Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124
Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124

መስፍን አረጋ
ተወርዋሪ ኮኮብ፣ እሳት የሚተፋ
በራሱ ነበልባል ተቃጥሎ የጠፋ
በጠቆረው ሰማይ ነበረ በይፋ።
ዮሐንስ አድማሱ (ተወርዋሪ ኮኮብ፣ 1954 ዓም)
አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ሦስተኛ …
የደረጃ ቁጥሮች አንደኛ (first)፣ ሁለተኛ (second)፣ ሶስተኛ (third) … እያሉ ይሄዳሉ። እነዚህን ቃሎች እጅ ከሚለው ቃል ጋር በማጣመር ደግሞ አንደኛጅ (first-hand)፣ ሁለተኛጅ (second-hand)፣ ሶስተኛጅ (third-hand) … የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። ለምሳሌ ያህል አንደኛጅ ጭሰት (first-hand smoking)፣ ሁለተኛጅ ጭሰት (second-hand smoking)፣ ሶስተኛጅ ጭሰት (third-hand smoking) … ይሆናሉ። ሶስተኛጅ ጭሰት ማለት ልብሶችን፣ እቃወችንና የመሳሰሉትን ለበከለ የሲጋራ ጭስ መጋለጥ ማለት ሲሆን፣ ካንደኛጅና ከሁለተኛጅ ጭሰት በማይተናነስ ደረጃ አደገኛ ነቀርሳዞግ (carcinogen) ነው።
first-hand = አንደኛጅ
second-hand = ሁለተኛጅ
third-hand = ሶስተኛጅ
fourth-hand = አራተኛጅ
ሃዴ፣ ክሌ፣ ስሌ …
አሃዱ፣ ክልኤቱ፣ ሠለስቱ፣ አርባዕቱ፣ ኀምስቱ፣ ስድስቱ፣ ሰባዐቱ፣ ስምንቱ፣ ተስዐቱ፣ ዐሥርቱ ከሚሉት የግእዝ ቁጥሮች፣ ሃዴ (mono)፣ ክሌ (bi)፣ ስሌ (tri)፣ ራቤ (quatri) … የሚሉትን፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ፊልጡፎች (prefixex) ማለትም ባዕድ መነሻወች እናገኛለን።
mono = ሃዴ
bi (di) = ክሌ
tri = ስሌ
quadri = ራቤ
penta = ሃሜ
hexa = ሳዴ
hepta = ሳቤ
octa = ሳሜ
nona = ታሴ
deca = አሴ
eleventh = አስሃዴ
dodeca = አስክሌ
thirteenth = አስስሌ
fourteenth = አስራቤ
fifteenth = አስሃሜ
sixteenth = አስሳዴ
seventeenth = አስሳቤ
eighteenth = አስሳሜ
ninteenth = አስታሴ
twentieth = ላቲማ
ላቲማ ማለት በወላይትኛ ሃያ ማለት ነው። እነዚህን ፊልጡፎች በመጠቀም የሚከተሉትን የመሳሰሉ ቃሎች እናገኛለን።
monopole = ሃዴዋልታ
dipole = ክሌዋልታ
quadrilateral = ራቤጎን
pentagon = ሃሜጎን
hexagon = ሳዴጎን
octagon = ሳሜጎን
nonagon = ታሴጎን
decagon = አሴጎን
dodecagon = አስክሌጎን
icosahedron = ላቲማግጽ
ሃዴቻ፣ ክሌቻ፣ ስሌቻ…
ሃዴ፣ ክሌ፣ ስሌ … ከሚሉት ቃሎች ሃዴቻ (mono)፣ ክሌቻ (double)፣ ስሌቻ (triple) … የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
mono = ሃዴቻ
double = ክሌቻ
triple = ስሌቻ
quadruple = ራቤቻ
quintuple = ሃሜቻ
sextuple = ሳዴቻ
septuple = ሳቤቻ
