በመሆኑ ነው።
አዴት (Position) እና ፍልሰት (Displacement)
- ኢዶ (ማለትም ቦታ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል አዴት (location, position) የሚለውን ቃል እናገኛለን። አዴት (position, location) ማለት መገኛ ቦታ፣ ያሉበት ቦታ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ አደተ (locate)፣ እድት (እዱት) (located)፣ አዳቲ (አዳች) [locating, locator]፣ እደታ (locating)፣ እዳቴ፣ እዳቶሽ እያለ ይሄዳል።
- ፈለሰ (ማለትም ተሰደደ፣ ቦታውን ለቆ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ) ከሚለው ፍልሰት (displacement) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ግሱም ሲረባ አፈለሰ (displace)፣ ፍልስ (/ፍሉስ\) [displaced]፣ አፍላሲ (አፍላሽ) [displacing]፣ ፈለሳ (displacement)፣ ፍልሰት (displacement) እያለ ይሄዳል።
position (location) = አዴት፣ ቅምጠት
initial position = ባተሜ አዴት
final position = ፍጻሜ አዴት
displacement = ፍልሰት
displace = አፈለሰ
ፍጥነት (Speed) እና ሶፊሳ (Velocity)
- ሰፊሳ (ማለትም ፍጥነት) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ሶፊሳ (velocity) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ግሱም ሲረባ ሶፈሰ፣ ሱፍስ፣ ሶፋሲ፣ ሱፈሳ፣ ሱፍሰት፣ ሱፋሴ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
- ፍጥነት (speed) የሚለው ቃል ምን ያህል ርቀት በምን ያህል ጊዜ መጓዘን የሚያመለከት አቅጣጫን የማያካትት ቃል ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሶፊሳ (velocity) ፍጥነትን ከአቅጣጫ ጋር የሚያጣምር ቃል ነው።
- ስለዚህም ፍጥነት (speed) ብክረት (magnitude) ብቻ ያለው፣ አቅጣጫ (direction) ግን የሌለው (በትክክል ለመናገር ደግሞ አቅጣጫን የማያጣምር) ናይባ (quantity) ስለሆነ፣ ሐዝተን ናይባ (scalar quantity) ነው።
- በሌላ በኩል ደግሞ ሶፊሳ (velocity) ብክረትም (magnitude) አቅጣጫም (direction) ያለው ፍላስተን ናይባ (vector quantity) ነው።
- ለምሳሌ ያህል 50 ሃጃኖሜትር በሰዓት (50 kilometer per hour) የሚጓዝ ሞጭላፊ (pick-up truck) የሚጓዘው ወደ ሐራምባም ሆነ ወደ ቆቦ ፍጥነቱ ያው ሲሆን፣ ሶፊሳው ግን የተለያየ ነው፣ አቅጣጫው የተለያየ ነውና።
- ሐራምባ ማለት የሐር ተራራ ወይም መንደር ማለት ሲሆን፣ የሚገኘውም ይፋት ውስጥ ነው። ቆቦ ደግሞ ባንኮበር በኩል የሚገኝ መንደር ሲሆን፣ ስያሜው የተገኘው ቆበበ (ጉብ አለ፣ ጎብታ መሰለ) ከሚለው ቃል ነው። ሐራምባና ቆቦ ማለት ገማዘንጋዊ ተቃራኒ (diametrically opposite) ማለትም ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ማለት ሲሆን፣ ጦሳና አዝዋ ወይም እንጦጦና የረር ልንለውም እንችላለን። ጦሳ እና አዘዋ እንደቅደምተከተላቸው በደሴ ምዕራብና ምሥራቅ የሚገኙ ተራሮች ናቸው።
speed – ፍጥነት
speedometer – ፍጥነትለኪ
velocity – ሶፊሳ
velocity (verb) – ሶፈሰ
velocity vector – ሶፊሳ ፍላስተን
diametrically opposite = ገማዘንጋዊ ተቃራኒ፣ ሐራምባና ቆቦ፣ ጦሳና አዘዋ፣ እንጦጦና የረር
ቶኪማ (Uniform) እና አልቶኪማ (Nonuniform)
- ቶኮ (ማለትም አንድ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ቶኪማ (uniform)፣ ቶኪማነት (uniformity) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። ቶኪማ (uniform) ማለት አንድ ወጥ እንደ ማለት ሲሆን፣ አልቶኪማ (nonuniform, non-uniform) ማለት ደግሞ ቶኪማ ያልሆነ፣ ማለትም አንደ ወጥ ያልሆነ ማለት ነው።
- የቶኪማ ግስ ቶከመ፣ ቱክም፣ ቶካሚ፣ ቱከማ፣ ቱክመት፣ ቱካሜ፣ ቱካሞሽ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም። ቶከመ ማለት ቶኪማ ሆነ ወይም አደረገ ማለት ሲሆን፣ ቱክም ማለት ደግሞ የተቶከመ ማለት ነው።
uniform (uniformity) = ቶኪማ፣ ቶኪማነት
