Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124
Physical Address
304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124

መስፍን አረጋ
ንጽጽር
ካማረኛ ጉድለቶች (shortcomings) አንዱ ንጽጽርን (comparison) በቀላሉ ለመግለጽ አለመቻሉ ነው። ለምሳሌ ያህል ትልቅ በሚለው ቅጽል ለማነጻጸር ስንፈልግ፣ በጣም ትልቅ፣ እጅግ በጣም ትልቅ እንላለን። ይህ ግን አሻሚ ከመሆኑም በላይ የተንዛዛ በመሆኑ ምክኒያት አመች አይደለም። በጣም ትልቅ ስንል ያንድን ነገር ትልቅነት እየገለጽን ወይም ደግሞ የሁለት ነገሮችን ትልቅነት እያነጻጸርን ሊሆን ይችላል። ይህን አሻሚነትና መንዛዛት ለማስወገድ ስል፣ ላማረኛ ንጽጽርን በሚከተለው መንገድ ፈጥሬለታለሁ።
ለምሳሌ ያህል ጥሩ (good) የሚለውን ብንወስድ፣ በጣም ጥሩ ለማለት ፐጥሩ (better) እንላለን፣ እጅግ በጣም ጥሩ ለማለት ደግሞ ዥጥሩ (best) እንላለን። ፊደሎች ፐ እና ዠ ለንጽጽር የተመረጡበት ምክኒያት፣ በነዚህ ፊደሎች የሚጀምሩ ብዙ ቃሎች ስለሌሉ ነው። በተመሳሳይ መንገድ ትልቅ (larger)፣ ፐትልቅ (larger)፣ ዥትልቅ (largest)፣ ትንሽ (small)፣ ፐትንሽ (smaller)፣ ዝትንሽ (smallest)፣ ውብ (beautiful)፣ ፐውብ (more beautiful)፣ ዥውብ (most beautiful) ይሆናሉ።
ለምሳሌ ያህል ለዠመጥፎ ተዘጋጅ (prepare for the worst)፣ ዠመጥፎውን ጠብቅ (expect the worst)፣ ዠመጥፎ ረገድ (the worst case) ይሆናሉ። እንዲሁም the nearer the church, the further from God የሚለው የፈረንጆች ብሂል ለቤተሔር ፐቅርብ፣ ላብሔር ፐሩቅ ተብሎ ባጭሩ ይተረጎማል። በተመሳሳይ መንገድ የሚከተሉትን ዐረፍተነገሮች እናገኛልን።
ማጥበቅ፣ ማላላትና፣ ማርዘም
አማረኛችን የማጥበቅና የማላላት ምልክቶች የሉትም። እርግጥ ነው፣ ይህ እንደ ጉድለት መታየት የለበትም፣ የቃልን መጥበቅና መላላት ካገባቡ (context) ወይም ከአውዱ መረዳት ይቻላልና። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ይህ የማጥበቅና የማላላት አሻሚነት፣ አማረኛን እንዳበጁት እያስበጁ ውብ ከሚያደርጉት እጹብ ጠባዮቹ ውስጥ አንዱና ዋናው ነው።
ሮቢት አግኝታት ገበያው ሲቀናኝ፣ ቅዳሜ ማለዳ ቶሎ ና ብትለኝ
ሐሙስ አላልፍ ብሎ ዓርብ ዓመት መሰለኝ።
ቅዳሜ መሽቶልኝ እስኪደርስ ሰንበት፣ ከሷ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት
ላፈር አይደለም ወይ የተፈጠርኩት።
አንዳንድ ጊዜ ግን ማጥበቅና ማላላትን ያለ አሻሚነት መግለጽ የግድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ለዚህ መፍትሄ ደግሞ ታላቁ ጦቢያዊ ደራሲ ክቡር ሐዲስ ዓለማየሁ ከሚጠብቀው ፊደል አናት ላይ ነቁጥ (.) ለመጨመር አሳብ አቅርበው፣ በታላቁ መጽሐፋቸው በፍቅር እስከ መቃብር ላይ ተግብረውታል (በተግባር አውለውታል)።
እንደኔ አመለካከት ግን፣ ነቁጥ ከመጠቀም ይልቅ መጥበቅና መላላትን በሚከተለው መንገድ መግለጽ የበለጠ አመች ይሆናል። ማጥበቅ ሲያስፈልግ፣ የሚጠብቀው ፊደል ወይም ፊደሎች በሁለት ፊትጌ ዘብሪሶች (forward slash, /…/) መካከል ይገባል። ማላላት ሲያስፈልግ ደግሞ፣ የሚላላው ፊደል ወይም ፊደሎች በሁለት ኋልጌ ዘብሪሶች (backward slach, \…\) መካከል ይገባል። ዘብሪስ (slash) የሚለው ቃል የተገኘው እዝባር ከሚለው ቃል ሲሆን፣ ግሱም ሲረባ ዘበረሰ (to slash)፣ ዝብርስ፣ ዘብራሽ፣ ዝብረሳ እያለ ይሄዳል።
ለምሳሌ ያህል አ/ለ/ ማለት ይገኛል ማለት ሲሆን፣ አ\ለ\ ማለት ደግሞ ተናገረ ማለት ነው። የሚጠ/ብ/ቅ ማለት የሚቆይ ማለት ሲሆን፣ የሚጠ\ብ\ቅ ማለት ደግሞ የሚጫኑት ማለት ነው። /አካፋ/ (drizzle) ማለት በትንሹ ጣለ ማለት ሲሆን፣ \አካፋ\ (shovel) ማለት ደግሞ ባለጀታ ማፈሻ ማለት ነው። /ያለኝ/ ማለት የያዝኩት ማለት ሲሆን፣ \ያለኝ\ ማለት ደግሞ የነገረኝ ማለት ነው። \ዱቤ\ ማለት ብድር ማለት ሲሆን፣ /ዱቤ/ ማለት ደግሞ የፈረንጅ ሽንብራ ነው። ሽንብራ /ዱቤ/ አይገኝም \በዱቤ\።
ፊደልን ለማጥበቅ ወይም ለማላላት ፊትጌ እና ኋልጌ ዘብሪሶችን (slashes) እንደምንጠቀም ሁሉ፣ ፊደልን ለማርዘም ወይም ለመገተት ደግሞ አጭር ቀስት (→) እንጠቀማለን። :: ለምሳሌ ያህል በ→ጀ፣ ኧ→ረ ይሆናሉ::
መስፍን አረጋ
mesfinarega.com
mesfinamharic.com
mesfin.arega@gmail.com