octuple = ሳሜቻ
decuple = አሴቻ
ሃዴቻን፣ ክሌቻን፣ ስሌቻን …
ሃዴቻ፣ ክሌቻ፣ ስሌቻ … ከሚሉት ቃሎች ሃዴቻን (monolet)፣ ክሌቻን (doublet)፣ ስሌቻን (triplet) … የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
monolet = ሃዴቻን
doublet = ክሌቻን
triplet = ስሌቻን
quadruplet = ራቤቻን
quintuplet = ሃሜቻን
sextuplet = ሳዴቻን
septuplet = ሳቤቻን
octuplet = ሳሜቻን
nonuplet = ታሴቻን
decuplet = አሴቻን
ሃዴማይ፣ ክሌማይ፣ ስሌማይ …
ሃዴ፣ ክሌ፣ ስሌ … ከሚሉት ቃሎች ሃዴማይ (primary)፣ ክሌማይ (secondary)፣ ስሌማይ (tertiary) … የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን።
primary = ሃዴማይ
secondary = ክሌማይ
tertiary = ስሌማይ
quaternary = ራቤማይ
senary = ሳዴማይ
septenary = ሳቤማይ
octonary = ሳሜማይ
nonary = ታሴማይ
denary = አሴማይ
ክልኤት፣ ሥልኤት፣ ራብኤት …
ክሌ፣ ስሌ፣ ራቤ … ከሚሉት ቃሎች ክልኤት (dual)፣ ስልኤት (tri)፣ ራብኤት (quad) … የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። ክልኤት ከሚለው ቃል ክልኤትፍና (dualism)፣ ክልኤትፈናኝ (dualist)፣ ክልኤትነት (duality) የመሳሰሉትን ቃሎች እናገኛለን። ግሱም ሲረባ ክልኤት ፈነተ (dualize)፣ ክልኤት ፍንት (dualized)፣ ክልኤት ፈናች (dualizer)፣ ክልኤት ፍነታ (dualization) እያለ ይሄዳል።
dual = ክልኤት
duality = ክልኤትነት
dualism = ክልኤትፍና
dualist = ክልኤትፈናኝ (ክልኤተኛ)
ለምሳሌ ያህል የቁስ ክልኤት ጠባይ (dual property of matter)፣ የብርሃን ክልኤትነት (duality of light) ይሆናሉ።
ደገመ፣ ሰለሰመ፣ አረተመ …
የድግግም ቁጥሮች ደገመ (repeat)፣ ሰለሰመ (three-peat)፣ አረተመ (four-peat)፣ ሃመሰመ (five-peat)፣ ሰደሰመ (six-peat)፣ ሰበተመ (seven-peat)፣ ሰመተመ (eight-peat)፣ ዘጠነመ (nine-peat)፣ ኮደነመ (ten-peat) ይሆናሉ። ሠለሰመ ማለት ሦስት ጊዜ በተከታታይ ደጋገመ ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል ሶስት ጊዜ በተከታታይ ማሸነፍ፣ ወይም ደግሞ ባንድ ጨዋታ ላይ ሦስት ግቦችን ማስገባት ሠለሰመ ይባላል። ሠለሰመ የሚለው ቃል ቆብጣለ (hat-trucj) ሊባልም ይችላል። ከዚህም ቆብጥሎሽ (hat-trick) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ኮደነመ የሚለው ቃል የተገኘው ኩደን (አስር) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ነው።
የሰለሰመ ግስ ሲረባ ሰለሰመ፣ ስልስም፣ ሰልሳሚ፣ ስልሰማ እያለ ይሄዳል። የአረተመ ግስ ሲረባ አረተመ፣ እርትም፣ አርታሚ፣ እርተማ እያለ ይሄዳል። የሃመሰመ ግስ ሲረባ ሃመሰመ፣ ህምስም፣ ሃምሳሚ፣ ህምሰማ እያለ ይሄዳል። የቀሩትም በተመሳሳይ መንገድ ይረባሉ።