uniform (verb) = ቶከመ
nonuniform (nonuniformity) = አልቶኪማ፣ አልቶኪማነት
ቶኪማ ሑሰት (Uniform Motion)
- ሶፊሳ (velocity) ማለት ፍጥነትን ከአቅጣጫ ጋር የሚያጣምር ቃል ነው ብለናል። ስለዚህም ቋሚ ሶፊሳ (constant velocity) ማለት ቋሚ ፍጥነት (constant speed) እና ቋሚ አቅጣጫ (constant dirrection) ማለት ነው።
- በሌላ አባባል ቋሚ ሶፊሳ (constant velocity) ማለት በቀጤ መስመር (straight line) ላይ ባንድ አቅጣጫ (one direction) እና በቋሚ ፍጥነት (constant speed) የሚካሄድ ሑሰት (motion) ወይም እንቅስቃሴ ማለት ነው።
- በቋሚ ሶፊሳ የሚካሄድ ሑሰት (motion) ቶኪማ ሑሰት (uniform motion) ይባላል። በሌላ አባባል ቶኪማ ሑሰት (uniform motion) ማለት በቀጤ መስመር ላይ ባንድ አቅጣጫና በቋሚ ፍጥነት የሚካሄድ ሑሰት ማለት ነው።
- ቶኪማ (uniform) ያልሆነ ሑሰት አልቶኪማ ሑሰት (nonuniform moton) ወይም ጥዱፍ ሑሰት (accelerated motion) ይባላል። ስለዚህም አልቶኪማ ሑሰት ወይም ጥዱፍ ሑሰት ማለት በጠዋጢ ሶፊሳ (variable velocity) ማለትም ቋሚ ባልሆነ ሶፊሳ የሚካሄድ ሑሰት ማለት ነው።
- በሌላ አባባል አልቶኪማ ሑሰት (nonuniform motion) ወይም ጥዱፍ ሑሰት (accelerated motion) ማለት በጠዋጢ ፍጥነት (veriable velocity) እና/ወይም (and/or) በጠዋጢ አቅጣጫ (variable speed) የሚካሄድ ሑሰት (motion) ማለት ነው።
ቁነና (Measurement)
- ባማረኛ ቆነነ ማለት ለካ፣ መጠነ፣ ሰፈረ ማለት ነው፣ በተለይም ደግሞ ድርጎን ወይም ዳረጎትን (commision)፣ ማለትም በየጊዘው የሚደረግን ክፍያ። ይህም ቃል measure የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
- ግሱም ሲረባ ቆነነ (measure)፣ ቁንን (measured)፣ ቆናኒ (ቆናኝ) [measuring]፣ ቁነና (measuring, measurement)፣ ቁንነት፣ ቁናኔ፣ ቁናኖሽ እያለ ይሄዳል።
measure = ቆነነ
measurement = ቁነና
measurement system = ቁነና ስርካት
measurement unit = ቁነና ቶካድ
ነፃሪ (Observer) እና ነፀራ (observation)
- ነፀረ (አየ፣ ተመለከተ፣ አስተዋለ) የሚለው የግእዝ ቃል observe የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል። ግሱም ሲረባ ነፀረ (observe)፣ ንፅር (ንፁር) (observed)፣ ነፃሪ (observer)፣ ነፀራ (observing, observation) እያለ ይሄዳል።
- ነፀራ (observation) ማለት በጥንቃቄ ማስተዋል ወይም መመርመር ማለት ነው።
observe = ነጸረ
observer = ነጻሪ
observation = ነጸራ
ፀናር (Relative) እና ፅነራ (Relativity)
- አንፃር ከሚለው ቃል ፀናር (relative)፣ ፀናራዊ (relativistic) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
- ፀናር (relative) ማለት ንጽጽር ወይም የንጽጽር ውጤት እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ፀነረ (relativize)፣ ፅንር (ፅኑር) [relativized]፣ ፀናሪ (relativizing)፣ ፅነራ (relativization)፣ ፅንረት፣ ፅናሬ፣ ፅናሮሽ እያለ ይሄዳል።
relative (relativistic) = ፀናር፣ ፀናራዊ
relativize = ፀነረ
relative density = ፀናራዊ እፍጋት
relative humidity = ፀናራዊ ወበቅ
relative motion = ፀናራዊ ሑሰት
relative velocity = ፀናራዊ ሶፊሳ
relativity = ፅነራ
relativistic theory (theory of relativity) = ፀናራዊ ግንገና (ፅነራ ግንገና)
ዋቢ (Reference) እና ውበባ (Referring)
- ባማረኛ ዋበ ማለት ሰጠ፣ አቀበለ፣ አስረከበ ማለት ነው (በጉራጌኛም ዋበኝ ማለት ስጠኝ ማለት ነው)። ዋቢ ማለት ደግሞ ሰጭ፣ አቀባይ ማለት ነው። ይህም ዋቢ የሚባል ቃል reference የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
- የዋቢ (reference) ግስ ሲረባ ወበበ (refer)፣ ውብብ (ውቡብ) [referred, referenced]፣ ወባቢ (referring, referencing)፣ ውበባ (referring, referencing)፣ ውብበት፣ ውባቤ፣ ውባቦሽ እያለ ይሄዳል።