repeat = ደገመ
three-peat = ሰለሰመ
hat-trick = ቆብጣለ
four-peat = አረተመ
six-peat = ሰደሰመ
seven-peat = ሰበተመ
eight-peat = ሰመተመ
nine-peat = ዘጠነመ
ten-peat = አሰነመ
የቁጥሮች ፊልጡፎች
ፊልጡፍ (prefix) የሚለው ቃል የተፈጠረው ፊት እና ልጡፍ ከሚሉት ቃሎች ሲሆን፣ ትርጉሙም ባዕድ መነሻ ማለት ነው፣ ሰብዓዊ ብለው ኢሰብዓዊ እንዲሉ። በተመሳሳይ መንገድ ኋላ እና ልጡፍ ከሚሉት ቃሎች ኋልጡፍ (suffix) ማለትም ባዕድ መድረሻ የሚለውን ቃል እናገኛለን፣ ሆድ ብለው ሆዳም እንዲሉ። የቁጥር ፊልጡፎች ማለት የቁጥርን መጠን ለመግለጽ የሚያገለግሉ ፊልጡፎች ማለት ነው።
አሃዱ፣ ክልኤቱ፣ ሰለስቱ፣ አርባዕቱ፣ ኀምስቱ፣ ስድስቱ፣ ሰባዐቱ፣ ስምንቱ፣ ተስዐቱ፣ ዐሥርቱ ከሚሉት የግእዝ ቁጥሮችና ጃኖ (ትልቅ) ከሚለው ያማረኛ ቃል፣ እንዲሁም ጢኖ (ትንሽ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል ፣ የሚከተሉትን የቁጥር ፊልጡፎች (number prefixes) እናገኛለን።
deca [10 = 101] = አሴ
deci [1/10 = 10-1] = አሲ
hecto [100 = 102] = ቶሴ
centi [1/100 = 10-2] = ቶሲ
kilo [1000 = 103] = ሃጃኖ
milli [1/1000 = 10-3] = ሃጢኖ
mega [106 = (103)2] = ካልጃኖ
micro [10-6 = (10-3)2] = ካልጢኖ
giga [109 = [(103)3] = ሳልጃኖ
nano [10-9 = [(10-3)3] = ሳልጢኖ
tera [1012 = (103)4] = ራብጃኖ
pico [10-12 = (10-3)4] = ራብጢኖ
peta [1015 = (103)5] = ሃምጃኖ
femto [10-15 = (10-3)5] = ሃምጢኖ
exa [1018 = (103)6] = ሳድጃኖ
atto [10-18 = (10-3)6] = ሳድጢኖ
zeta [1021 = (103)7] = ሳብጃኖ
zepto [10-21 = (10-3)7] = ሳብጢኖ
yota [1024 = (103)8] = ሳምጃኖ
yocto [10-14 = (10-3)8] = ሳምጢኖ
ronna [1027 = (103)9] = ታስጃኖ
ronto [10-27 = (10-3)9] = ታስጢኖ
quetta [1030 = (103)10] = አስጃኖ
quecto [10-30 = (10-3)10] = አስጢኖ
የቁጥፍ ፊልጡፎች የንግሊዘኘ ስሞች ስርዓትን ያልተከተሉ ስለሆኑ፣ በቃል ለማጥናት በጣም አስቸጋሪ ናቸው። አስተማሪ በመሆኔ ይህን የተማሪወች ችግር አውቀዋለሁ፣ እረዳዋለሁም። ስለዚህም፣ በንግሊዘኛ ተናጋሪወች ዘንድ በሰፊው የሚታወቁት የቁጥር ፊልጡፎች በጣም ጥቂቶቹ፣ ምናልባትም ሃጅኖ (kilo) እና ካልጅኖ (mega) ብቻ ናቸው።
የቁጥር ፊልጡፎች ያማረኛ ስያሜወች ግን አሀዱ፣ ክልኤቱ፣ ሰለስቱ … የሚለውን የግእዝ ቁጥር አካሄድ እንዲከተሉ ስላደረኳቸው በቀላሉ ሊታወሱ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል ሃጅኖ (kilo) የሚለው ፊልጡፍ የተገኘው፣ አሃድ እና ጃኖ የሚሉትን ቃሎች በማጣመር ሲሆን፣ ሃጢኖ (milli) የሚለው ፊልጡፍ የተገኘው ደግሞ አሃድ እና ጢኖ የሚሉትን ቃሎች በማጣመር ነው።