- ወበበ (refer) ማለት አመሳከረ፣ ወደሚመለከተው አመራ፣ አቀረበ፣ ጠቀሰ ማለት ሲሆን፣ ውብብ (ውቡብ) [referred, referenced] ማለት ደግሞ የተወበበ ማለት ነው።
reference = ዋቢ
refer (to reference) = ወበበ
reference level = ዋቢ ጠለል
reference point = ዋቢ ነጥብ
ዋቢ መቃን (Reference Frame)
- ቅምጠቶችን (positions) ለመግለጽ በስተቀኝ (on the right) በኩል ወይም በስተግራ (on the left) በኩል ስንል፣ ከሆነ አካል (body) በስተቀኝ በኩል ወይም ከአካሉ በስተግራ በኩል ማለታችን ነው። በሌላ አባባል ቅምጠቶች የሚገለጹት ከሆነ አካል ወይም አካሎች አንጻር ነው።
- በተመሳሳይ መንገድ ፍጥነቶች የሚገለጹት ከሆነ አካል ወይም አካሎች አንጻር ነው። ለምሳሌ ያህል የመኪናው ፍጥነት 70 ሃጃኖሜተር በሰዓት (70 kilometer per hour) ነው ስንል፣ ከመንገዱ ዳር ከቆመ ንፃሪ (observer) ወይም ከመንገዱ ዳር ከሚገኝ ዛፍ ወይም ከሌላ ተመሳሳይ ነገር አንጻር ማለታችን ነው።
- ቅምጠትን (position)፣ ፍጥነትን (speed) እና የመሳሰሉትን ናይባወች (quantities) ባንጻራዊ እይታ ለመቆነን (measure) የሚያገለግል አካል (body) ወይም ያካሎች ስርካት (system of bodies) ዋቢ መቃን (reference frame) ይባላል።
- የቁነና (measurement) ውጤት ቁነናውን ለማከናወን በሚያገለግለው ዋቢ መቃን (reference frame) ላይ ይመይፋል (depend) ማለትም ይመካል። ለምሳሌ ያህል በፈጣን መኪና ውስጥ ያለ ተሳፋሪ እና ምድር ላይ የቆመ ነጻሪ (observer) ያሞራን ፍጥነት ቢቆንኑ (measure ) ማለትም ቢለኩ የሚያገኟቸው እሴቶች የተለያዩ ናቸው።
ቁስ (Matter)፣ ቁሰት (Mass) እና ቁስበት (Gravity)
- ቁስ (matter) ከሚለው ቁሰት (mass) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ቁሰት (mass) ማለት የቁስ መጠን እንደ ማለት ነው።
- ቁስ (matter) እና ስበት ከሚሉት ቁስበት (gravity, gravitation, gravitational force) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ግሱም ሲረባ ቆሰበ፣ ቁስብ፣ ቆሳቢ፣ ቁሳባ፣ ቁሳቤ፣ ቁሳቦሽ እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
matter = ቁስ
antimatter = ፀረቁስ
dark matter = ጸሊምቁስ
mass – ቁሰት
center of mass – ቁሰት ማዕከል
mass number – ቁሰት ቁጥር
mass spectrometer – ቁሰት ቀልዛሪ
massless – ቁሰታልባ፣ ቁሰትቢስ
gravity (gravitation) = ቁስበት
gravity (verb) = ቆሰበ
gravitational = ቁስበታዊ
gravitational force = ቁስበት
gravitational mass = ቁስበታዊ ሑሰት
gravitational field = ቁስበታዊ መስክ
gravitational lens = ቁስበታዊ ምስሮ
ሃኬት (Inertia)
- ሃከየ (ማለትም ሰነፈ) ከሚለው የግእዝ ቃል ሃኬት (inertia) የሚለውን ቃል እንገኛለን።
- ሃኬት (inertia) ማለት ላለመለወጥ የሚደረግ ጥረት፣ ማለትም ለውጥን የመቃወም ዝንባሌ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ሃከየ ፣ ህክይ (ህኩይ)፣ ሃካይ፣ ህከያ፣ ህክየት እያለ ሲሄድ የንግሊዘኛ አቻ የለውም። ሃከየ ማለት ሃኬታም ሆነ ማለት ነው።
inertia = ሃኬት
inertia (verb) = ሃከየ
inert = ሃካይ
inert gas = ሃካይ ጋስ
inertial = ሃኬታዊ
inertial mass = ሃኬታዊ ቁሰት
the law of inertia = የሃኬት ሕግ
ሃኬታዊ ዋቢ መቃን (Inertial Reference Frame)
- ካሉበት የማይንቀሳቀሱ ማለትም አዴታቸውን (position) የማይለውጡ ርፍቅ (stationary) ወይም ድብድ (fixed) ናቸው ከሚባሉት ሩቅ ኮኮብች (distant stars) አንጻር ርፍቅ (stationary) የሆነ ወይም ደግሞ በቋሚ ሶፊሳ (constant velocity) የሚሶፍስ ዋቢ መቃን (reference frame) በልዩ ስም ሃኬታዊ ዋቢ መቃን (inertial reference frame) ይባላል።
- በሌላ አባባል ሃኬታዊ ዋቢ መቃን (inertial reference frame) ማለት ሩቅ ኮኮቦች ላይ የቆመ ነፃሪ (observer) ቢነፅረው (observe) ማለትም ቢመለከተው ካለበት የማይንቀሳቀስ ርፍቅ (stationary) ወይም ደግሞ በቀጥታ መስመር ላይ ባንድ አቅጣጫና በቋሚ ፍጥነት (constant velocity) የሚጓዝ ሁኖ የሚታይ ዋቢ መቃን (reference frame) ማለት ነው።
- ሃኬታዊ ዋቢ መቃን (inertial reference) ሃኬታዊ (inertial) የተባለበት ምክኒያት፣ የሃኬት ሕግ (the law of inertia) የሚባለው የጉሲን ሕግ (law of physics) የሚሰራው በዚህ ዓይነት መቃን ላይ ብቻ ስለሆነ ነው።
- ሃኬታዊ ያልሆነ ዋቢ መቃን አልሃኬታዊ ዋቢ መቃን (noninertial reference frame) ወይም ደግሞ ጥዱፍ ዋቢ መቃን (accelerated frame) ይባላል።
- ምድር (Earth) በፀሐይ ዙርያ የምትዞር በመሆኗ ሳቢያ፣ አቅጣጫዋን ስለምትቀያይር፣ ራሷ ምድር ወይም ደግሞ ምድር ላይ የሚገኝ ማናቸውም ነገር በትክክል ለመናገር ሃኬታዊ ዋቢ መቃን (inertial reference frame) ሊሆን አይችልም። ነገር ግን የምድር እንቅስቃሴ ሩቅ ኮኮቦች ላይ በቆመ ነጻሪ (observer) ቢነጸር ከንቅስቃሴ የማይቆጠር ኢምንት እንቀስቃሴ ስለሆነ፣ ምድር ላይ የቆመ ማናቸውም ነገር (ቤት፣ ዛፍ፣ ተራራ ወዘተ.) እንደ ሃኬታዊ ዋቤ መቃን ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
- የፅነራ መርሕ (principle of relativity) በሚባለው የጉሲን መርሕ (principle of physics) መሠረት ደግሞ ከሃኬታዊ ዋቢ መቃን (inertial reference frame) አንጻር በቋሚ ሶፊሳ (constant) የሚሶፍስ ማናችወም ዋቢ መቃን እሱ ራሱም ሃኬታዊ ዋቢ መቃን ነው። በሌላ አባባል አንድ መቃን ሃኬታዊ ከሆነ፣ ከዚህ መቃን አንጻር በቋሚ ሶፊሳ የሚሶፍስ ማናቸውም መቃን ሃኬታዊ ነው።
- ስለዚህም ምድር ገጽ ላይ የተደበደ (fixed) ማለትም የተቸከለ ማናችውም አካል (ቤት፣ ዛፍ፣ ተራራ ወዘተ. ) እንዲሁም ከዚህ አካል አንጻር በቋሚ ሶፊሳ (constant velocity) የሚሶፍስ፣ ማለትም በቀጤ መስመር ላይ ባንድ አቅጣጫና በቋሚ ፍጥነት የሚጓዝ ማናቸውም አካል እንደ ሃኬታዊ ዋቢ መቃን (inertial reference frame) ሊያገለግል ይችላል ማለት ነው።
- ሃኬታዊ ያልሆነ ዋቢ መቃን አልሃኬታዊ ዋቢ መቃን (noninertial reference frame) ወይም ጥዱፍ ዋቢ መቃን (accelerated reference frame) ይባላል።
inertial reference frame = ሃኬታዊ ዋቢ መቃን
noninertil reference frame = አልሃኬታዊ ዋቢ መቃን
accelerated reference frame = ጥዱፍ ዋቢ መቃን
nonaccelerated reference frame = አልጥዱፍ ዋቢ መቃን
ሁንዳ (Universe) እና ማትሁንዳ (Multiverse)
- በኦሮምኛ ሁንዳ ማለት ሁሉ፣ ሁሉም ማለት ነው። ይህም የኦሮምኛ ቃል universe የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል።
- ሁንዳ (universe) ማለት ሁለንተና እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ሆነደ (universalize)፣ ሁንድ (universalized)፣ ሆናዲ (ሆናጅ) [universalizer]፣ ሁነዳ (universalization) እያለ ይሄዳል።
- ሆነደ (universalize) ማለት አጠቃላይ አደረገ እንደማለት ሲሆን፣ ሁንድ (universalized) ማለት ደግሞ የተሆነደ ማለት ነው።
- ሁንዳ (universe) እና መዲና (ከተማ) ከሚሉት ደግሞ ሁንዲና (university) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- በተጨማሪ ደግሞ ማት (multi) እና ሁንዳ (universe) ከሚሉት ማትሁንዳ (multiverse)፣ ማትሁንዳዊ (multiversal) የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። ማትሁንዳ (multiverse) ማለት ብዙ ሁንዳወች ማለት ነው።
universe = ሁንዳ
universal = ሁንዳዊ
universal law = ሁንዳዊ ሕግ
universal law of gravitation = ሁንዳዊ የቁስበት ሕግ
universal gravitational constant = ሁንዳዊ የቁስበት ቋሚ
universal time = ሁንዳዊ ጊዜ
universalize = ሆነደ
universalization = ሁነዳ
university = ሁንዲና
multiverse (multiversal) = ማትሁንዳ፣ ማትሁንዳዊ
ክስተት (phenomenon) እና ሁንጊት (Event)