አሴ (deca, deka) እና አሲ (deci) የሚሉት ፊልጡፎች የተገኙት፣ አስር ከሚለው ቃል ሲሆን፣ ቶሴ (hecto) እና ቶሲ (centi) የሚሉት ፊልጡፎች የተገኙት ደግሞ መቶ ከሚለው ያማረኛ ቃል ነው። እነዚህን የቁጥር ፊልጡፎች በመጠቀም የሚከተሉትን የመሳሰሉ ቃሎች እናገኛልን።
centimeter = ቶሲሜትር
centigram = ቶሲግራም
millimeter = ሃጢኖሜትር
milligram = ሃጢኖግራም
micrometer = ካልጢኖሜትር
microgram = ካልጢኖግራም
kilometer = ሃጃኖሜትር
kilogram = ሃጃኖግራም
kilowatt = ሃጃኖዋት
kilohertz = ሃጃኖሄርዝ
megawatt = ካልጃኖዋት
megahertz = ካልጃኖሄርዝ
gigawatt = ሳልጃኖዋት
gigahertz = ሳልጃኖሄርዝ
እንግሊዘኛውን እንዳለ ወስደን፣ ሚሊዮን፣ ቢሊዮን፣ ትሪሊዮን … የምንላቸው ቁጥሮች፣ ያማረኛ አቻወቻቸው ካልጅኖ፣ ሳልጅኖ፣ ራብጅኖ … ይሆናሉ። ካልጅኖ ማለት አንድ ሺ ሺወች ማለት ስለሆነ፣ ሌላው ስሙ ሺሺ ነው።
ten [10 = 101] = አሴ (አስር)
tenth [1/10 = 10-1] = አሲ
hundred [100 = 102] = ቶሴ
hundredth [1/100 = 10-2] = ቶሲ
thousand [1000 = 103] = ሃጃኖ (ሺ)
thousandth [1/1000 = 10-3] = ሃጢኖ
million [106 = (103)2] = ካልጃኖ (ሺሺ)
millionth [10-6 = (10-3)2] = ካልጢኖ
billion [109 = [(103)3] = ሳልጃኖ
billionth [10-9 = [(10-3)3] = ሳልጢኖ
trillion [1012 = [(103)4] = ራብጃኖ
trillionth [10-12 = (10-3)4] = ራብጢኖ
quadrillion [1015=(103)5] = ሃምጃኖ
quadrillionth[10-15=(10-3)5]= ሃምጢኖ
quintillion [1018= (103)6] = ሳድጃኖ
quintillionth [10-18 = (10-3)6] = ሳድጢኖ
sextillion [1021 = (103)7] = ሳብጃኖ
sextillionth [10-21 = (10-3)7] = ሳብጢኖ
septillion [1024 = (103)8] = ሳምጃኖ
septillionth [10-24 = (10-3)8] = ሳምጢኖ
octillion[1027 = [(103)9] = ታስጃኖ
octillionth [10-27 = (10-3)9] = ታስጢኖ
nonillion [1030 = (103)10] = አስጃኖ
nonillionth [10-30 = (10-3)10] = አስጢኖ
ከነዚህ ሰንጠረዦች እንደምንመለከተው፣ በንግሊዘኛ ስሜ የሌላቸው እስከሚመስሉ ድረስ የማይታወቁ ቁጥሮች፣ ባማረኛ ግን በቀላሉ ሊታወሱ የሚችሉ ስያሜወች አሏቸው። በሌላ አባባል፣ ቁጥሮችን በተመለከ አማረኛ ከንግሊዘኛ የላቀ ሆነ ማለት ነው። በሌሎች ዘርፎችም አማረኛን ከንግሊዘኛ የላቀ ለማደረግ የሚያስፈልገው ፍላጎት ብቻ ነው፣ ቋንቋው እንዳበጁት የሚበጅ ነውና።