- ሁነት እና ድርጊት ከሚሉት ቃሎች ሁንጊት (event) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ሁንጊት (event) ማለት የሚሆን (የሆነ) ነገር፣ ድርጊት፣ ክስተት እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ሆነገተ፣ ሁንግት፣ ሆንጋቲ (ሆንጋች)፣ ሁንገታ፣ ሁንጋቴ፣ ሆንጋቶሽ እያለ ሲሄድ፣ የንግሊዘኛ አቻ የለውም።
- ክስተት (phenomenon) ተከሰተ እንደምንለው፣ ሁንጊት ሆነገተ እንላለን።
phenomenon = ክስተት
event = ሁንጊት
event (verb) = ሆነገተ
event horizon = ሁንጊት አድማስ
ፀናራዊ ጉሲን (Relativistic Physics)
ፀናራዊ ጉሲን (relativistic physics) ማለት የጉሲን ሕጎች (the laws of physics) በተለያዩ ዋቢ መቃኖች (reference frames) ላይ ያሏቸውን መልኮች የሚያነጻጽር ጉሲን (physics) ማለት ነው።
- ፀናራዊ ጉሲን (relativistic physics) ጋሊላዊ ፅነራ (Galilean Relativity) እና አንዲንጋዊ ፅነራ (Einstein’s Relativity) ተብሎ በሁለት ዐበይ ክፍሎች ይከፈላል።
- ጋሊላዊ ፅነራ (Galilean Relativity) የተሰየመው በጣልያናዊ ጉሲነኛ (physicist) በጋሊሊዮ ጋሊሊ (Galileo Galilei) ስም ነው።
- አንዲንጋዊ ፅነራ (Einstein’s Relativity) የተሰየመው በጀርመናዊው ጉሲነኛ (physicist) በአልበርት አንዲንጋ (Albert Einstein) ስም ነው። አንዲንጋ (Einstein) የሚለው ቃል የተገኘው አንድ ዲንጋ ከሚለው ነው፣ Einstein ማለት በጀርመንኛ አንድ ዲንጋ ማለት ነውና።
- በጋሊላዊ ፅነራ (Galilean Relativity) ላይ ጊዜ (time)፣ ርዝመት (length) እና ቁሰት (mass) ሁንዳዊ (universal) ናቸው። በሌላ አባባል ጊዜን፣ ርዝመትን እና ቁሰትን በመቆነን (measure) ማለትም በመለካት የሚገኙት እሴቶች (value) በቆናኙ ዋቢ መቃን (refererence) ላይ የማይመይፉ (independent) ማለትም የማይመኩ ሁንዳዊ እሴቶች (universal values) ናቸው። ለምሳሌ ያህል ባንድ ዋቢ መቃን (reference frame) ላይ የሚገኝ ነጻሪ (observer) አንድ ሁንጊት (event) ለመሆንገት የሚፈጅበትን ጊዜ ሲቆንን ያገኘው እሴት አስር ኑሲቃ (ten second) ቢሆን፣ በሌላ በማናቸውም ዋቢ መቃን ላይ የሚገኝ ነጻሪ ይህ ሁንጊት ለመሆንገት የሚፈጅበትን ጊዜ ቢቆንን የሚያገኘው እሴት ያው አስር ኑሲቃ ነው። ርዝመት (length) እና ቁሰትም (mass) እንደዚሁ።
- ባንዲንጋዊ ፅነራ (Einstein’s Relativity) ላይ ጊዜ (time)፣ ርዝመት (length) እና ቁሰት (mass) አልሁንዳዊ (nonuniversal) ናቸው፣ ማለትም ሁንዳዊ (universal) አይደሉም። ይህ ማለት ደግሞ ጊዜን፣ ርዝመትን እና ቁሰትን በመቆነን (measure) ማለትም በመለካት የሚገኙት እሴቶች (value) በቆናኙ ዋቢ መቃን (refererence) ላይ ይመይፋሉ (independent) ማለትም ይመካሉ ማለት ነው።
ላዕላብ (Superscript) እና ታሕታብ (Subscript)
- ባማረኛ ከተበ ማለት ጻፈ ማለት ሲሆን፣ ኪታብ ማለት ደግሞ ጽሑፍ ማለት ነው። ክትባት የሚለውም ቃል የተገኘው ከዚሁ ነው።
- ላዕል (super) እና ኪታብ (script) ከሚሉት ላዕላብ (superscript) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ታሐት (sub) እና ኪታብ (script) ከሚሉት ደግሞ ታሕታብ (subscript) የሚለውን ቃል እናገኛለን።
- ላዕላብ (superscript) ማለት ካናት በኩል የሚጻፍ ጽሑፍ እንደ ማለት ሲሆን፣ ታሕታብ (subscript) ማለት ደግሞ ከግር በኩል የሚጻፍ ጽሑፍ ማለት ነው።
የፀናራዊ እሴት ታሕታቦች
የፀናራዊ እሴት (relativistic value) ታሕታቦችን (subscripts)በተመለከተ የታሕታብ ስምምነት (subscript convention) የሚባል አጠቃላይ ስምምነት (general agreement) አለ። በዚህ አጠቃላይ ስምምነት መሠረት
- ከማናቸውም ዋቢ መቃን (reference frame) አንጻር የሚቆነን (measured) ማለትም የሚለካ የማናቸውም አካል (object) አዴት (position)፣ ሶፊሳ (velocity) እና ሌላም እሴት በሁለት ታሕታቦች (two subscripts) ይመለከታል።
- የመጀመርያው ታሕታብ (first subscript) ሁልጊዜም የሚወክለው አካሉን (the object) ሲሆን፣ ሁለተኛው ታሕታብ (second subscript) ደግሞ ሁልጊዜም የሚወክለው ዋቢ መቃኑን (the reference frame) ነው።
ምያጥ (Transform) እና ምየጣ (Transformation)
- በግእዝ መየጠ ማለት መለሰ፣ ቀለሰ፣ ቀለበሰ፣ አዞረ ማለት ነው። ይህም ቃል transform የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል። ግሱም ሲረባ መየጠ (transform)፣ ምይጥ (ምዩጥ) [transformed]፣ መያጢ (መያጭ) [transformer]፣ ምየጣ (transformation)፣ ምይጠት፣ ምያጤ፣ ምያጦሽ እያለ ይሄዳል።
- መየጠ (transform) ማለት ለወጠ በተለይም ደግሞ ቅርጽን እንደ ማለት ሲሆን፣ ምይጥ (ምዩጥ) [transformed] ወይም ምያጥ (transform) ማለት ደግሞ የተመየጠ ማለት ነው።
transform (noun) – ምያጥ
transform (verb) – መየጠ
transformation – ምየጣ፣
transformer – መያጢ፣ መያጭ
Fourier transform – ፉርየ ምያጥ
Fourier transformation – ፉርየ ምየጣ
ጋሊላዊ የሶፊሳወች ምየጣ (Galilean Transformation of Velocities)
- ጋሊላዊ የሶፊሳወች ምየጣ (Galilean velocity transformation) ማለት ከተለያዩ ወቢ መቃኖች (different reference frames) አንጻር የተቆነኑ (measured) ማለትም የተለኩ ሶፊሳወችን (velocities) በጋሊላዊ ፅነራ መሠረት (according to Galilean relativity) የሚያዛምድ (relate) ቀመር (formula) ማለት ነው።
- በሌላ አባባል፣ ጋሊላዊ የሶፊሳወች ምየጣ ማለት ሶፊሳወችን ካንድ ዋቢ መቃን ወደ ሌላ ዋቢ መቃን በጋሊላዊ ፅነራ መሠረት ለመመየጥ (transform) የሚያገለግል ቀመር ማለት ነው።
- በትክክል ለመናገር (strictly speaking) ጋሊላዊ ምየጣ (Galilean transformation) የሚሠራው በሃኬታዊ ዋቢ መቃኖች (inertial reference frames) ላይ ብቻ ነው። በሌላ አባባል ጋሊላዊ ምየጣ የሚሠራው ከሩቅ ኮኮቦች (distant stars) አንጻር በቋሚ ሶፊሳ (constant velocity) በሚሖሱ (move)፣ ማለትም በቀጤ መስመር ላይ በቋሚ ፍጥነት በሚሖሱ ዋቢ መቃኖች (reference frame) ላይ ብቻ ነው።
- ላብዛኞቹ ግልጋሎቶች ደግሞ ምድር እንደ ሃኬታዊ ዋቢ መቃን ልትወሰድ ትችላለች። ስለዚህም፣ ምድር ላይ ለተደበደ (fixed) ማለትም ለተቸከለ ርፍቅ ዋቢ መቃን (stationary reference frame) ወይም ከምድር አንጻር በቋሚ ሶፊሳ (constant velocity) በሚሶፍስ፣ ማለትም በቀጤ መስመር ላይ በቋሚ ፍጥነት በሚሖስ (move) ማናቸውም መቃን ላይ ጋሊላዊ ምየጣ ይሠራል።
የጋሊሊዮን የሶፊሳ ምየጣ (Galilean transformation of velocity) ቀመር (formula) የፍላስተኖችን ስሌጎናዊ ድመራ ዘዴ (triangle method of vector addition) በመጠቀም እንደሚከተለው በቀላሉ መረቸግ (derive) ማለትም ማግኘት ይቻላል።
በጋሊላዊ ምየጣ ላይ የታሕታቦች ስደራ (Order of Subscripts)
- ባማረኛ ሰደረ ማለት ደረደረ፣ ረደፈ፣ በመደዳ አስቀመጠ ማለት ነው። ይህም ቃል order የሚለውን የንግሊዘኛ ቃል ይተካልናል። ግሱም ሲረባ ሰደረ (to order)፣ ስድር (ስዱር) [ordered]፣ ሰዳሪ (ordering)፣ ስደራ (ordering) እያለ ይሄዳል።
- የጋሊላዊ ምየጣ እኩልታን (equation of Galilean transformation) ቀኝጌ (Right-hand Side, RHS) እና ግራጌ (Left-hand Side, LHS) ስናስተውል
- የእኩልታው ቀኝጌ (RHS) ውስጣዊ ታሕታቦች (inner subscripts) [ማለትም ሁለቱ M] ያውቴ (same) ናቸው።
- የእኩልታው ቀኝጌ (RHS) ውጫዊ ታሕተቦች (outer subscripts) ስድረት (order) ከእኩልታው ግራጌ (LHS) ታሕታቦች ስድረት ጋር ያውቴ (same) ነው።
ጋሊላዊ ምየጣ ለሦስት መቃኖች
- የጋሊላዊ ምየጣ ቀመር (Galilean transformation formula) ለሁለት ዋቢ መቃኖች (reference frames) ያለው መልከ የተገኘው አዴት ፍላስተኖችን (positon vectors) በስሌጎን ዘዴ (triangle method) በመደመር ነው።
- ቁጥራቸው ሦስት ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ዋቢ መቃኖች (reference frames) ላይ የጋሊላዊ ምየጣ ቀመር ያለውን መልክ ለማገኘት የሚያስፈልገው ደግሞ አዴት ፍላስተኖችን (positon vectors) በማትጎን ዘዴ (polygon method) መደመር ብቻ ነው።