ከቁጥሮች ስያሜ አንጻር፣ ሌላው የንግሊዘኛ ችግር ቢሊዮን (billion) የሚለውን ቃል የተመለከተ ነው። ባሜሪቃኖች (USA) ዘንድ፣ ቢሊዮን ማለት አንድ ሃጃኖ ካልጃኖ (one thousand million)፣ ማለትም 103 × 106 = 109 ማለት ሲሆን፣ በንግሊዞች (UK) ዘንድ ደግሞ፣ ቢሊዮን ማለት አንድ ካልጃኖ ካልጃኖ (one million million)፣ ማለትም 106 × 106 = 1012 ማለት ማለት ነው። ያማረኛ የቁጥር ስያሜወች ግን ይህ ድንግረት (confusion) የለባቸውም። አሜሪቃኖች ቢሊዮን የሚሉት ባማረኛ ሳልጃኖ የሚባለውን ሲሆን፣ እንግሊዞች ቢሊዮን የሚሉት ግን ባማረኛ ራብጃኖ የሚባለውን ነው።
ያሜሪቃ ቢሊዮን [109 = (103)3] = ባማረኛ ሳልጃኖ
የንግሊዝ ቢሊዮን [1012 = (103)4] = ባማረኛ ራብጃኖ
ካሜሪቃ ቢሊዮን አትቀበል፣ ከንግሊዝ ቢሊዮን አትበደር።
ሃጃኖ (thousand)፣ ካልጃኖ (million)፣ ሳልጃኖ (billion)፣ ራብጃኖ (trillion) … ከሚሉት የቁጥር ፈልጡፎች፣ ሃጅነኛ (“thousander”)፣ ካልጅነኛ (millionaire)፣ ሳልጅነኛ (billionaire)፣ ራብጅነኛ (trillionaire) … የመሳሰሉትን ቃሎች እናገኛለን።
thousander = ሃጅነኛ
millionaire = ካልጅነኛ
billionaire = ሳልጅነኛ
trillionaire = ራብጅነኛ
የጦቢያ ብር በሚበርበት መጥን ከቀጠለ፣ በካልጅነኖች (millionaires) ብዛት ጦቢያ ካለም አንደኛ የምትሆነበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። ምናልባትም ደግሞ ያለማችን የመጀመርያው ራብጅነኛ (trillionaire) ጦቢያዊ ሊሆን ይችላል።
ቶሲ (centi) ከሚለው የቁጥር ፊልጡፍ እና ደረጃ ከሚለው ቃል፣ ቶሲረጃ (centigrade) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ከዚህም ቶሲረጃ ጉላፕ (centigrade degree, degree centigrade) የሚለውን ቃል እናገኛለን። ጉላፕ (degree) የሚለው ቃል የተገኘው ጎለመ (ከፈለ፣ ለየ) ከሚለው ያማረኛ ቃል ነው።
ቶሲረጃ ጉላፕ የሙቀት ቶካድ (temperature unit) ሲሆን፣ ሌላው ስሙ ሴልሸስ ጉላፕ (Celsius degree) ነው። ቶካድ (unit) ማለት መለኪያ (መስፈሪያ) ማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘው ደግሞ ቶኮ (አንድ) ከሚለው የኦሮምኛ ቃል እና አሃድ (አንድ) ከሚለው የግእዝ ቃል ነው። ሌሎቹ የቀሙት ቶካዶች ፋረንሃይት ጉላፕ (Farenheit degree) እና ኬልቪን ጉላፕ (Kelvin degree, degree Kelvin) ናቸው። ቶሲረጃ ጉላፕ (ሴልሸስ ጉላፕ) ባጭሩ ቶጉ (ሴጉ)፣ ፋረንሃይት ጉላፕ ባጭሩ ፋጉ፣ ኬልቪን ጉላፕ ደግሞ ባጭሩ ኬጉ ይባላል። የነጻነት ጉላፕ (degree of freedom) ደግሞ ባጭሩ ነጉ ይባላል።
degree = ጉላፕ
unit = ቶካድ
centigrade = ቶሲረጃ
centigrade degree = ቶሲረጃ ጉላፕ (ቶጉ)
Celsius degree = ሴልሸስ ጉላፕ (ሴጉ)
Kelvin degree = ኬልቪን ጉላፕ (ኬጉ)
Fahrenheit degree = ፋረንሃይት ጉላፕ (ፋጉ)
degree of freedom = የነጻነት ጉላፕ (ነጉ)
መስፍን አረጋ
mesfinamharic.com
mesfinarega.com
mesfin.arega@gmail.com