ርስበርስ ፅነራወች
- ፀናራዊ ሶፊሳ (relative velocity) VBA ሁልጊዜም የፀናራዊ ሶፊሳ (relative velocity) VAB ሉንታ (negative) ነው።
- በሌላ አባባል የርስበርስ ፀናራዊ ሶፊሳወች VAB እና VBA የርስበርስ ሉንታወች (negatives of each other) ናቸው።
- አሁንም በሌላ አባባል ማናቸውም አካል A ከሌላ ከማናቸውም አካል B አንጻር ያለው ፀናራዊ ሶፊሳ (relative velocity)፣ አካል B ከአካል A አንጻር ያለውን ሶፊሳ ሉንታ (negative) ነው።
ምሳሌ (የርስበርሰ ፀናራዊ ሶፊሳወች)፤ ኮንኮል (car) A ከምድር (ground) አንጻር በ 85 kmh ፍጥነት (speed) ወደ ቀኝ ቢጓዘና፣ ኮንኮል B ደግሞ ከምድር አንጻር በ 75 kmh ፍጥነት ወደ ቀኝ ቢጓዝ፣ ኮንኮል A ከኮንኮል B አንጻር፣ እንዲሁም ኮንኮል B ከኮንኮል A አንጻር ያለውን ፀናራዊ ሶፊሳ (relative velocity) ፈልግ።
ምሳሌ (የርስበርሰ ፀናራዊ ሶፊሳወች)፤ ኮንኮል (car) A ከምድር (ground) አንጻር በ 25 m/s ፍጥነት (speed) ወደ ቀኝ ቢጓዘና፣ ኮንኮል B ደግሞ ከምድር አንጻር በ 35 m/s ፍጥነት ወደ ግራ ቢጓዝ፣ ኮንኮል A ከኮንኮል B አንጻር፣ እንዲሁም ኮንኮል B ከኮንኮል A አንጻር ያለውን ፀናራዊ ሶፊሳ (relative velocity) ፈልግ።
ምሳሌ (መስቀለኛ መንገድና ፀናራዊ ሶፊሳ)፤ ሁለት ኮንኮሎች (two cars) A እና B በ 90o ወደሚመሳቀሉ ሩንጋ (perpendicular) መስቀለኛ መንገዶች እየተቃረቡ ነው። ኮንኮል A በ 40 kmh ፍጥነት ወደ ምሥራቅ ይጓዛል። ኮንኮል B ደግሞ በ 60 kmh ፍጥነት ወደ ሰሜን ይጓዛል። ኮንኮል A ከኮንኮል B አንጻር ያለውን ፀናራዊ ሶፊሳ (relative velocity) ፈልግ።
አየር (Air)፣ ሰቴ (Plane) እና ሰታይ (Pilot)
- አየር (air) ከሚለው አየረ (aerate) የሚለውን ግስ እናገኛለን። አየረ (aerate) ማለት አየር አስገባ፣ አናፈሰ እንደ ማለት ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ አየረ (aerate)፣ እይር (እዩር) [aerated]፣ አያሪ (aerator)፣ እየራ (aeration) እያለ ይሄዳል።
- ሰቴ (plane) ማለት ለጥ ያለ፣ ጠፍጣፋ ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ሰቲት ከሚለው የግእዝ ቃል ነው። በግእዝ ሰቲት ማለት ለጥ ያለ፣ የተዘረጋ ማለት ነው፣ ሰታቴ (ድስት)፣ ሰቲት ሑመራ እንዲሉ።
- አየር እና ሰቴ (plane) ከሚሉት አየርሰቴ (airplane) የሚለውን ቃል እናገኛለን። አየርሰቴ (airplane) ማለት አይሮፕላን የምንለው ሲሆን፣ ባጭሩ ደግሞ ሰቴ (plane) ይባላል።
- ያየርሰቴ አብራሪ ደግሞ አየርሰቴ ሰታይ (airplane pilot) ወይም ባጭሩ ሰቴ ሰታይ፣ ይበልጥ ባጭሩ ደግሞ ሰታይ (pilot) ይባላል።
air = አየር
aerate = አየረ
airplane (plane) = አየርሰቴ (ሰቴ)
aircraft = አየር ኪናግ
airport = አየር ወደብ
pilot = ሰታይ፣ አብራሪ
ፊትጌ ንፋስ (Headwind)፣ ኋልጌ ንፋስ (Tailwind) እና ጎንጌ ንፋስ (Crosswind)
በሰቴ (plane) ላይ የሚነፍሱ ንፋሶች (winds) ፊትጌ ንፋስ (headwind)፣ ኋልጌ ንፋስ (tailwind) እና ጎንጌ ንፋስ (crosswind) ተብለው በሦስት ይከፈላሉ።
- ፊትጌ ንፋስ (headwind) ማለት ከሰቴው በፊት በኩል ወይም በግንባር በኩል የሚነፍስ ንፋስ ማለት ነው። በሌላ አባባል ፊትጌ ንፋስ ማለት ከሰቴው ግንባር (head) ወደ ሰቴው ጅራት (tail) የሚነፍስ ንፋስ ማለት ነው። አሁንም በሌላ አባባል ፊትጌ ንፋስ ማለት ሰቴውን ወደኋላ የሚገፋ ንፋስ ማለት ነው። ፊትጌ ማለት በፊት በኩል ማለት ነው፣ ራስጌ፣ ግርጌ እንዲሉ።
- ኋልጌ ንፋስ (tailwind) ማለት ከሰቴው በኋላ በኩል ወይም በጅራት በኩል የሚነፍስ ንፋስ ማለት ነው። በሌላ አባባል ኋልጌ ንፋስ ማለት ከሰቴው ጅራት (tail) ወደ ሰቴው ግንባር (head) የሚነፍስ ንፋስ ማለት ነው። አሁንም በሌላ አባባል ኋልጌ ንፋስ ማለት ሰቴውን ወደፊት የሚገፋ ንፋስ ማለት ነው።
- ጎንጌ ንፋስ (tailwind) ማለት ከሰቴው በጎን በኩል የሚነፍስ ንፋስ ማለት ነው። በሌላ አባባል ጎንጌ ንፋስ ማለት ሰቴውን ወደጎን የሚገፋ ንፋስ ማለት ነው።
ንፋስ ሶፊሳ (Windvelocity)፣ ንፋሳንጻር ሶፊሳ (Airvelocity) እና ምድራንጻር ሶፊሳ (Groundvelocity)
ያየር ሰቴ በረራ (airplane flight) ንፋስ ሶፊሳ (windvelocity)፣ ንፋሳንጻር ሶፊሳ (Airvelocity) እና ምድራንጻር ሶፊሳ (groundvelocity) የሚባሉ ሦስት ሶፊሳወችን (velocities) የሚያካትት በረራ ነው።
- ንፋስ ሶፊሳ (windvelocity) ማለት ንፋስ (wind) የሚነፍስበት ፍጥነት (speed) እና አቅጣጫ (direction) ማለት ነው። በሌላ አባባል ንፋስ ሶፊሳ ማለት ንፋስ ከምድር አንጻር ያለው ሶፊሳ ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል አየሩ ንፋስ የሌለው (ማለትም ፀጥ ረጭ ያለ) ከሆነ፣ ንፋስ ሶፊሳ (windvelocity) ዳዶ (zero) ይሆናል።
- ንፋሳንጻር ሶፊሳ (airvelocity) ማለት ሰቴው ከንፋስ አንጻር ያለው ፍጥነት (speed) እና አቅጣጫ (direction) ማለት ነው።
- ምድራንጻር ሶፊሳ (groundspeed) ማለት ሰቴው ከምድር (ground) አንጻር ያለው ፍጥነት (speed) እና አቅጣጫ (direction) ማለት ነው።
ያየር ጉዞ ጋሊላዊ ምየጣ
ያየር ጉዞ ጋሊላዊ ምየጣ (Galilean transformation for air travel) በሚከተለው የፀናራዊ ሶፊሳወች (relative velocitis) ፍላስተን እኩልታ (vector equation) ይሰጣል።
ምሳሌ (መነሻ ፍጥነት በፊትጌ ንፋስ)፤ ያቅሙን የተጫነ (fully loaded) 747 ሰቴ ከምድር ይነሳ ዘንድ ከንፋስ አንጻር ያለው ፍጥነት በቅርበዛ (approximately) 300 km/h መሆን አለበት። ፍጥነቱ 40 km/h የሆነ ፊትጌ ነፋስ (headwind) ባለበት ሁኔታ፣ የሰቴው መነሻ ፍጥነት (takeoff speed) ከምድር አንጻር ምን ያህል መሆን አለበት?
ምሳሌ (መነሻ ፍጥነት በኋልጌ ንፋስ)፣ ያቅሙን የተጫነ (fully loaded) 747 ሰቴ ከምድር ይነሳ ዘንድ ከንፋስ አንጻር ያለው ፍጥነት በቅርበዛ (approximately) 300 km/h መሆን አለበት። ፍጥነቱ 40 km/h የሆነ ኋልጌ ነፋስ (headwind) ባለበት ሁኔታ፣ የሰቴው መነሻ ፍጥነት (takeoff speed) ከምድር አንጻር ምን ያህል መሆን አለበት?
ምሳሌ (ጎንጌ ንፋስና ምድራንጻር ፍጥነት)፣ ያንድ ሰቴ (plane) ሰታይ (pilot) የሰቴውን ብሶል (compass) ከሰቴው መሪዳ (dashboard) ማለትም መሪ ሰሌዳ ላይ ሲመለከት የሰቴው ንፋሳንጻር ሶፊሳ 215 km/h ወደ ምዕራብ መሆኑን፣ የንፋሱ ሶፊሳ ደግሞ በ 75 km/h በ 75o ምሥራቅ ሰሜን (North of East) አቅጣጫ መሆኑን ይመለከታል። የሰቴውን ምድራንጻር ሶፊሳ (Groundvelocity) ፈልግ።
የውሃ ጉዞ ጋሊላዊ ምየጣ
የውሃ ጉዞ ጋሊላዊ ምየጣ (Galilean transformation for water travel) በሚከተለው የፀናራዊ ሶፊሳወች (relative velocitis) ፍላስተን እኩልታ (vector equation) ይሰጣል።
- ውሃ ሶፊሳ (watervelocity) ማለት ውሃ (water) የሚፈስበት ፍጥነት (speed) እና አቅጣጫ (direction) ማለት ነው። በሌላ አባባል ውሃ ሶፊሳ ማለት ውሃ ከምድር አንጻር ያለው ሶፊሳ ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል ውሃው የማይንቀሳቀስ (ማለትም ፀጥ ረጭ ያለ) ከሆነ፣ ውሃ ሶፊሳ (watervelocity) ዳዶ (zero) ይሆናል።
- ውሃንጻር ሶፊሳ ማለት ጀልባው ከውሃ አንጻር ያለው ፍጥነት (speed) እና አቅጣጫ (direction) ማለት ነው።
- ምድራንጻር ሶፊሳ (groundvelocity) ማለት ጀልባው ከምድር (ground) አንጻር ያለው ፍጥነት (speed) እና አቅጣጫ (direction) ማለት ነው።
ምሳሌ (ወንዝ የምታቋረጥ ጀልባ)፣ አንድ ወንዝ በ 2.55 km/h ፍጥነት ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ይፈሳል። አንድ ጀልባ ደግሞ አፍንጫዋን ቀጥታ ወደ ሰሜን (ማለትም ወደ ወንዙ ዳርቻ) አድርጋ በ 8 km/h ውሃንጻር ፍጥነት ወንዙን ለማቋረጥ ትሞክራለች። የጀልባዋን ምድራንጽር ሶፊሳ (groundvelocity) ፈልግ።
ምሳሌ (በዝናብ መንዳት)፣ አንድ ኮንኮለኛ (car driver) ኮንኮሉን (car) በቀጤ አግዳሜ መንገድ (straight horizontal road) ላይ በ 4.7 m/s ፍጥነት ሲነዳ፣ ዝናቡ ከወርጃሚ (vertical) ጋር 25o ዘዌ (angle) ሲሰራ ይመለከታል። የዘናቡን ሶፊሳ (velocity) ከኮንኮሉ አንጻር (relative to the car) እና ከምድር አንጻር (relative to the ground) ፈልግ።
መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com